The 123rd Extraordinary Commemoration of the Victory of Ethiopia at the Battle of Adwa

የ፩፪፫ኛው የኢትዮጵያዉያን የድል ቀን አዲስ አበባ ዉስጥ ከፍኛ የሃገር ፍቅር በታየበት ሁኔታ ተከበረ
የ፩፪፫ኛው የኢትዮጵያዉያን የድል ቀን አዲስ አበባ ዉስጥ ከፍኛ የሃገር ፍቅር በታየበት ሁኔታ ተከበረ። ይህ አስደናቂ ትእይንት ለአንዳንድ ጸረ አንድነት ጸረ ሰላምና ጸረ ነጻነት አናሳ ሀይሎች ግልጽ መልእክት አስተላልፎአል። ተደጋጋሚ ድል ለነጻነት ወዳዱና ጀግናው የኢትዮጵያ ህዝብ ዉርደትና ሽንፈት ለባንዶችና ለጸረ ታሪክ ዘረኞች። ተደጋጋሚ ድል ለነጻነት ወዳዱና ጀግናው የኢትዮጵያ ህዝብ ዉርደትና ሽንፈት ለባንዶችና ለጸረ ታሪክ ዘረኞች።

The Extraordinary Commemoration of the Victory of Ethiopia at the Battle of Adwa and its Terrific Message to the Minority Ethnocentric (Fanatic) AntiUnity Elements in Addis Ababa!

የጸረ ኢትዮጵያዉያንና የጸረ አፍሪካዉያን የጥቃት ኢላማ የሆነችዉ የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማThe History and legacy of the Victory of Ethiopia at the Battle of Adwa has thought an important lesson for the World that independent nations can defend themselves from other aggressive dictator led countries. The victory of Ethiopia led by the the wise & glorious King Menelik II against the unjust war of Fascist Italy has been inspiring enslaved African and Asian people all over the world since 01 March 1896. Today the first independent Flag of Ethiopia is considered to be a symbol of freedom and justice across the globe. Happy Victory Day for Ethiopians, Africans and for All Peace Loving International Community.

የአድዋ ጦርነትና የኢትዮጵያዉያን ድል :- የካቲት 23 ቀን የቅዱስ ጊዮርጊስ ለት በ1888 ዓ.ም (እደ ኤሮፓ አቆጣጠር ማርች 1 ቀን 1896 ዓ.ም) የዓለምን የፖለቲካ አቅጣጭና በዘር ላይ የተመሰረተዉን ኢሰብአዊ ግንኙንት የለወጠ የፍትህና የመከላከል ጦርነት ኢትዮጵያ ዉስጥ አድዋ በሚባለው ቦታ ላይ ተካሄደ። ጦርነቱ የተካሄደው በእብሪት ከኤሮጳ ባህር ኣቁአርጦ በመጣው የኢጣሊያ ጦርና ዓለም ከተፈጠረች ጀምሮ ሀግሩ ዉስጥ በሚኖረው የኢትዮጵያ ህዝብ መካከል ነበር። ኢትዮጵያዉያን በጀግናና በብልህ ንጉሳቸው በዳግማዊ ምኒልክ ስር ተሰባስበው ዘመናዊ መሳሪያ ታጥቆ የመጣዉን ወራሪ ጦር ቅስሙን በመስበር የሃገራችውን ነጻነት አስከብረው መላው በባእድ አገዛዝ ስር የሚማቅቀው የአለም ህዝብ ተስፋ እንዲኖረው አድርገዋል:: ዳግማዊ ምኒልክ ኢትዮጵያ እንድታድግና ዜጎች እንዲጠቀሙ አስደናቂ የልማት ስራወችን በማከናወን ህዝቡ በሰላምና በስርአት እንዲኖር ኣድርገዋል።

