ኢትዮጵያን ለማዳን

https://www.youtube.com/watch?v=lg_xKCG3urE&feature=youtu.be

ሀገራዊ የምክክር አደባባይ ራዕይ: ተልዕኮ እና መርህ መር የሀሳብ አምዶች

1. የሀገራዊ የምክክር አደባባይ ራዕይ
የሀገራዊ የምክክር አደባባይ ራዕይ ፍትህ ሰላም እኩልነት እና ዲሞክራሲ የሰፈነባት በምልዓት የበለጸገች አንዲት
ነጻ ኢትዮጲያን ማዬት ነዉ::

2. የሀገራዊ የምክክር አደባባይ ተልዕኮ
የሀገራዊ የምክክር አደባባይ ተልዕኮ የኢትዮጵያን አንድነቷን: የህዝቧን ሰላም እና ግዛታዊ ልኡዋላዊነቷን ጠብቃ
እንደ ሀገር እንድትቀጥል የሚፈልጉ እና የሚሰሩ ሀይሎች በአንድ ሆነዉ ሀገር የማዳን ስራ ለመስራት
የሚያስችላቸዉን አቅም እና ጉልበት እንዲያገኙ ብሎም የኢትዮጵያን ስነ መንግስት ለመረከብ የሚያስችል
የምክክር አደባባይ እንዲሆን ነው

3. የሀገራዊ የምክክር አደባባይ መርህ መር የሀሳብ አምዶች
1. ኢትዮጵያ ጥንታዊ ሀገር ነች:: ጸረ ኢትዮጵያዉያን እንደሚሰብኩት ኢትዮጵያ በቅኝ ግዛት የተۿጠረች ሀገር
አይደለችም:: በኢትዮጵያ በየትኛዉም አካባቢ መጤና እና ነዋሪ የሚባል ማህበረሰብ የለም:: ኢትዮጵያ
የኢትዮጵያዉያን ክዚያም ካለፈ የአማራ አጽመ እርስት ነች::

2. የነግዶችን እኩልነት መቀበል የኢትዮጵያን ጥንታዊ ሀገርነት መቀበል መገለጫ ነዉ:: በቀደምቲቱ ኢትዮጵያ
ጨቋኝ እና ተጨቋኝ ማህበረሰብ /ነገድ/ ብሄር አልነበረም:: በዚህ ዘመን ጸረ ኢትዮጵያዉያን (ማለትም
ወያኔ/ሻቢያ/ ኦነግ/ኦዴፓ/ደህዴን/አዴፓ/ኢህአዴግ/ብልጽግና/ጀዋራዉያን) የቀመሩትን መርዛማ የታሪካዊ
ፖለቲካ ትንታኔ ብሎም የነዙትን የጥላቻ ሀሰተኛ ትርክት መቀልበስ ብሎምይሄዉአስተሳሰብ ለአንዴና ለመጨረሻ
ጊዜ ከስሩ ተነቅሎ እንዲቃጠል ማድረግ ብቸኛዉ ኢትዮጵያን የማዳኛ መንገድ ነዉ::

3. በአማራ ማህብረሰብ ላይ በማኒስቶ እና በህገመንግስት እንዲሁም በፖለቲካ ፕሮግራሞች በመመራት የዘር
܄ፍጅት ልብዙ አስር አመቶች ሲከናወን ቆይቷል:: ጸረ ኢትዮጵያዉያ ሀይላት ሁሉ ይሄን
አማራን የማጽዳት ስራ ተጠናክሮ እንዲቀጥል እየተጉ ነዉ:: እንዲሁም አንዳንድ የኢትዮጵያን አንድነት ስም
ለብሰዉ የሚንቀሳቀሱ ግን በልባቸዉ ጥላቻን ለአማራ ማህበረሰብ ያረገዙ የፖለቲካ ድርጅቶችም በአማራ
ማህበረሰብ ላይ እየተከናወነ ያለዉን የዘር ܄ፍጅት በአይናቸዉ እያዩ ይክዳሉ::


ከአማራ ብሄር እና ከኦርቶዶክስ እምነት በተጨማሪ ልዩ ልዩ የኢትዮጵያ ብሄሮች/ነገዶችም አብረዉ የዘር መጽዳት
ኢላማ ተደርገዋል:: በዚህም የጌዴዎ: የጉራጌ: የሀድያ: የጋሞ: የሲዳማ: የወላይታ: የሶማሌ: የአሪ እና
ሌሎችም ብሄሮች ከተኛ የዘር ጭጨፋ܂ የሀብት ዉድመት እና የማፈናቀል ወንጀል ተፈጽሞባቸዋል::
የሀገራዊ የምክክር አደባባይ በግልጽ መርህ እና ሃሳብ ላይ በመቆም በኢትዮጵያዉያን ሁሉ ላይ እየተከናወነ ያለው
የዘር ܄ፍጅት በማንኛዉም መልክ መቀልበስ አለበት ብሎ ያምናል:: እንዲሁም የዘር ܄ፍጅት የተፈጸመበትን አካል
ይቅርታ ተጠይቆ ካሳ ይገባል ብሎም ያምናል::

