ሎሬት ጸጋዬ ገብረመድህን ቀዌሳ የ1950 ዓ.ም የትግራይ ረሃብ የመቀሌ ቆይታውና ትዝታው

ሎሬት ጸጋዬ ገብረመድህን ቀዌሳ የ1950 ዓ.ም የትግራይ ረሃብ የመቀሌ ቆይታውና ትዝታው

ሎሬት ጸጋዬ ገብረመድህን ቀዌሳ የ1950 ዓ.ም የትግራይ ረሃብ የመቀሌ ቆይታውና ትዝታው በዶክተር አሰፋ ነጋሽ – (በሆላንድ  ነዋሪ  የሆኑ  ኢትዮጵያዊ  ስደተኛ)  – 8th of September 2016  Email Address——————– Debesso@gmail.com 

በትያትር ድርሰት ጽሁፎቹ በትርጉምና የግጥም ስራዎቹ ታዋቂነትን ያተረፈው ሎሬት ጸጋዬ ገብረመድህን ቀዌሳ (ነፍሱንይማርና) 1987 . እዚህ በስደተኛነት ነዋሪ የሆንኩበት ሆላንድ ሀገር መጥቶ በርካታ ኢትዮጵያውያን በተገኙበት ህዝባዊ ስብሰባ ላይ ንግግር አድርጎልን ነበር። እንደሚታወቀው ጋሽ ጸጋዬ የወያኔ መንግስት ስልጣን ላይ እንደወጣ የደረሰው ወይምየጻፈው አንድ  ሀሁ  ፐፑ የተሰኘ የትያትር ስራው ለህዝብ እንዳይታይ ታግዶበት ነበር። አዋሳን በመሰሉ የኢትዮጵያ ከተሞች ደግሞ ተዋንያን መድረክ ላይ ሆነው ትያትሩን ሲተውኑ በወያኔ ወታደሮች በዱላ እየተደበደቡ ተውኔቱ እንዲቋረጥ ተደርጓል።

ሌላው ቀርቶ በቀዳማዊ ኃይለ ስላሴ ዘመነ መንግስት ለታላቁ ጸረፋሽስት የኢትዮጵያ ሰማእትና አርበኛ ለአቡነ ጴጥሮስ ማስታወሻ የደረሰውንጴጥሮስ ያቺን ሰዓት የተባለውን ትያትር ለህዝብ እንዳይታይ የወያኔ ትግሬዎች መንግስት ማገዱ ይታወቃል። ጴጥሮስ ያቺን ሰዓት የተሰኘው ትያትር በዐጼ ኃይለስላሴም ሆነ በደርግ ዘመን ካለአንዳች እገዳ ለህዝብ ይታይ የነበረ ትያትር ነው። በወያኔ ዘመን ግን ይህ ተወኔት እንዳይታይ እገዳ ተጣለበት። ይህ የትግራይና የኢጣሊያን ፋሽስቶች ርዕዮተ ዓለማዊ አንድነትና ጸረ-ኢትይጵያ የድርጊት መመሳሰል የሚያስረዳ ይመስለኛል። በእዚህ ምክንያት ገና ወያኔ ስልጣን ላይእንደ ወጣ ጋሽ ጸጋዬን የመሰሉ ሰፋ ያለ ሀገራዊ አመለካከት ያላቸው የጥበብ ሰዎች የወያኔ ትግሬዎች መንግስት የጥቃት ሰለባ ሊሆኑ ችለዋል። ለነገሩ እንደ ወያኔ ያለ የፋሽስት ስርዓት በነጻነት እያሰቡ የጥበብ ስራዎቻቸውን የሚያዘጋጁ ሰዎችን አይታገስም። ታዲያ ጋሽ ጸጋዬ ስለ ወያኔዎች ጉዳይ አንስቶ እዚህ አምስተርዳም ከተማ ለተሰበሰብነው ኢትዮጵያውያን ሲናገር  የሚከተለውን 1950 ዓመተ ምህረቱን የትግራይ ገጠመኙን አጫወተን። 

ሎሬት ጸጋዬ ገብረመድህን ቀዌሳ የ1950 ዓ.ም የትግራይ ረሃብ የመቀሌ ቆይታውና ትዝታው

ጊዜው 1950 . በክረምቱ ወራት ላይ ነው። ጋሽ ጸጋዬ አዲስ አበባ ከሚኘው ለወትሮው የንግድ ስራ ትምህርት ቤት (Commerical School) ተብሎ  ከሚታወቀው ሰንጋ ተራ አካባቢ ካለው  ትምህርት ቤት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱንያጠናቀቀበት ጊዜ ነው። ታዲያ ጋሽ ጸጋዬ ገና ከወጣትነቱ ጀምሮ የነበረው የጽነ ጽሁፍ ዝንባሌው ጠንካራ ነበር። በዚህም ምክንያት አንድ መጽሃፍ ለማሳተም ይፈልግ ነበር። በዚያን ጊዜ ግን በተማሪ አቅም መጽሃፍ ማሳተም የማይሞከር ነገር ነበር።ግን ይህንን መጽሃፍ የማሳተም ፍላጎቱን ለሚቀርቡት ጓደኞቹ ከማካፈል አልቦዘነም ነበር።

