የዓማርኛ ንግግር ስህተቶች
| ትክክል √ | ስህተት Χ |
| ምን አልክ? | ምን እያልክ ነው ያለኸው? |
| እኔ የምለው | እኔ እያልኩ ያለሁት |
| ሃሳብ | ህሳቤ |
| የሚታወቁት/የምናዉቃቸው | እዉቅና ያገኙት |
| መታደስ | ህዳሴ |
| ምሳሌ | ተምሳሌት |
| መልስ ሰጥተዋል | ምላሽ ሰጠዋል |
| መጣሁ | መጣሁኝ |
| ጅምር የተጀመረው የጀመርነው | ጅማሮ |
| ተቀባይነት | ቅቡልነት |
| ሰዉነት | ሰብአዊነት |
| አለሁ | አለሁኝ |
| ሄድኩ | ሄድኩኝ |
| መጣሁ ወይም እየመጣሁ ነው | እየመጣሁኝ ነኝ |
| ዓይነ ዉሃው አላማረኝም | የዓይኑ ቀለም አላማረኝም |
| ከሙከራ/ከልምድ | ተሞክሮ/ተመክሮ |
| ሃሳቡ ለህዝብ እንዲሰራጭ | ህሳቤው ለህዝብ ተደራሽነት እንዲኖረው |
| ማዳበሪያው ለገበሬው እንዲደርሰው | ማዳበሪያው ለገበሬው ተደራሽ እንዲሆን |
| ማስካካት | ማሽካካት |
| ሰንደቅ ዓላማ | ባንዲራ |
| የግድ ነው/ግዴታ ነው/እንገደዳለን | ግድ ይላል |
| ማሰላሰል | ማንሰላሰል |
| እንጥፍጣፊ | እንጭፍጫፊ |
| ቢላዎ | ቢላ |
| አስበን/አስበንበት/ከግምት ዉስጥ በማስገባት | ታሳቢ አድርገን |
| ይሁን ወይም እሺይ | አሉታ |
| አይሆንም ወይም እምቢ | አወንታ |
| ጎታ | ጎተራ |
| አስገራሚ ነገር | ገራሚ ነገር |
| ከግምት ዉስጥ አስገብተን | ታሳቢግምት አድርገን |
| የምንቀበለው/የምንስማማበት | ቅቡልነት ያለው |
| የማንቀበለው/የማንስማማበት | ቅቡልነት የሌለው |
| ተቀባይ የሌለው የማንቀበለው የማንስማማበት | ቅቡልነት የሌለው |
| መተዳደር | መስተዳደር |
| መተዳደሪያ | መስተዳደሪያ |
| አስተዳደር | መስተዳደር |
| አስተዳዳሪ | መስተዳድር |
| ተዳዳሪ | ተስተዳዳሪ |
| ክብር (ከበረ አስከበረ አክባሪ ተከባሪ) | አክብሮት |
| ጥቅም | ጠቀሜታ |
| የምናቃቸው ወይም የሚታወቁ | እዉቅና ያገኙ |
| ያመለክታል | ያመላክታል |
| ታማኝ ወይም የሚታመን | ተአማኝነት ያለው |
| የማይታመን | ተአማኝነት የሌለው |
| መልስ ሰጠዋል | ምላሽ ሰጥተዋል |
| ክብር | አክብሮት |
| እናከበረዋለን | አክብሮት እንሰጠዋለን |
| አናከብረዉም | አክብሮት አንሰጠዉም |
| አናከብረዉም | ክብር አንሰጠዉም |
| ክብረ ቢስ ነው ወይም ወራዳ ነው | አክብሮት የሚሰጠው አይደለም |
| ሃሳቡን አከብራለሁ | ለሃሳቡ ክብር አለኝ |
ንግግር:- ለአንድ ውይም ከአንድ በላይ ለሆኑ ሰዎች የሚደረግ የቁም ነገር ንግግር
ወሬ:- የተረጋገጠም ይሁን ያልተረጋገጠ ተራ ወሬ ማዉራት

One thought on “የዓማርኛ ንግግር ስህተቶች”
Please leave your comments