የሌለው የወያኔ ህገ መንግስት

የሌለው የወያኔ ህገ መንግስት
ሸንቁጥ አየለ 

የሌለው የወያኔ ህገ መንግስት

የሌለው የወያኔ ህገ መንግስት

ወያኔ ኢትዮጵያዊ አይደለም እና የጻፈው ህገ መንግስት ኢትዮጵያዉያኖች እንዲጫረሱ በሚያመች መልክ ነዉ።

የወያኔን ህገ መንግስት የኢትዮጵያ ህዝብ 26 አመታት ሙሉ የሌለ ህገ መንግስት መሆኑን ያዉቃል። ወያኔ አለ እያለ ቢዘላብድም  በራሱ በወያኔ የፈረሰ ህገ መንግስት ነዉ። ወያኔ ህግ አይገዛዉም። ወያኔ በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ የሰራዉ ነገር ሁሉ ፈራሽ ነው።

ወያኔ  ጸረ ኢትዮያዊ ሀይል ስለሆነ በኢትዮጵያ እና በኢትዮጵያዊነት ጉዳይ ላይ አንዳችም ህጋዊነት የለዉም። የኢትዮጵያን ህገ መንግስት የኢትዮጵያ ህዝብ እራሱ ተስማምቶ እና ተነጋግሮ ይጽፋል።

ኢትዮጵያዉያን የብሄር እና የቋንቁዋ ልዩነታቸዉን በሰከነ ሁኔታ ተነጋግረዉ ሁሉንም ነገር መልክ ያሲዙታል። ለሁሉም ኢትዮጵያዊ የምትመች ዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ በኢትዮጵያዉያን ትሰራለች።

ወያኔ የዘራዉ መርዝ ሁሉ ይነቀላል።ወያኔም ከኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ጋር እድል ፈንታ የለዉም። ወያኔ የጻፈዉን ህገ መንግስት እራሱን አሸክሞ እንዲቃጠል ይደረጋል። ስለሆነም ወያኔ ብቻዉን ጽፎ ለኢትዮጵያ ህዝብ ህገ መንግስት ብሎ የሚዘባርቀዉን ሰነድ ከቁም ነገር አትቁጠሩት።

7 thoughts on “የሌለው የወያኔ ህገ መንግስት

  1. ብዙ ዲሞክራሲን (ህግና ስርአት) የሚከተሉ ሃገሮች ህገ መንግስት ቢኖራቸዉም ሌሎች ህገ መንግስት የሌላቸዉ ዲሞክራት ሃገሮች ብዙ ናቸው። ይህም ማለት የተጻፈ ህገ መንግስት የሌላቸው ነገር ግን በህግና ስርአት የሚመሩ ሃገሮች አሉ ማለት ነው።

    እንዲያዉም እነዚህ የማስመሰያ ህገ መንግስት የሌላቸዉ ሃገሮች በዉስጥ የሚያወጡአቸዉን መመሪያና ህጎች በማክበር የታወቁ ናቸው። ህገመንግስት ሳይኖራቸው የህዝባቸዉን ሰብአዊ መብትና እኩልነት በማስከበር አንቱ ከተባሉ ሃገሮች ውስጥ የሚከተሉትን መጥቀስ ይቻላል።

    ታላቁዋ ብሪታያ
    ሰሜን አየርላንድ
    ካናዳ
    እስራኤል
    አዉስትራሊያ ይገኙበታል

    ወያኔ የኢትዮጵያንና የአለምን ህብረተሰብ ለማታለል የጻፈው (ያስጻፈው) ህገመንግስት አለኝ እያለ ህዝቡ ዋጋ የሌለዉን የዉሸት ሰነድ እንደ ጣኦት እንዲያመልክበት ሓያ አምስት አመት ሙሉ ፕሮፓጋንዳዉን ነዝቶአል። በነገራችን ላይ ህገ መንግስት ለኢትዮጵያ አዲስ አይደለም። በአጼ ሃይለስላሴ ዘመን ሲሰራበት ነበር።

    ህገመንግስት አለኝ የሚለው ወያኔ ህገ መንግስቱን በሚጻረር መልኩ (ከጻፈው ህገ መንግስት ዉጭ) የሰው ዘርን በማጥፋት በማሰር በመቀጥቀጥ በመዝረፍ ከስራና ከአያቶቻቸው መሬት ላይ ህዝብን ህገወጥ በሆነ መንገድ በማፈናቀል ዘግናኝ ወንጀሎችን ፈጽሞአል። ለዚህ ነው የወያኔ ህገ መንግስት የዉሸትና ገበሬ እህሉን ወፎች እንዳይበሉበት እርሻው መሃል ከሰቀለው አሻንጉሊት የማይሻለው።

Leave a Reply