ታዲይ በኮሜርስ ትምህርት ቤት አብረውት ከሚማሩት የቅርብ ጓደኞቹ አንዱ ስብሃት የሚባል የአስመራ ልጅ አንተ ይህን ያህልጠንካራ የሆነ መጽሃፍ የማሳተም ፍላጎት እያለህ አዲስ አበባ ላይ ባለው ውድ መጽሃፍ የማሳተሚያ ዋጋ ተስፋ እየቆረጥክ ከምትቀመጥ ለምን አስመራ መጥተህ እዚያ ለማሳተም አትሞክርም? አስመራ ላይ እኮ የመጽሃፍ ማሳተሚያው ዋጋ እዚህ አዲስ አበባ ካለው በእጅጉ ያነሰ ነው እያለ በተደጋጋሚ ምክሩን ያቀርብለት ነበር። ታዲያ ጋሽ ጸጋዬም የንግድ ትምህርት ቤት ትምህርቱን እንደ ጨረሰ እኔ እዚህ መሃል ሀገር ሸዋ ተወልጄ ከዚሁ ሳልወጣ ቆይቼአለሁኝ እስቲ ወደ ሰሜን ያለውንሀገሬንም ሄጄ ልየው በዚያውም መጽሃፍ አስመራ የማሳተሙ ነገር እንዴት እንደሆነም ለማወቅ ያስችለኛል ብዬ ወደአስመራ  ለመሄድ ወሰንኩ ብሎ ነገረን።

በዚያ ጊዜ ከአዲስ አበባ ተነስቶ አስመራ ለመድረስ ሶስት ቀናት ይወስድ ነበር። ታዲያ ወደ አስመራ በሚያደርገው ጉዞ እግረመንገዱን መቀሌ ላይ ማደር ግድ ይል ነበር። ስለዚህ  አንድ ምሽት መቀሌ ላይ አድሮ ጠዋት ወደ አስመራ የሚያደርገውን የመጨረሻውን ጉዞ ከመጀመሩ በፊት እሱና ሌሎች ተጓዦች  ያደሩበት ሆቴል ቁርስ ብሉ ብሎ ሻይ በዳቦ አቀረበላቸው። ጋሽ ጸጋዬም እንደ ነገረን ያንን የተሰጠውን ትኩስ ሻይና ዳቦ ይዞ እያለ ትንሽ ራቅ ብሎ የሰው ግርግር ይመለከታል። ያንን ዳቦና ሻይ እንደ ያዘ የሰዉ ግርግር ወደሚታይበት አቅጣጫ ፊቱን አዙሮ መራመድ እንደ ጀመረ ተመለስ ተመለስ የሚል ድምጽ ክኋላው ሰማ።

ጋሽ ጸጋዬ የሚሰማውን ድምጽ ከምንም ሳይቆጥር እንዲያውም በተጨማሪ ፍጥነትና ጉጉት ይህንን የግርግሩን መንስዔ ለማወቅ ተጣድፎ ወደ ግርግሩ ቦታ ያመራል። ግርግሩ ቦታ እንደ ደረሰ በርካታ ሰዎች በረሃብ ተጎድተው በየሜዳው ላይ ወድቀው ያያል። ያየው የወገን ስቃይ አሳዛኝ ነበር። ያንን የያዘውን ዳቦና ሻይ አስቀምጦ ከእነዚያ በረሃብ ከወደቁት ወገኖቹ አንዱን ትንሽ ልጅ ያነሳና እቅፉ ላይ ያደርገዋል። ከዚያም ያንን ለቁርስ የሰጡትን ዳቦ በሻይ እያማገ በደረቁት የልጁ ከናፍሮችና አፍ ላይ አደረገለት።

በረሃብ የደከመውና የጠወለገው ልጅ አይኖቹን ከፍቶ ለመንቀሳቀስ ሞከረና  ምግቡንም መመገብ ሳይችል ጋሽ ጸጋዬ እቅፍ ላይ እስከ ዘላለሙ አሸለበ (ሞተ)። ጋሽ ጸጋዬ የዚያን  ረሃብ ህይወቱን የቀጠፈውን የመቀሌ ልጅ መልክና አራስ ልጇን እተወለደችበት ሀረር ከተማ ጥላ በእናት ሀገር ጥሪ ስም የኢትዮጵያን ጦር ልትቀሰቅስ ኤርትራ ሄዳ በሻቢያ ፈንጂ ህይወቷ ያለፈውን ትዕግስት የተባለችውን ቆንጆዋን የሀረር ልጅ መልክ ምንጊዜም እስከምሞት ድረስ ልረሳ አልችልም ብሎ በተሰበረ ልብ ነገረን። በመቀጠልም የዚያን በእቅፉ ላይ በረሃብ የሞተውን የትግራይ ልጅ ታሪክለምን ሊነግረን እንደ ፈለገ በሚከተለው መንገድ አስረዳን።

“ክፋትን ያየ ሰው ክፋትን አጥብቆ ስለሚጠላው ባህርይው ይበልጥ ሰብዓዊ ይሆናል ብዬ አምን ነበር”!!!