4. የሀይማኖቶች እኩልነትን መቀበል ብሎም በኢትዮጵያ ማንኛዉም አይነት እምነት እና አመለካከት
በእኩልነት እንዲስተናገድ የሚያስችል ስርዓት መገንባት ይኖርበታል:: ኢትዮጵያ እምነቶች በጋራ ተቻችለዉየኖሩባት ሀገር ነች:: ሆኖም ኢትዮጵያን ለማፍረስ እና ኢትዮጵያዉያንን ለማዋረድ ይመቻቸዉ ዘንድ ጸረ ኢትዮጵያዉያን በኢትዮጵያ የነበረዉን የሀይማኖት መቻቻል እዉነተኛ ታሪክ በጥላቻ ትርክት ቀይረዉታል::

ሀገራዊ የምክክር አደባባይ ራዕይ: ተልዕኮ እና መርህ መር የሀሳብ አምዶች
በሀሰተኛ እናመርዘኛ ትርክት ጸረ ኢትዮጵያዉያ ሀይሎች ኦርቶዶክስ ጨቋኝ ነች የሚል ትርክት ይዘዉ መርዛቸዉን
እረጭተዋል:: በዚህም በኢትዮጵያ የሚገኙ ልዩ ልዩ ሀይማኖቶች መሀከል ጥላቻ እንዲሰ܄ን ሰርተዋል:: በተለይም
በኦርቶዶክስ እና በእስልምና ሀይማኖቶች መሃከል ጥላቻ እንዲኖር ሰርተዋል:: በእነዚህ ጸረ ኢትዮጵያ ሀይሎች
የፖለቲካ ትርክት መሰረት ኢትዮጲያ ዉስጥ የሀይማኖት እኩልነት ፈጽሞ አልነበረም። ኦርቶዶክስ ጨቋኝ እምነት
ሲሆን ሙስሊም ግን ተጨቋኝ እምነት ነበር ይላሉ። እነዚህ ጸረ ኢትዮጵያ ሀይሎች ኢትዮጲያ ዉስጥ የተደረጉ ܄ፍጹም
የሀይማኖት ܄መቻቻሎች እና አብሮ የመኖር ሂደቶችን ሁሉ ክደዉ ይነሳሉ።

በዋናነትም የጸረ ኢትዮጵያዉያን ፖለቲካዊ የሀይማኖት ትረካ ሙስሊም ኢትዮጵያዉያንን ስትጨቆኑ ነበረ፡
እኩልነት አልነበራችሁም፡ ኦርቶዶክስ ጠላታችሁ ነዉ በሚል ፕሮፖጋንዳ ጠፍሮ በማሰር በኢትዮጵያዉያን
ሀይማኖቶች መሀከል መቻቻል ሳይሆን የእርስ በርስ ጥርጣሬ እንዲነግስ የሚያደርግ ܄ነዉ። ይሄዉ የጸረ ኢትዮጲያዉያን የሀይማኖቶች
የፖለቲካ ትንታኔ ዋና ግብ በአለም መዝገብ የተመዘገበዉን፡ የእስልምና እምነት ዋናዉ መስራችና መሪ ነቢዩ መሀመድ ክርስቲያን ኢትዮጵያን አትንኩ። ክርስቲያን ኢትዮጵያ የሙስሊም መጠጊያ ከለላ ሀገር ነችና” ሲሉ የመሰከሩትን ቃል ለማረስ እና ለመሻራ የተገመደ የተንኮል ቀመር እና ስልት ነዉ።