በሌላ በኩል በጠላትና በደጋፊዎቹ ጸረ ሰላም እና ጸረ እኩልነት ሃይሎች ጎራ ከፍተኛ ድንቃጤን ከመፍጠሩም በላይ አንዳንዶቹም ቂም ከመያዝ አልፈው በረቀቀ መንገድ ሀዝቡን በመከፋፈል ለመጉዳት ከፍተኛ ተንኮል ሸረቡ:: የሁለተኛዉን የዓለም ጦርነት ኣጋጣሚ በመጠቀም በድጋሚ ወረራ አካሂደው አሰቃቂ የሆነ ኢሰብአዊ ድርጊት ፈጸሙ። ከዚያ ወዲህ ያለው ትዉልድ ታሪኩን እንዳያዉቅና እንዳይጠነቀቅ የዉሸት ጽሁፎችን በሀገር ዉስጥና በዉጭ ሃገር ሰዎች በማጻፍና በመበተን እልሀቸዉን በረቀቀ ስልት መወጣት እንድሚፈልጉ አሁን ያለዉን የኢትዮጵያ ሁኔታ በጽሞና ለሚከታትል ስዉር ሊሆንበት አይችልም። እነዚህ ሁለት የእብሪት ዎረራወች ታሪክ እራሱን ይደግማል የሚለዉን እንዳንረሳ ማስጠንቀቂያ ናቸዉ። ለዚህ ነው ታሪክን መማርና ማወቅ ያለብን በተገኘው ድል ለመኩራራትና ለመጠቀም ብቻ ሳይሆን ታሪክ እራሱን መድገሙ ስለማይቀር ለመዘጋጀትም ጭምር ነው::

በዚህ በብዙ ሺህ የኢትዮጵያዉያን መሰዋእትነት በተገኘው ድል ኢትዮጵያ አለኝታና ተስፋ ከመሆን አልፋ ለአፍሪካና ለሌሎች በባርነት ቀንበር ስር ለሚማቅቁ ህዝቦች የበኩሉዋን ድርሻ አበርክታለች። በዚህ የተንሳ ብዙ ሃገሮች ነጻ ሲወጡ የሰንደቅ አላማዋን ህብረ ቀለም ይወስዳሉ:: ጣሊያኖች በድጋሜ ኢትዮጵያን በወረሩበት ወቅት የኢትዮጵያኖችን ስነልቦናና ክብር ለመንካት ሰንደቅ አላማዋችንን ከተሰቀለበት ቦታ እያወረዱ ይረግጡት እንደነበረ በታሪክ ይታወቃል። ምንም እንኩአን የኢትዮጵያ ህዝብ ባይቀበላቸዉም ዛሬ የባንዳ ልጆች (ወያኔወች) ፋሽስቶች ካደረጉት ለወጥ አድርገው አባቶቻችን ተሰዉተው ያስረከቡንን ህጋዊና ታሪካዊ ሰንደቅ አላማችንን ባእድ አካል እመሃል ላይ በመለጠፍ የኢትዮጵያ ህዝ እዉቅና ያልሰጠዉን ባንዲራ በመስቀል ተደብቆ የቆየዉን ጸረ ኢትዮጵያ ድርጊታቸዉን በዉስጥ አርበኝነት በመፈጸም የህዝቡን ስነ ልቦና ከመጉዳትም አልፈው የዲሞክራሲያዊ መብቱን በመንፈግና ነፍሰገዳዮችን በማሰማራት ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ረገጣን በማካሀድ ላይ ናቸዉ። በዚህ የተነሳ መልካቸዉን ቀይረዉ በመጡት የዉስጥ ከሃዲወችና በነጻነት ወዳዱ ሰፊዉ የኢትዮጵያ ህዝብ መካከል በአሁኑ ሰአት የከረረ ትግል በመካሄድ ላይ ነው። የአድዋን ድል ኢትዮጵያዉያን ይደግሙታል:: ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!! አመሰግናለሁ!!

ሰምና ወርቅ የአድዋ ጦርነትና የኢትዮጵያዉያን ድል