ጋሽ ጸጋዬ የሚከተለውን አለን። ወያኔ አዲስ አበባ ገብቶ ስልጣን ይዞ የኢትዮጵያን ህዝብ ታይቶ ለማይታወቅ የጭካኔና የጥላቻ ድርጊት ሰለባ አደረገው። ወያኔ ስልጣን እስከ ወጣበት ጊዜ ድረስ በህይወቱ ክፋትን ያየ ሰው ያንን በእሱ ላይ የደረሰውን የክፋት  ስራ እየጠላው ስለሚኖር በሌሎች ሰዎች ላይ ያንን እሱ የጠላውን ክፋት ሊፈጽመውና ሊደግመውአይችልም ብዬ አምን ነበር። ወያኔ ስልጣን ላይ እስከወጣበት ጊዜ ድረስ ክፋትን ያየ ሰው በህይወቱ  ያየው ክፋት በሌላ ሰውላይ እንዳይፈጸም  አጥብቆ  ይከላከላል ብዬም  አምን ነበር።

ባጭሩ በሰው ልጅ ላይ የደረሰ የክፋትና የጭካኔ ስራ የሰውን  ልጅ  ይበልጥ ሰብዓዊ  ያደርገዋል (Cruelty ennobles human character) ብዬም አምን ነበር። ዛሬ ግን የክፋትና  የጭካኔ ሰለባ የነበረ ሰው እንዲያውም ይበልጥ ጨካኝና አረመኔ እንደሚሆን የወያኔዎች ተግባር  አስረዳኝ። ይህን ያልኩበትን ምክንያት ላስረዳችሁ። ዛሬ ደርግን በጠመንጃ ጥለው አዲስአበባ ላይ ስልጣን የጨበጡት የወያኔ መሪዎች  ከዚያ 1950  . በትግራይ ውስጥ ከተከሰተው ረሃብ የተረፉት ልጆችናቸው ብሎ ወያኔዎች እንዴት በጥላቻ ውስጥ ተወልደው በበቀልና በቂም ስሜት ተኮትኩተው እንዳደጉ በአምስተርዳሙ ስብሰባ ላይ አስረዳን። ጋሽ ጸጋዬ የትግራይ ረሃብ ከተከሰተ ከ33 ዓመታት በኋላ የደረሰበት ይህ ግንዛቤ በአይምሮ ሀኪሞች (ሳይካትሪስቶችና) በስነ ልቡና ባለሙያዎች (ሳይኮሎጂስቶች) ዘንድ በሰፊው የሚታወቅ  ክስተት ወይም ጉዳይ ነው።

ብዙውን ጊዜ በጥላቻና ክፋት ውስጥ የሚያድጉ ልጆች በእድሜ ከፍ ብለውም እስከ ህይወት ዘመን ፍጻሜያቸው ድረስ እነዚያኑ በህይወታቸው ውስጥ ያለፉባቸውን የክፋት ድርጊቶች በሌሎች ላይ ሲደግሙ ይኖራሉ። በዚህ ዓይነት የክፋትና የጥላቻ አዙሪት ሳይሰበር ከትውልድ ትውልድ፤ ከቤተሰብ ቤተሰብ ይሸጋገራል። ዛሬ በኢትዮጵያ በወያኔ የአገዛዝ ዘመንእንደሚታየው ክፋትና ጥላቻ ጎሳን ተንተርሶ ሲመጣ ደግሞ የሚያደርሰው ማህበረሰባዊ ቀውስ እጅግ የከፋና ሀገር አጥፊይሆናል።

የትግራይ ልሂቃን በጎሳ ማንነታችን ምክንያት ጭቆና ደረሰብን ብለው ጥላቻን መሰረት አድርገው ያጠነጠኑት  የትግራይ ብሄረተኛነት ከመቶ ዓመታት በላይ እንደ ተዳፈነ እሳት ፍም ውስጥ ውስጡን ሲግም ቆይቶ፤ ባለፉት ሃምሳ ስድስት አምስት ዓመታት ደግሞ በግራ ፓለቲካ መፈክሮች (በተማሪውና በግራው እንቅስቃሴ ውስጥ) ሽፋን ሲገፋ ቆይቶ እነሆ ባለፉት ለአርባ ሁለት ዓመታት ታላቅ የሆነ ኢትዮጵያን አፍራሽ የሆነ የፓለቲካ ኃይል ሆኖ ብቅ አለ።

ለዘመናት በትግራይ ማህበረሰብ ውስጥ ከትውልድ ትውልድ ይተላለፍ ከነበረ ጥላቻ ራሱን በትግል የወለደው ህወሃት የቀዝቃዛው ጦርነት ባአሳለጠለት ወይም ባመቻቸለት የምዕራብ መንግስታትና የእርዳታ ድርጅቶች ድጋፍ ታላቅ ኃይል ሆኖ በ1983 ዓ.ም የመንግስትነት ስልጣን ተቆጣጠረ። በማንነታችን ምክንያት አማራ የሚባል ህዝብ ጭቆና አድርሶብናል ብለው የተነሱት የትግራይ ብሄረተኞች ባለፉት አርባ ሁለት ዓመታት መላውን የትግራይ ህዝብ አሉታዊ በሆነ መንገድ በማንቀሳቀስ የአክራሪ ብሄረተኛነት መገለጫ የሆነውን የፋሽስት ስርዓት ፈጠሩ። የወያኔ ትግሬዎች የዛሬ ሃያ አምስት ዓመት ኢትዮጵያ ላይ የዘረጉት ፋሽስታዊ ስርዓት በዋናነት የአማራውን ህዝብ የጥቃቱ ዒላማ ቢያደርግም በአማራ የመሰላትን ትልቋን ኢትዮጵያን አፈራርሶ ታላቋን በእውቀት፤ በእንዱስትሪና በልማት የበለጸገች  ትግራይን ለወርቁ የትግራይ ህዝብ ለመገንባት እንዳለመ እስክ ቅርብ ጊዜ ድረስ በተለይ የአማራ ብሄር ጭቆና ሰለባዎች ነበርን ለሚሉ ለበርካታ የኢትዮጵያ ልሂቃን አልተከሰተላቸውም ነበር።