በርካታ የእስልምና ምሁር ነን ባይ የሀይማኖት መሪዎቹ አንድ በጋራ የመሰከሩት እዉነት አለ:: ይሄም በጥንታዊት
ኢትዮጵያ የክርስቲያን ኢትዮጵያ ነገስታት እና መሳፍንቶች ሙስሊሞችን በፍርድ ቤታቸዉ በፍትህ እና በእዉነት
የዳኙ፡ እዉነትን የሚፈርዱ ናቸዉ። በዚህም በኢትዮጲያ የነበሩ ሙስሊሞች ልክ በሸሪያ ህግ እንደሚዳኙት
ሁሉ ደስ ብሏቸዉ ይኖሩ የነበር። ሀይማኖታቸዉንም በነጻነት ያስምልኩ እንደነበረ መስክረዋል። ይሄዉ እዉነት
ሲወርድ ሲዋረድ በበርካታ ክርስቲያን የኢትዮጵያ ነገስታት አስተዳደር ዘመን እዉን ሆኖ የኖረ ሀቅ ነዉ። ኢትዮጵያ
የሀይማኖቶች እኩልነት ብቻ ሳይሆን የሀይማኖቶች እና የእምነቶችም መዳኛ የነበረች ሀገር ነበረች። ይሄን ሀቅ
የማይቀበል፡ በኢትዮጲያ ሀይማኖቶች እና እምነቶች መሀል የጸረ ኢትዮጵያዉያንን የፖለቲካ ትረካ ተሸክሞ
የሚሹለከለክ ሁሉ የህዝባችን አጠቃላይ ጠላት ነዉ። 

5. እንደ አማራ ማህበረሰብ ሁሉ በሀሰተኛ ትርክት የዘር ማጥፋት እና ማጽዳት ኢላማ የተደረገችዉ የኦርቶዶክስ
ተዋህዶ እምነት ነች:: ስለ ሆነም ይሄን የዘር ማጥፋት ወንጀል ማዉገዝ: በማንኛዉም መንገድ እንዲቀለበ
መስራት ይገባል::

6. ሀገራዊ የምክክር አደባባይ ሂደት እና ራዕይን የማሳለጥ ግዴታ እንደሚያስፍልግም ሰፊ܁ ትንታኔ
አድርጓል:: የሀገራዊ ምክክር አደባባይ ራዕይ ካላይ ቁልጭ ብሎ ተቀምጧል:: ሆኖም በጸረ ኢትዮጲያዉያን የጎሳ
ፖለቲካ የተነሳ ኢትዮጵያዉያን በየነገዳቸዉ ተደራጅተዋል:: ሀገሪቱም ልትፈርስ ከፍተኛ መከራ እና ጭንቅ
ዉስጥ ገብታለች:: ስለሆነም በኢትዮጵያዊነት ብቻ መደራጀት የሚለዉ አማራጭ ሀገር ሊያድን የሚችል በቂ ጉልበት ሊሰበስብ አይችልም:: ከሁሉም በላይ ደግሞሀገሪቱ አሁን ባለዉ ሁኔታ በአንድ ድርጅት/ፓርቲ ከመፍረስ ልትድን አትችልም:: ሆኖም በራዕዩ ላይ ብቻ በመስማማት ከጸረ ኢትዮጵያዊነት አላማ ዉጭ በልዩ ልዩ መልክ የተደራጁ ሀይሎችን ማሰባሰብ እና በጋራ እንዲመክሩ ማስቻል ብሎም ሀገር እንዲረከቡ ማደረግ ብቸኛዉ መፍትሄ ነዉ::

ሀገራዊ የምክክር አደባባይ ራዕይ: ተልዕኮ እና መርህ መር የሀሳብ አምዶች
በነገድ: በሀይማኖት: በሲቪል ማህበራት: በፖለቲካ ፓርቲ ደጋ܁ፊነት: በኢትዮጵያዊነት ወይም በማንኛዉም ሁኔታ
የተደራጀዉን ኢትዮጵያዊ በአንድ እንዲቆም እና ሀገር ለመረከብ የሚያስችለዉን ስትራቴጂ በጋራ እንዲነድፍ܄
ብሎም ሀገር እንዲረከብ ብቃት ላይ እንዲደርስ ማስቻል ይገባል:: ይሄንንም በመረዳት ሀገራዊ የምክክር አደባባይ
ሂደት እና ራዕይን የማሳለጥ ግዴታን እዉን ለማድረግ የተዘረዘሩትን ልዩ ልዩ መርህ መር የሀሳብ አምዶችን
የሚቀበሉ ሀይሎች ሁሉ በአደባባዩ እንዲሳተፉዉሳኔ አድርጓል::

