እብደት ወይስ ቅብጠት

እብደት ወይስ ቅብጠት

ቅብጠት ወይስ እብደት
እብደት ወይስ ቅብጠት
እብደት ወይስ ቅብጠት

ሰሞኑን የምንሰማው ነገር ደሞ የሚገርም ብቻ ሳይሆን የሚደንቅ ነው። በብዙ ከፍተኛ ወታደራዊ መኪናዎች የሰፈሩ ወታደሮች ትግራይ ዉስጥ በአካባቢው ህዝብ ከክልሉ እንዳይወጡ ታግተው መቆማቸው የኢትዮጵያን ህዝብ ብቻ ሳይሆን የአለምን ህዝብ ጭምር እያነጋገረ ነው። የአንድ ሃገር ድንበር ጠባቂ የመከላከያ ሃይል ከነሙሉ ትጥቁ ከመንደር በተሰበሰቡ መደዴዎች መታገት በየትም ሃገር የማይታሰብና የማይደረግ ስርአተ አልበኝነት ትግራይ ዉስጥ ተፈጽሞአል። ይህም ድርጊት ህጻን ልጅ ወደ እሚንቦገቦግ የሰደድ እሳት እየዳኸ ሄዶ የመጠጋት ያህል አደገኛና ጠብ ጫሪነትም ነው። በኢትዮጵያ ህዝብ ስምና ገንዘብ ተመስርቶ የወያኔ ተላላኪ በመሆን ፪፯ አመት ሙሉ የነሱን ጥቅምና ዝርፊያ ሲያስከብር የኖረውን ጦር የኢትዮጵያ ህዝ ተናዶ “ሌባ” አላለዉም። በወያኔው መሪ በመለስ ዜናዊ የተቀረጸዉን እርኩስ ጸረ ኢትዮጵያ ሶዶማማ ባንዲራ ተሸክሞ ኩሩ ህዝባችንንና ታሪካችንን ሲያረክስ እንኩዋን ሌባ ብሎ አልሰደበዉም። 

እብደት ወይስ ቅብጠት
እብደት ወይስ ቅብጠት

በትግራይ ስም ተመስርቶ ወኪል (ነጻ አዉጭ) ነኝ የሚለው ወያኔ ከሁሉም በላይ የሆነዉን ስነምግባርንና ስነስርአትን ከህዝቡ አእምሮ ዉስጥ በማጠብ ማን አለብኝነትን ባዶ የዉሸት ኩራትንና እምነተቢስነትን በህዝቡ አእምሮ ውስጥ አስርጎ አስገብቶአል። የትግራይ ህዝብን እንወክላለን የሚሉት ወሮበሎች የክፉ ቀን ወንድሞቻቸዉን የአማራዉን የኦሮሞዉንና የሌሎች ወገኖቻችን ዘር ሲያጠፉ ሲዘርፉ ጥፍር ሲነቅሉ እጅና እግር ሲቆርጡ ዝም ማለታቸውና ማጨብጨባቸው አንሶ ዛሬ ደሞ እነሱን ከሻእቢያ መንጋጋ በደሙና ባጥንቱ ያተረፋቸውን የኢትዮጵያ ጦር እንደ ባእድ ወይም እንደጠላት ጦር እመንገድ ላይ እየተኮለኮሉ ከመዝጋትም አልፈው “ሌባ ሌባ” እያሉ ሲሳደቡ መስማት የቅብጠት ነው ወይስ የእብደት? ወይስ አሁንም በየወታደራዊ እዝ ዉስጥ ያሉትን የነሱን አይነት ምግባረ ብልሹ ለኢትዮጵያ በጎ ነገር የማያስቡትን ወያኔ/ትግሬዎች ከዉስጥ መኖር ተማምነው ይሆን? “የቀበጡ ለት ሞት አይገኝም” አሉ አባቶቻችን!!

ይህን ስርአተ አልበኝነት የጠቅላይ ሚንስቴር አብይ መንግስት እንደቀላል አይቶ ትግራይ ዉስጥ የመሸጉትን ነፍሰገዳዮችና የኢትዮጵያ ጠላቶች እያደነ ለፍርድ ካላቀረባቸው ለሃገራችንም ሆነ ለጠቅላይ ሚንስቴርይ አቢይ ደህንነት በእጅጉ አስጊ ናቸው:: 

ከዚህ በፊት ደብረ ጺዮንና የወያኔ የቦና ግልገሎች በመፈክር ሳይቀር “ከአማራ ሱዳን ይሻለናል” በማለት ከጠላትና ከባርነት ነጻ አዉጥቶ ያልተገዛን ህዝብ ነን እያሉ እንዲኮሩ ያደረጋቸዉን ሰፊዉን የአማራ ህዝብ ብቻ ሳይሆን መላዉን የኢትዮጵያ ህዝብ አስቀይመዋል። ባጎረስኩ እጄን ተነከስኩ!!  ይህ ወጥ ረገጣ ወያኔዎች የተማመኑበትን አንድ ነገር ቁልጭ አድርጎ ያሳያል። ያም በደህንነቱም ሆነ በወታደራዊ እዝ ዉስጥ የተሰገሰጉ ወኪሎቻቸው በድብቅ መኖራቸውን ነው። ወያኔ በተፈጥሮው ኮሳሳና አቅመቢስ ስለሆነ መኖር የሚችለው በጥገኝነት ወይም በቅጥረኝነት ብቻ ነው። ይህንን ጸረ ህዝብና አሸባሪ ድርጅት ከሌሎች ንጹሃን ህዝቦችና የዉጭ አካሎች ጋር ኢትዮጵያን እንዳያነካካ አድርጎ መነጠልና ማሶገድ የጊዜው አንገብጋቢ ተግባር መሆን አለብት። 

በዚህም አላበቃም በቅርብ ጊዜ በመመተማ በኩል በወያኔ ተንኮል የተነሳ ከሁለት አስር አመቶች በላይ ተለያይቶ የኖረው የኢትዮጵያና የኤርትራ ህዝብ ሲገናኝ የመሸባቸው የወያኔ ግልገል የሰፋሪ ልጆች አማራ አጽመ እርስት (ወልቃይት) ላይ በህገውጥ መንገድ ተንደላቀው እየኖሩ አቶ ገዱንና ዶክተር አብይን  “ሌባ ሌባ” በማለት የራሳቸውን ስራ በሌሎች ላይ ለማላከክ ላንቃቸው እስከሚላቀቅ በመጮህ ጸረ እኢትዮጵያዉይነታቸውንና ጸረ አማራ አቁአማቸውን ጥርት ባለ ሁኔታ አሳይተውል።   ያተረፉት ግን ዉርደትንና ትዝብትን ብቻ ነው። ልብ ያለው ልብ ይበል!! ወያኔ እንደ ድርጅት እስካለ ድረስ ኢትዮጵያም ሆነች ባጠቃላይ ምስራቅ አፍሪቃ ሊረጋጋና ሰላም አግኝቶ ወደ እድገት ሊያመራ በፍጹም አይችልም።

ድል ለተበዳዩ መላው የኢትዮጵያ ህዝብ