ወያኔ ስልጣን ላይ እንደወጣ ራሳቸውን ከምንም ነገር በላይ በኢትዮጵያዊነት ማንነት የሚገልጹ የአማራ ተወላጆች የወያኔ መንግስት የጎሳ ፓለቲካ ሀገር ያፈርሳል ብለው የሰላ ትችት ሲያቀርቡ፤ ይህንን ተቃውሞዋቸውን  በአስራዘጠነኛው ክፍለ ዘመን በአማሮችና በትግሬዎች መካከል ይደረግ የነበረው የስልጣን ሽኩቻ አካል አድርገው የሚያዩ የሌሎች ጎሳዎች ልሂቃን እንደነበሩ ለአንባቢዎቼ ማስታወስ እፈልጋለሁኝ። እነዚህ የሌሎች ጎሳ ተወላጆች ልሂቃን በዚህ ስሌት ነበር በሰኔ 1983 ዓ.ምየ”ሰላም ጉባኤ” ላይ ከአሜሪካና ከአውሮፓ ድረስ ፈጥነው ወደ አዲስ አበባ በመሄድ የወያኔን መንግስት ስርዓተ-ንግስ በ”ታዛቢ ስም” በአዳማቂነትና በአሸብሻቢነት ያጀቡት። ዛሬ እነዚህ ሰዎች ምንም ሳያፍሩ በስደት የተቃዋሚ ድርጅት አቋቁመው ተመልሰው የወያኔን መንግስት እንፋለማለን እያሉ “የኢትዮጵያ ታሪካዊ ወዳጅ ከሆነችው ሀገር ከኤርትራ”) ወያኔ መጣሁብህ፤ አታመልጠኝም እያሉ ከበሮአቸውን ይደልቃሉ።  

በአክራሪ የትግራይ ብሄረተኛነት የሰከሩት የዛሬው ዘመን የትግራይ ተወላጆች እንዴት ከኢትዮጵያዊነት ወጥተው፤ ለራሳቸው የተለየ ሰብዕና እንደሰጡና ራሳቸውንም በተለየ መንገድ እንደሚያዩ ከዚህ በታች ያሰፈርኩትና ባለፈው ሰሞን ከመላው አውሮፓ ተጠራርተው አምስተርዳም ላይ ተሰብስበው የነበሩትን የትግራይ ተወላጆች በስሜት ያስጨፈራቸው ዘፈን ይዘት ይመሰክራል። ከዚህ በታች የምጠቅሰው የወያኔዎች ዘፈን በተለይ ቀለም ቆጥረዋል የተባሉት የትግራይ ተወላጆች ጨርሶ መታወራቸውንና ለብዙዎቻችን የሚታየው እውነታ (ብርሃን) ለእነሱ የማይታያቸው መሆኑን በተጨባጭ ያሳየናል።

የወያኔ ትግሬዎች እንደ ዓይናቸው ብሌን የሚያዩት መንግስታቸው በኢትዮጵያ ውስጥ በአማራና በኦሮሞ ህዝብ ላይ የጅምላ ፍጅት አውጆ ኢትዮጵያን የሃዘን ማቅ ሲያለብሳት፤ እነሱ ደግሞ አምስተርዳም ላይ ያቅራሩና ይዘፍኑ ነበር። እነዚህ አምስተርዳም ላይ ድልድል ያለ ድግስ ደግሰው “እናሳያችኋለን፤ እጃችንን ታውቋታላችሁ” እያሉ በስሜት ይጨፍሩ የነበሩ የትግራይ ተወላጆች የትግራይን ጎሳ ታላቅነት፤ ምርጥ ዘርነት፤ አልበገሬነት ወዘተ ለሶስት ቀናት በቀጠለው ጭፈራቸውና ዳንኪራቸው ሲገልጹቆይተዋል። እነዚህ ኩሩዎቹ ትግራውያን  ከትግራይ በታች እንዳሉት ኢትዮጳያውያን  ዘራቸው ከእንክርዳድ ጋር አለመደባለቁን፤ እነሱ ብቸኛ የንጹህ ዘር ምንጭ ከሆነውና በጀግንነቱ፤ በቅርስ ባለቤትነቱ፤ በታሪኩ ወደር ከሌለው የትግራይህዝብ እንደፈለቁ፤ በዚህም ኩራትና ክብር እንደሚሰማቸው በሹሩባቸው

አጊጠውና በወርቃቸው ደምቀው እየዘፈኑና እየጨፈሩ አሳዩን። ዝርዝሩን በዓይናችሁ ለማየት Youtube ውስጥ ይህንን ይጫኑ። https://www.youtube.com/watch?v=o6dGJvkPtbE

እንግዲህ የአርያን ዝርያ ነን ያሉትም የጀርመን ናዚዎች ይህንኑ ዛሬ የትግራይ ተወላጆች የሚያሳዩትን ጣሪያ የነካ የብሄረተኛነት እብሪት ነበር ይገልጹ የነበሩት። ይህ ፋሽስታዊ አመለካከት የለኮሰው እሳት ነበር ለሃምሳ ሚሊዮን አውሮፓውያን ህይወት ህልፈት ምክንያት የሆነውና የሁለተኛውን ዓለም ጦርነት ያስነሳው።

ከመላው አውሮፓ ተጠራርተው አምስተርዳም ላይ የተሰበሰቡት ትግራውያን የሚከተለውን በህብረት እያዜሙ ነበር አክራሪ ብሄረተኛነት በሚፈጥረው የእብሪትና የኩራት ስሜት ውስጥ ሰጥመው ይዘፍኑና ይጨፍሩ የነበሩት።