7. ምንም እንኳን አሁን ኢትዮጵያን ለማዳን በተለያዬ መልክ የተደራጁ ሀይሎችን ቢያቅፉም እንዲሁም
ኢትዮጵያዉያን በመሰላቸዉ እንዲደራጁ ቢያበረታታም: ቢያግዝም የሀገራዊ የምክክር አደባባይ የመጨረሻዉ
መዳረሻ ግን ኢትዮጵያን እንደ ሀገር ማቆም ይሆናል:: ኢትዮጵያን እንደ ሀገር ለማቆም ደግሞ የመጀመሪያዉ
እርምጃ ኢትዮጵያን መረከብ እና ኢትዮጲያን እንደ ሀገር የሚያስቀጥሏትን ሀገራዊ እርምጃዎችን መዉሰድ
ይሆናል:: ለዚህ አላማም ፋኖ ታጭቶአለ። ስለሆነም ፋኖ የጸረ ኢትዮጵያዉያንን ሀይላት ካሸነፈ በኋላ ኢትዮጵያን አሁን ካሉ ጸረ ኢትዮጲያን ሀይሎች በመነጠል ማሶገደ ይገባል:: ይሄዉም የወያኔን/ኦነግን ህገመንግስት በኢትዮጵያዊ ህገመንግስት መተካት: የጎሳ ፖለቲካ በህግ በማገድ የኢትዮጵያዊነት ፖለቲካን
የማስፈን ብሎም የጎሳ ክልሎችን በማፍረስ ለኢትዮጲያ ህዝብ የሚያመች ስራተእ መተካት የመጀመሪያው
እርምጃ ሊሆን ይገባል::

በመሆኑም አሁን በየነገዳቸዉ/ብሄራቸዉ እንዲደራጁ የምናበረታታቸዉ ልዩ ልዩ የብሄር/የነገድ ድርጅቶች ወይም
በራሳቸዉ ተደራጅተዉ ይሄን ሀገራዊ የምክክር አደባባይ የሚቀላቀሉ ልዩ ልዩ የነገድ/የብሄር/የሀይማኖት/የሲቪል
ድርጅቶች ወደፊት ኢትዮጵያን መረከብ ሲቻል እራሳቸዉን ወደ ሀገራዊ የፖለቲካ ድርጅት ለማሳደግ ከአሁኑ
የወሰኑ እንዲሁም የተዘጋጁ መሆን መቻል አለባቸዉ:: የዚህም ዋነኛ አላማዉ ኢትዮጵያዉያን ሀገር እንዲኖራቸዉ
ለማስቻል ከተፈለገ ኢትዮጵያን ከጸረ ኢትዮጵያዉያን ሀይላት (ወያኔ/ሻቢያ/ኦነግ/ኦዴፓ/ደህዴን/አዴፓ/ኢህአዴግ/ብልጽግና) ከቀመሩት መርዛማ የፖለቲካ ቀመር ማላቀቅ የመጀመሪያዉ እርምጃ መሆን ስላለበት ነዉ::

በመሆኑም

(ሀ) የወያኔን ህገመንግስት በኢትዮጵያዊ ህገመንግስት መተካት : የጎሳ ፖለቲካ በህግ በማገድ
የኢትዮጲያዊነት ፖለቲካን የማስፍን ብሎም የጎሳ ክልሎችን በማፍረስ ለኢትዮጵያ ህዝብ በሚመች አከላለል
የመተካት የመጀመሪያ እርምጃ ይወሰዳል

(ለ) ኢትዮጵያዊ መሆን እና የማንኛዉም ጎሳ አባል መሆን የሚደጋገ܄
እንዲሁም አብሮ የሚሄዱ መሆናቸዉ የሚካድ አይደለም:: ሆኖም ኢትዮጵያ አንድነቷ የተከበረ: የዜጎች እኩልነት
የተረጋገጠባት: ጠንካራ እና የበለጸገች ሀገር እንድትሆን ከማህበራዊ አደረጃጀት እና የሲቪል ማህበራት አደረጃጀት
ዉጭ በማንነት ላይ የተመሰረት፤ በሀይማኖት እና በጎሳ ላይ የተመሰረት የፖለቲካ ድርጅት በህግ መታገድ
ይኖርበታል::

(ሐ) የፖለቲካ ድርጅቶች ሊመሰረቱ እና ሊደራጁ የሚገባቸዉ በሀሳብ የበላይነት
መሰረት ነው (ዲሞክራት/ሪፐብሊካን/ሶሻል ዲሞክራት/ሊበራል ዲሞክራሲ /ሌላ ማንኛዉም አይነት ሀሳብ የተመሰረተ
እንዲሆን፣

(መ) የሃገራችን ኢትዮጵያ ሰንደቅ-ዓላማ ምንም ዓይነት ድሪቶ የሌለበት ጥንታዊዉ፣ የነጻነት ምልክቱና ታሪካዊዉ አረንጓዴ፣ ቢጫና ቀይ ይሆናል::

ሀገራዊ የምክክር አደባባይ ጋር አብረዉ ለመስራት ከወሰኑ በሚከተለዉ ኢሜይል ያገኙናል።
Ethiopiansaffair@gmail.com 

Leave a Reply