ኮከብ

ኮከብ (አዉደ ነገስት)

የምእራባዉያን ኮከብ ቆጠራ (አስትሮሎጂ) ቅምር በሆሮሰኮፕ (Horoscopes) ላይ የተመሰረተ ነዉ: ዪህም ማለት የአንድን ግለሰብ ሁለንተና ወይም ዕጣ ፋንታና ታሪኩን ለመተነበይ የጠሀይን፤ የጨረቃንና የሌሎች ፕላኔቶችን አቅጣጫ በመከተልና ከልደት ቀን ጋር በማገናኘት ነዉ።

ኮከብ
አስራ ሁለቱ ኮከቦችና ምሳሌአቸው

 ከምእራባዉያን ኮከብ ቆጠራ (አስትሮሎጂ) ሌላ በመላዉ  ዓለም በይበልጥ ታወቁት የህንድና የቻይና ኮከብ አቆጣጠሮች ናቸዉ። የኢትዮጵያዉያን የኮከብ አቆጣጠር ራሱን የቻለ ቀመርና አተረጘጎም አለዉ፡ በጣም የሚያስገርመው ነገር ኢትዮጵያዉያን በስም ላይ በመመርኮዝ የግለሰብን ሁለንተና ወይም ዕጣ ፋንታና ታሪኩን ብቻ ሳይሆን ሚወለድበትን ቀን ጭምር ያመለክታሉ፡

ትንሽ ስለ ኮከብ ቆጠራ ታሪክ

ዛሬ  በዚህ  ዓለም  ያለውና የሚታየው  ጥበብ  ሁሉ  ከጥንት  ጀማሪወቹ ነገደ  ኩሣ  ናምሩዳውያን  ከመርዌ  ሓበሻ (አበ-ኣሻሕ) ኢትዮጵያ  ወይም  የኩሽ ልጆች  መሆናቸውን ጊዜው  አጉልቶ  እስኪገልጸው  ድረስ  በትንንሽ  ሐውልትና   በጥቃቅን ነገሮች ላይ ተጽፎ ይገኛል፡፡  ዋናው  ትልቁ  የኢትዮጵያ ታሪክና እዉቀታችን ኤሮፓዉያን ዱሮ  የወሰዱት “መጽሃፈ ፀሐይ” የሚባለው መጽሃፋችን ነው።  ጀርመን ሀገር ዉስጥ ነዉ ያለው ይባላል፡፡

የኤውሮፓ ሊቃውንቶች  ይህ  አሁን በአክሱም  ያለው ትንሹ  ሓውልት  በማድነቅ  ከጫፉ  ላይ  ተነድሎ  መዳብ  ሽቦ አለውና  መጥረቡም  ማምጣቱም  ማቆሙም  በኤሌክትሪክ  ኃይል  የተከናወነ ነው ይላሉ  ፡፡  የሐውለቱም  ቁጥር 120 ነበር  ይባላል ፡፡ የሓውልትና  የፒራሚድ  ሥራ  የተጀመረውም 4ቱ  ነገሥታተ  ኢትዮጵያ፡- ኣክቴ ሳኒስ ፣ መንድስ ፣ጵሮተውስና  አሞሲስ ምስርን (ግብጽን) ደርበው  በገዙበት ጊዜ  ነው፡፡  ዓመተ ዓለሙ ከ2473 – 2936 ፡፡ ከክርስቶስ ልደተበፊት ከ1531-1868 ነው፡፡ ኢዘንበርግ  14ኛ  ገጽ ሦስተኛ  ጰሪዮዶስ (ክፍል) ዋዜማ  ምዕራፍ 3 ገጽ 13 ፡፡ ተመልከት  ዘፍ  11፡ 3፡፡ 

 

Amharic Ethiopian Zodiac
አስራ ሁለቱ ኮከቦች ወሮቻቸውና ምሳሌወቻቸው

ለታሪክ  ዋና  መሰረቱ  ቋንቋ ነው  ስለሆነም ኤልክትሪክ  በኢትዮጵያ  ለመጀመሩ ዋና  መስረጃው በአማርኛና በግዕዙ  ወንጌለ  ሉቃስ  ምዕ 11 ቁ 36 ፡ ከመ  ማኅቶተ  መብረቅ  ያበርሀከ  የሚለውን ቃል  የግዕዝና በአማርኛ ቋንቋ  የኤሌክትሪክን  የመብረቅ  መብራት መሆኑን  ለይቶ ያስረዳናል ፡፡   ጥንት  በግብጽ የነበረው የሐውልትና ፒራሚዶች የልዩ ልዩ  ጥበብ  ሁሉ ግብጻውያን ከኢትዮጵያውያንኖች  ከስናርና (ሰነዓር) ከመርዌ  ከተማ  ቀድተው  እንደወሰዱት የዓለም  ታሪክ  ከኢዘንበርግ መጽሐፍ  2ኛ  ጰሪዮዶስ  በገጽ 13 ይገኛል ፡፡ ዘፍ  11 ፡ 1-6 ፡፡