የት ነው  አገርሽ?  ብለው  ቢጠይቁሽ  ትግራይ  ነው በያቸው። የት ነው አገርሽ? ብለው ቢሉሽ ትግራይ የጀግኖች  አገር  ብለሽ  ንገርያቸው። እነዚያ  ስለ  ሕዝባቸው  ሲሉ  የታጠቁ፤  ከደደቢት  የፈለቁ ትግሬዎች የሕዝባቸውን  ወኔ  የታጠቁ፤ ባለ  ሱሪዎች ጀግኖች  ናቸው። እኛ ትግራውያን ሁሉንም  ነን። ማለትም  የታሪክ፤ የቅርስ፤  የጀግንነት  መፍለቂያዎች  ነን። እኛ  ወያኔዎች  የእነዚያ  እንክርዳድ የማይደባለቅባቸው (ከጠራ ዘር የወጣን፤ ቆሻሻ ያልተደባለቀብን) ትግራውያን  ልጆችነን***።

ስለ አክራሪ ብሄረተኛነት ብዙ የጻፈ Ernst Gellner የተባለ ታላቅ የብሄረተኛነት ሊቅ (expert on nationalism) ሰዎች ብሄረተኛነት ስሜት ሲጠናወታቸው ራሳቸውን ማምለክ ይጀምራሉ ብሎ ነበር። እነሆ ይህ ከላይ የጠቀስኩትና ሌሎችም በስፋት በመጪዎቹ ጽ ሁፎቼ ውስጥ የምጠቅሳቸው የትግራይ ብሄረተኞች ዘፈኖች ይህንን የErnst Gellner አስተያየት በእጅጉ ያንጸባርቃሉ። የብሄረተኝነትን ጽንሰ-ሀሳብ ሀሁ ያልተረዱ ወይም በአንድ ህዝብ ላይ የሚፈጥረውን የስነልቦና ለውጥና የሚያሳድረውን ህሊና-አሳዋሪ ተጽዕኖ ሳይረዱና ሳይመረምሩ እንደዚሁ በደመነፍስ ያለፈውን የትግራይን ህዝብ ታሪክ (የእነ ራስ አሉላ አባ ነጋን፤ የእነ ዐጼ ዮሃንስን ወዘተ) እየጠቀሱ ስለትግራይ ህዝብ የማይናወጥ የኢትዮጵያዊነት መንፈስ ዛሬም ለሚሰብኩን ምሁራን ይህን ከላይ የጠቀስኩትንና ሌሎችንም ዛሬ በበርካታ የትግሬዎች ዘፈኖች ውስጥ የሚደመጡት ስንኞችን ይዘት እንዲመረምሩ በትህትና እጋብዛለሁኝ።

እነዚህን የመሳሰሉ በዘፈኞችም ሆነ በወያኔ ትግሬዎች መጽሃፍት ወዘተ ውስጥ የሚገለጹ ሃሳቦች የዛሬው የትግራይ ትውልድ በአመለካከቱ ጨርሶ ከኢትዮጵያዊነት መንፈስ የወጣ መሆኑን በማያሻማ መንገድ ያሳዩናል። በዚህም ምክንያት እነዚህ ስለ ትግራይ ተወላጆች ጥልቅ የኢትዮጵያዊነት ስሜት ባለቤት መሆን ዛሬም በረፈደው ሰዓት የሚሰብኩን የሞራል ዘማቾች (Moral Crusaders) እነዚህን ስንኞች እንዲመረምሩ በትህትና አሳስባለሁኝ። ይህ ጨርሶ ከኢትዮጵያዊነት የወጣ የዛሬው የትግራይ ትውልድ የሌሎችን ከትግራይ ውጭ ያሉ ኢትዮጵያውያንን ሰብዓዊነት እንደማይቀበል ማጤን ይገባናል።

ይህ ከኢትዮጵያዊነት አመለካከት የወጣ የዛሬው የትግራይ ትውልድ ከትግራይ ህዝብ ውጭ ያሉ ኢትዮጵያውያንን እንደ ሰው ፍጡራን ሳይሆን እንደ አውሬ ነው የሚመለከተው። የትግራይ ትውልድ ባለፉት አርባ ሁለት ዓመታት አይምሮው የተቀረጸበት ፋሽስታዊ አስተሳሰብ ራሱን ከሌሎች ኢትዮጵያውያን የበለጠ ሰብዕና እንዳለው አድርጎ እንዲመለከት አድርጎታል። ይህ የአክራሪው የትግራይ ብሄረተኛነት መገለጫ የሆነው ፋሽስታዊ አስተሳሰብ የትግራይ ተወላጆች ከራሳቸው ጎሳ ውጭ ያሉትን የኢትዮጵያ ተወላጆች፤ በተለይም የአማራውን ጎሳ ተወላጆች ዘራቸው መጥፋት እንዳለበት አደገኛ አውሬ እንዲቆጥሩ አድርጓቸዋል።

ካለአንዳች ርህራሄ በሰላማዊ መንገድ ድምጻቸውን ሊያሰሙ የወጡ ኢትዮጵያውያን ወጣቶችን፤ ህጻናትን፤ አሮጊቶችን፤ ሽማግሌዎችን በዓለማያ፤ በአወዳይ፤ በሮቤ፤ በጎባ፤ በአምቦ፤ በሻሸመኔ፤ በዶምቢዶሎ፤ በጎንደር፤ በባህር ዳር፤ በደብረ ታቦር፤ በአምባጊዮርጊስ፤ በዳንግላ፤ በመተማ፤ በደብረማርቆስ፤ በቡሬ፤ ወዘተ እየጨፈጨፈ ያለው አጋዚ የተባለው ልዩ ጦር የተገነባው ይህን መሰል አስተሳሰብ ባላቸው የትግራይ ተወላጆች ነው።

