ሰምና ወርቅ

ሰምና ወርቅ ትምህርት
ሰምና ወርቅ ትምህርት

ሰምና ወርቅ      

ነይልኝ በፈረስ በሚገስግሰዉ!
መቸ በቅሎ ያዉቃል እንዳንቺ ያለ ሰዉ

ሞጣ ቀራኒዮ   ምነዉ አይታረስ
በሬ ሳላይ መጣሁ ከዚያ እስከዚህ ድረሰ

አዉው ብትል ጅቦ መች እፈራሃለሁ
ና ብላኝ ና ብላኝ እደጅዋ ቆሜአለሁ

አዳራሹ ሰፊ ቤቱ አልጠበባችሁ
በተራ በተራ ምነዉ መግባታችሁ?

ከበጌምድር ጎጃም ተሻገር ያልከኝ
ሰሜን ወደሁዋላ ተመልከትልኝ

ለምን ገለበጡት ወተቱን በጋን
ችዬ እገፋዋለሁ የማልለዉን

ከዚያ ላይ ያለች፣ሸክላ ሰሪ፣
ድሃ ናት አሉ፣ ጦም አዳሪ፣
ማን ነገራት፣ጥበቡን፣
ገልአፈር መሆኑን።

በጎጃም ያካፋል በሸዋ ፀሀይ 
በጎንደር ደመና መቅረቱ ነውይ 

ቤተስኪያን ስሞ፣ ለመኖር፣
መልካም ነው አሉ፣ ጎንደር፣
አይቀርምና፣መዳኘት፣
ከተማሰው፣ መግባት።

በገዛ አገራችን በገዛ ወንዛችን 
በሉ እጠቡንና እንግባ እቤታችን

ቢወጡም ቢወርዱም ቢዞሩም በዓለም፣
እንደ ባልንጀራ የሚስማማ የለም
 

ቢጮኸው ቢያነባው ስላልጠቀመው፣
ድኾ በጉልበቱ ነው ያለቀሰው
 

ባለሁበት ሰፈር፣
እኔን ጠበበኝ ምድር፣
አንተ ነህና አለኝታዬ፣
አስፋ ወሰን ጌታዬ
 

ባልሻሪው ቢሠራ በዶማ ባካፋ፣
የዘሩትም ቀረ አልበቀለም ጠፋ
 

ባልሽ ወዴት ሄደ ብለን ብንጠይቃት ስለ ጉዳያችን፣
ተሰብሮ አሁን መጥቶ ተኝቷል አለችን
 

ቢገዛን በጠላሁ የራስ ኃይሉ ልጅ
የኃላውን ካሳ ብፈራ ነው እንጅ
 

ባሁኑ ጦርነት ማንም ማን አይኮራ
ኃይለ ሥላሴ ነው ይኸንን የሠራ

አልነገርሽም ወይ ባላባት ነኝ ብለሽ
እንግዲያ ምነዋ ከዚህ ሃገር የለሽ?

የጠጅህን ማማርብርሌህ ነገረኝ

ከጠላህ አደርስም ምንም ቢቸግረኝ።

ሰምና ወርቅን አባባሎችንና ሌሎች አስደናቂ የዓማርኛ አነጋገሮችን ለማንበብና የዕዉቀት አድማስዎን ለማስፋት ከታች ባሉት መገናኛወች ላይ ይጠቁሙ