ከሜቴክ አመራሮች ጋር የሚታይና የጠ.ሚ. አብይ መንግሰት መርሳት የሌለበት ጥብቅ ጉዳይ 

ከሜቴክ አመራሮች ጋር የሚታይና የጠ.ሚ. አብይ መንግሰት መርሳት የሌለበት ጥብቅ ጉዳይ 

 

ከሜቴክ አመራሮች ጋር የሚታይና የጠ.ሚ. አብይ መንግሰት መርሳት የሌለበት ጥብቅ ጉዳይ 
የብረታብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን

 ሰሞኑን ጠሚ አብይ በህወሐት የጦር መኮንንኖች የበላይ አዛዥነት በሚንቀሳቀሰው የብረታብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (METEC) ላይ የወሰደው እርምጃ ተገቢና የሚያበረታታ ቢሆንም ከአመራሮች ጋር ጎን ለጎን የሚታይና የጠ.ሚ. አብይ መንግሰት መርሳት የሌለበት አንድ ጥብቅ ጉዳይ መኖሩ ታወቀ፡፡የብረታብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (METEC) የህዝብ ገንዘብ ሲዘረፍ በከፍተኛ ሁኔታ ከዘራፊዎች ጋር ተባብረው ሲዘርፉ የነበሩ የመንግስት የልማት ድርጅቶችን የሚመሩ ሃላፊዎችም አሉበት፡፡

በጣም የሚያሳዝነው በልማት ድርጅቶች ውስጥ እውነትን ይዘው የሚሟገቱ አንዳንድ አመራሮች ተገቢ ያልሆነውን አሰራር ሲቃወሙ ዋናዎቹ አመራሮች የኮርፖሬሽኑን ሀሳብ ካላስፈፀማችሁ እየተባሉ ተባርረዋል። እድገት የተከለከሉ በርካታ ሀቀኛ ኢትዮጵያውያንም አሉ፡፡

መንግሰት ይህን ሁኔታ በጥልቀት አይቶ አድር ባይ አመራሮች አስፈራረተውን ነው ምናምን እያሉ ሀገር የጣለችባቸውን አደራ ወደ ጎን በመተው በክህደትና በአድር ባይነት አብረው ሲዘርፉ የነበሩ አመራሮችም መጠየቅ አለባቸው፡፡ ይህ ካልተደረገ ወደፊት ለሀገሩ የሚሰራ በዲሲፕሊን የታነጸ ሀቀኛ የሰው ሃይል ለማፍራት አስቸጋሪ ይሆናል።

ኮርፖሬሽኑ በርካታ ፕሮጀክቶችን ያለአቅሙ እሰራለሁ እያለ በመዉሰድ በህዝብ ገንዘብ ላይ ከፍተኛ ምዝበራ ከማድረሱም በላይ በሙያቸዉ ብቁ የሆኑትንና ሃቀኛ ሰራተኞችን በማሸማቀቅ ከስራ ዝቅ በማድረግና በማባረር በሰራተኞች ላይ ጭምር ከፍተኛ ጉዳት ሲያደርስ እንደነበር ይታወቃል።