ከላይ በጠቀስኩት የዘፈን ግጥም ውስጥ ለማሳየት እንደሞከርኩት ይህ የአጋዚ ጦር የተገነባው የትግርኛ ተናጋሪዎች ያልሆኑትን ከትግራይ በታች ያሉ የኢትዮጵያ ተወላጆችን እንደ ሰው ማየት በማይችሉ፤ የሰው ልጆች ሁሉ እንደ ሰብዓዊ ፍጡር እኩል መሆናቸውን በማይቀበል አክራሪ የትግራይ ብሄረተኛነት ርዕዮተዓለም የተቀረጸ አመለካከት ባላቸው የትግራይ ተወላጆች ነው። የኢትዮጵያ ህዝብ ይህንን እውነታ በውል ሊያጤነውና በደንብ ሊገነዘበው ይገባል። ብዙውን ጊዜ ሰው ሌላውን ሰው የሚያየው እራሱን በሚያይበት መነጽር ነው። ሌባ የሆነ ሰው ሁሉ ሰው እንደሱ ሌባ እንደሚመስለው ሁሉ፤ በየዋህነት ህይወቱን የሚመራ የዋህ ሰው ጎረቤቱም እንደሱው የዋህ ነው ብሎ ያስባል። ስለሆነም ይህ የዋህ ሰው ጎረቤቱም እንደ እሱ የዋህና በጎ አሳቢ ስለሚመስለው ሊያጠፋኝ ይችላል ብሎ ከቶ አያስብም።

ባለፉት አርባ ሁለት ዓመታት የወያኔ ትግሬዎች በምን ዓይነት ጥላቻ ተኮትኩተው እንዳደጉ ከትግራይ በታች የሚኖረው የኢትዮጵያ ህዝብ እስከ ቅርብ ጊዜ ከቶ ሊረዳ አልቻለም። ወያኔዎች ከቂም በቀል በላይ በሆነ ስሜት ቁጥሩ ግማሽ ሚሊዮን ይገመት የነበረውን የኢትዮጵያ ጦር ቢያንስ አንድ ሚሊዮን ተኩል ከሚቆጥሩ የቤተሰብ አባሎቹ ጋር መንገድ ላይ ሲጥሉትና ሴቶችን ለሽርሙጥና፤ ወንዶች ልጆቻቸውን ለዱርዬነትና ለጎዳና ተዳዳሪነት ሲዳርጉ ዝም ብሎ ደንዝዞ ተመልክቷል።

ይህ ድርጊት ወራሪው የጣሊያን የፋሽስት ጦር ካደረገውም የባሰ ድርጊት ነበር። ግን ድርጊቱ የተፈጸመው ኢትዮጵያዊ መልክና ቀለም ባላቸው፤ እኛ የምንናገረውን ቋንቋ በሚናገሩ ሰዎች ስለሆነ የወያኔ ትግሬዎችን እንደወራሪው የጣሊያን ፋሽስት ልናያቸው አልቻልንም። ግን የወያኔ ትግሬዎች መታየት ያለባቸው ከወራሪው ጣሊያን ፋሽስት ባልተለየ ዓይን ነው። በእውቀት፤ በጥናትና በመረጃ የማይመራ ሀገራችንን ኢትዮጵያን የመሰለ  ሀገር እንኳን  ችግሮችን  አስቀድሞ  አጥንቶ  ለመተንበይ  ቀርቶ፤ ችግሮቹ  ከተከሰቱ  በኋላ  እንኩዋን ተመልሶ የችግሮቹን መንስዔ  ለማጥናት አይሞክርም። የእኛ ነገር ሁልጊዜ  አሳዛኝ ነው። ለምን  ቢሉ አንድ ነገር ማቃጠሉን  የምናውቀው አከላታችን  በእሳቱ  ከተለበለበ  በኋላ  ነው። አስቀድመን ችግሮችን  አውቀን ለመከላከል የሚያስችለን  ባህልና ክህሎት አልገነባንም።

እኛ ከሌሎች ሀገሮች (ለምሳሌ  ከዩጎዝላቪያ፤ ከቀድሞዋ የሶቬት ህብረት፤ ከሩዋንዳ  ወዘተ) መጥፎ ልምድ አንማርም። በዚህም ምክንያት የወያኔዎችን ጸረ-ኢትዮጵያዊነት ለመረዳት ሃያ አምስት ሙሉ እነሱ ባቀጣጠሉት እሳት መፈጀት ነበረብን። እነተስፋዬ ገብረአብን በመሳሰሉ የሻቢያና የወያኔ የቀድሞ ካድሬዎች ጭንቅላት በተቀመመ መርዝ አኖሌ (አርሲ) ላይ ሀውልት ተሰርቶ ሁለት ትልልቅ ጎሳዎች እርስ በርስ በጥላቻና በጎሪጥ ዓይን እንዲተያዩ ሲደረግ፤ የኢትዮጵያ ሀብት ወደ ትግራይና ወደ ኤርትራ (እስከ ባድሜ ጦርነት ድረስ) ሲጋዝ፤ ኤርትራ የቡና ላኪ ሀገር ስትሆን፤ ኤርትራ የጎጃምን ጤፍ በሀሰተኛ ብር እየገዛች ስትወስድ፤ የኢትዮጵያ የእንዱስትሪ ዘርፍ እንዲወድቅ ተደርጎ የኤርትራ ፋብሪካ ውጤቶች የኢትዮጵያን ምርቶች ከገበያ ሲያስወጡና የኢትዮጵያን ባለሀብቶች ሲያከስሩ፤ ሆርን የተባሉትን የኤርትራ ባንኮች የመሳሰሉ ኢትዮጵያ ውስጥ ገብተው የኢትዮጵያን የፋይናንንስ ተቋሞች ሲያዳክሙ፤ ወዘተ ቁጭ ብለን እናይ ነበር።