መጻሕፍቶቻችን  ሁሉ  ኤውሮፓውያኖች  ወስደውት በየ ቤተ-መጻሕፍቶቻቸው (Bibliotheca) በክብር  አስቀምጠዋቸዋል ይባላል፡፡ ሥለዚህ  አሁን  ያለው  ጥበብ ሁሉ ግብጻውያን ጥንት ከኩሣውያን (ኢትዮጵያውያን)  እንደቀዱት ሁሉ  ኤውሮፓዎችም  አሁን  የሚጠቀሙበት  ጥበብ ሁሉ ከኢትዮጵያ መጻሕፍት የተቀዳ ነው ቢባል የሚያስደፍር እውነት ነው እነጅ  የሚያሳፍር  ሐሰት  አይደለም  ፡፡ ኢዮ 28 12-19 ፡፡ኢሳ 18  ፡፡

ዛሬ ግን የዚሁ ዝርያ አዳድ ገጽ ቁንጽል  የታሪክ  ጥበብ የያዙ  ጥቂት  መጻሕፍት  ቢኖሩና ቢገኙም  በካህናት  እጅ  ብቻ  ሥለሆኑ  ሚስጥር እንዳይባክን በማለትና ሚስጥራዊ ሀይል አላቸው ብለው ስለሚያምኑ ሰው  ዕንዳያውቅባቸው ሠውረው ይዘዋቸው ይኖራሉ፡፡  ለሰው ልጅ እጅግ ጠቃሚ የሆኑ መድህኒቶችንና አቀማመማቸዉን ሳያሳዩና ሳይጠቅሙበት ደብቀው እንደያዙት ከዚህ ዓለም የሚለዩም አሉ::  

ከልጆቻቸው ዉስጥ አንዱን በመምረጥ ወይ ከቤተ ዘመድ ወይም በአካባቢ ለሚያዉቁት ቁምነገረኛ ልጅ ማሳየትና ማስተላለፍ ሲገባ ሳያስተላልፉ መሞት ሥህተትና መጥፎ  ሊቅነት  ነው፡፡ ከዚያም ሌላ አንዳንድ የህብረተሰብ ክፍሎች (የኛዎቹ ኢትዮጵያዉያን) ሃገር በቀል የሆነዉን እዉቀት ለመማር ከመሞከርና ከማሳደግ ይልቅ ጠንቁዋይ መድሃኒተኛ እያሉ ተመራማሪዉንም ሆነ ተጠቃሚዉን በመሃይም አንደበታቸዉ እያንቁዋሸሹ በሌላ በኩል ደግሞ ያንኑ የሚመስል ግልጋሎት ከምእራብና ከምስራቃዉያን በማድነቅ ይቀስማሉ።

ዛሬ ብዙ ኢትዮጵያዉያን በየሃገሩ በሚወጡ ጋዘጦች ዌብሳይቶችና መጽሄቶች ላይ ተተክለው ብዙ ሰአታት እንድሚያጠፉ ጥናቶች ያመለክታሉ። ታዲያ የዉጭው ሰው ሲያደርገው ስልጣኔ ኢትዮጵያዉያን ሲያደርጉት ደግም ጠንቃይ የሚያሰኛቸው ምን ይሆን? እዉቀት ድረገጽ የእዉቀት መጀመሪያ እግዚአብሄርን መፍራት መሆኑን እናምናለን። ተፈጥሮንና የሰዉን ልጅ ባህሪ ማወቅ ማድነቅና መመራመር የእግዚአብሄርን ረቂቅ ስራ እንድንረዳና እምነታችን እንዲጠነክር ይረዳናል እንጂ መንፈሳችንን ከዚያ ዉጭ እንዲያስብ አያደርገዉም።  ከዚህ  እውነታ  በመነሳት የኢትዮጵያን  ጥበባትና የምናዉቀዉን እውቀት  ሁሉ  ለትዉልድ  ማስተማርና ማስተላለፍ ይኖርብናል ፡፡ 

ኮከብዎን፡ማንነትወትንና ዕድልዎን ለማዎቅ ከታች ያለዉን ርእስ ይጠቁሙ :: ይቀጥላል::

የአስራሁለቱ ኮከቦች

የአስራሁለቱ ኮከቦች ባህሪና እድላቸው ሲተነተን