ሌላው ቀርቶ ኤርትራና ትግራይ ባድሜ ላይ በጦርነት ሲፋለᎀ በመካከላቸው የተፈጠረው ጠብ በድንጋያማው የባድሜ መሬት ሰበብ ሳይሆን ሁለቱ ኃይሎች የተጣሉት ከትግራይ በታች ያለውን የኢትዮጵያን ህዝብ ሃብት ሲዘርፉ ባደረጉት ማን የአንበሳውን ይውሰድ በሚል ጥል መሆኑን አልተገነዘብንም ነበር። በዚህም ምክንያት ከሰማንያ ሺህ በላይ ወጣቶች፤ በተለይም ከትግራይ በታች ካሉት የኢትዮጵያ ክፍሎች የወጡ የአማራ፤ የኦሮሞ፤ የደቡብ፤ የአፋር፤ የሶማሌ ወዘተ ተወላጆች የኢትዮጵያ ዳር ድንበር ተደፈረ ብለው ለመከላከል ትግራይ ሄደው ፈንጂ ረጋጮች ሆነው ደማቸውን በከንቱ ዛሬ በጥይት ለሚፈጁአቸው የትግራይ ተወላጆች ደህንነት ሲሉ አፈሰሱ። እኔ በጊዜው የኢትዮጵያ ህዝብ ወደ ባድሜ ዘምቶ ከወያኔ ጋር በመሰለፍ ለትግራይ ተወላጆች የሰጠውን ድጋፍ በጣም ስቃወም ነበር፤ ይህን በማድረጌም አልጸጸትም።

እንኳን ከትግራይ ርቆ የሚኖረው በርካታው በመሃልና በደቡብ የኢትዮጵያ ክፍል የሚኖረው የኢትዮጵያ ህዝብ ቀርቶ ከትግራይ ህዝብ ጋር በታሪክ፤ በጋብቻም ሆነ በጉርብትና እጅግ ቅርበትና ትስስር ያለው የወልቃይትና የጸገዴ ህዝብ ከትግራይ የወጡ ሰዎች ይህንን ያህል የጠላትነት ስራ ይሰሩብኛል ብሎ መጠርጠር ቀርቶ ሊያስብም አይችልም ነበር። ግን ያልተጠበቀው ሆነ፤ አይደረግም የተባለው ተደረገ። እንዴት ክፋትን ያየ እጅግ ክፉ ይሆናል? ጋሽ ጸጋዬንም ያስደነቀው ነገር ይህ ነው። ለመሆኑ የትግራይ ተወላጆች ክፋትንስ ቢያዩ እንዲህ እነሱ ባለፉት ሃያ አምስት ዓመታት በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ የፈጸሙትን ዓይነት የክፋት ስራ የትኞቹ እነሱ የአማራ መንግስታት የሚሏቸው መንግስታት ፈጸሙባቸው? ለመሆኑ እነዚህ እነሱ የአማራ መንግስታት የሚሏቸው መንግስታት ትግሬዎችን ለይተው የክፋት ስራ ሲፈጸሙባቸው በሌላው ኢትዮጵያዊ (አማራውንም ጨምሮ) ያልፈጸሙት ክፋት የቱ ይሆን? ውድ አንባብያን የትግራይ ብሄረተኛነት ታላቅ የጥፋት ኃይል ሆኖ ኢትዮጵያን እንደ ሀገር እያከሰመ ነው።

ባለፉት ሃያ አምስት ዓመታት ለትግራውያን የልማት፤ የደስታ፤ የተረጋጋ የሰላም ዘመን ይዞላቸው የመጣው የወያኔ መንግስት ከትግራይ በታች ላለው የኢትዮጵያ ህዝብ ደግሞ ጥፋትን፤ ሞትን፤ መፈናቀልን፤ የእርስ በርስ ጥላቻን፤ ፍጅትን ድንቁርናን፤ መሃይምነትን፤ በሽታን ወዘተ አምጥቷል። ከወያኔ ህልፈት እንኳን በኋላ የወያኔ መንግስት ዘመን ለትግራውያን የወርቅ ዘመን ሆኖ በጋራ ትውስታቸው (Tigrean collective memory) ውስጥ ሲዘከር ይኖራል። በተቃራኒው ከትግራይ በታች ለሚኖረው ለአብዛኛው የኢትዮጵያ ህዝብ (የምስራቅ ወያኔዎች ከሚባሉት ከአደሬ ጎሳ ተወላጆች በስተቀር  – ምክንያቱም አደሬዎች እንደ ወያኔ ጌቶቻቸው ይህን ዘመን እንደ ወርቅ ዘመን ያዩታል) የወያኔ ዘመነ መንግስት የጭለማ ዘመን ተብሎ ይዘከራል።

በእኔ እይታ ይህ የወያኔ ስርዓት ከእሱ በፊት የአንድን ህዝብ ማንነት ተንተርሶና በአክራሪ ብሄረተኝነት ተቃኝቶ ስልጣን ላይ እንደወጣው የናዚ ጀርመኖች ወይም የኢጣሊያን ፋሽስቶች ስርዓት ወደ መቃብሩ ይሄዳል። ይህ ሲሆን የወያኔ ትግሬዎች መንግስት ፋሽዝም በሚፈጥረው ስሜታዊነት እንደ መንጋ ባንድ ሃሳብ፤ ባንድ መሪና በአንድ ድርጅት ስር አሰልፎ የሚመራውን የትግራይ ህዝብ ከራሱ ጋር ይዞ ገደል ይገባል። ዛሬ ይህ አደጋ በብዙ ሚሊዮን ለሚቆጠሩ የወያኔ ትግሬዎች አይታያቸውም ምክንያቱም ህሊናቸው በብሄረተኛነት ስሜት ታውሮአልና!!!!! የወያኔ ትግሬዎች ታላቅ ውድቀት የማይቀርና እውን የሚሆን ጉዳይ ነው።

በእኔ እይታ የወያኔ ትግሬዎች የቁልቁለቱን ጉዞ በግልጽ ጀምረውታል። በቅርቡ በዋሽንግተንና በአምስተርዳም እንዳየነውና እንደታዘብነው የወያኔ ትግሬዎች ፈረንጆቹ እንደሚሉት በእሳተ ገሞራ ላይ ጭፈራቸውን እያቀለጡት (dancing on the volcano)ነው። የዘመናቸው ፍጻሜ ደወል ተደውሏል። ፍጻሜያቸውም ቀርቧል። ይህ ደግሞ ሊሆን ግድ ይላል፤ ለውጥ የተፈጥሮ ህግ ነውና!!!! ይህን ስል ወያኔዎች በአልሞት ባይ ተጋዳይነት ብዙ ጥፋት ሊያደርሱ እንደሚችሉ ለአፍታም ሳልዘነጋ ነው። ይህችን ጽሁፌን በጣም የማከብረው ታላቅ የማሲንቆ ተጫዋችና ዘፋኝ አቶ ቻላቻው አሸናፊ (አፈር ይቅለለውና) ስለ ኢትዮጵያ ሀገራችን መፍረስ ጠበቃሽ ማን  ይሆን፤ ዋስሽስ  ማን ይሆን? የነበረሽ  ሁሉ  እንዳልነበረ  ሲሆን”!!!!  እያለ ከዘፈነው ዘፈን፤

ሲጠፋ  የሚያየው  እልፍኝ  አዳራሹ 

አይጨነቅም  ወይ  ለነገው  ወራሹ?።

የሚሉትን ስንኞቹን አብሬው እየደገምኩ ህሊናቸው በአክራሪ የትግራይ ብሄረተኝነት ለታወረው የወርቁ (የታላቁን መሪ የመለስ ዜናዊን አገላለጽ በመከተል) የትግራይ ጎሳ ተወላጆች እነዚህን ስንኞች በጥያቄ መልክ በማቅረብ ስለነገው ድህረወያኔ ዘመን ትጨነቁ ይሆን? ብዬ በትህትና እየጠየቀኳቸው እደመደምድማለሁ። ይህን ጥያቄ የምጠይቀው የትግራይ ተወላጆች ወደህሊናቸው ይመለሳሉ ብዬ አይደለም። የወያኔ ትግሬ መሪዎችም ሆኑ እንደ እነሱ የታወሩ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ተከታዮቻቸው እንደ ሂትለር ጦር እስከ መጨረሻው ሰዓት ድረስ በአቋማቸው እንደሚጸኑ አውቃለሁ። የወያኔ ትግሬዎች ከእንቅልፋቸው የሚነቁት የወያኔ ኃይል እንደ ሂትለር ወይም ሙስሊኒ የፋሽስት ጦር ተንኮታኩቶ ሲፈርስ ነው። ያን ጊዜ ለአርባ ሁለት ዓመታት ያጠፏትን ኢትዮጵያን  ተመልሶ ለማግኘት መሞከር አስቸጋሪ  ይሆናል!!!   

*** ከላይ የጠቀስኩትን በአምስተርዳም የተሰበሰቡትን የትግራይ ተወላጆች በስሜት አሳብዶ ጣሪያ እንዲነኩ ያስደረጋቸውን ይህንን ዘፈን  እንዲተረጉምልኝ ጠይቄው ጥያቄን እንደ ወትሮው ወዲያው ተቀብሎ  ከትግርኛ ወደ አማርኛ ተርጉሞ የላከልኝ በአሜሪካን ሀገር ነዋሪ የሆነውን የትግራይ (አክሱም) ተወላጅ አቶ ጌታቸው ረዳ ነው። እሱ ላደረገልኝ ድጋፍ ምስጋናዬ ከፍ ያለ ነው። ወዳጄ አቶ ጌታቸው ዛሬ አሜሪካ ውስጥ ከሚኖሩት በሺዎች ከሚቆጠሩ የትግራይ ተወላጆች ወያኔን ፊት ለፊት ቆሞ የሚቃወመው ብቸኛው ሰው ነው። 

———————————————–መልካም ንባብ—————————————————-

7 thoughts on “ሎሬት ጸጋዬ ገብረመድህን ቀዌሳ የ1950 ዓ.ም የትግራይ ረሃብ የመቀሌ ቆይታውና ትዝታው

Leave a Reply