የሰሜን ሸዋ ህዝብ ጥያቄ

የሰሜን ሸዋ ህዝብ ጥያቄ

መፍትሄ የናፈቀው የደብረ ብርሃን - እነዋሪ መንገድ ዜና ሐተታ (ከጅሩ ልጆች - ፌስቡክ የተገኘ)
የፈራረስው የእነዋሪ መንገድ። የሁለት አሃዝ እድገት መለኪያው ይሆን?

የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ሐብታሙ ተገኝ  የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ምክትል ዳይሬክተር ኢንጅነር መሀመድ አብዱል አማን ከጠቅላይ ቤተክህነት የሀገር ተወላጅ አስተባባሪ አባ ለይኩን አስፋ ወሰን እና ሌሎች ከፍተኛ የመንገድ ባለስልጣኖች በ 7/4/2011 ዓ.ም  በሞረትና ጅሩ ወረዳ ከደብረ ብርሀን ጅሁር ያለው መንገድ እያዩ እነዋሪ ከተማ መግባታቸው ተሰምቶአል።

የሞረትና ጅሩ ህዝብ ለነዚህ አዳዲስ ባለስልጣኖች መንገር ያለበት በጣሊያን ጊዜ የተሰራዉ ከደብረ ብርሃን እስከ ጅሁር ያለው መንገድ እንዲታደስ ብቻ ሳይሆን:-

፩) በእነዋሪ በኩል ዠማን አቁአርጦ (በድልድይ) እስከ አለም ከተማ መንገድ እንዲሰራና ነጋዴዉም ሆነ ገበሬው ተጠቃሚ እንዲሆን።

፪) እስካሁን ድረስ ሞረትን ጂሩን ተጉለትንና መንዝን የሚያገኝ መንገድ ስለሌለ መንገድ እንዲሰራላቸውና እንዲገናኙ

፫) ቆላማውን አካባቢ ማለትም ላምዋሻን ሞረትን እንሳሮንና ሌሎች ያልጠራሁዋቸዉን አካባቢዎች ከእነዋሪ ከተማ ጋር እንዲገናኙ አጠንክሮ መጠየቅ።

፬) ከዚህ በተጨማሪ እጅግ አንገብጋቢ ሆነው መጠየቅ ያለባቸው ሀ) የመብራት ለ) የትምህርትና ሐ) የዉሃ አገልግሎቶች ሲሆኑ ከላይ በተጠቀሱት ቆላማ አካባቢዎች ጭምር እንዲሰራ አክርሮ መጠየቅና የህዝቡን እስካሁን ድረስ ግብር እየከፈለ መበደሉን ማስረዳት ያስፈልጋል።

ከቆላ ወደ ደጋ የሚደረግ የእግር ጉዞ
የጅሩ መለሎ ስንዴ

ካሁን በሁዋላ የሞረትና ጅሩም ሆነ ሌላው የሰሜን ሸዋ ህዝብ ግብር እየገፈገፈና ኢትዮጵያ ስትጠቃ ቀድሞ መስዋእት እየሆነ ተረስቶ መኖር የለበትም። ከላይ የጠቀስኩዋቸው በሌሎች አካባቢዎች እንደተገነቡት በቢሊዮን ብር የሚጠይቁ  ከባድ ኢንዱትሪ ስላልሆኑ እንዲሰሩም መጠየቅ አልነበረብንም:: ወረዳን ከወርዳ የማገናኘቱ (Basic infrastructure) ስራ ከዛሬ 27 አመት በፊት መፈጸም ሲኖርበት ይባስ ተብሎ ዛሬ ጣሊያን የሰራው መንገድ እንኩዋን ተበላሽቶ ይገኛል።  ስለሆነም ህዝቡ ባለስልጣኖቹን እስከመቼ ድረስ እንደሚሰሩ መጠየቅና ማስታወሻ መያዝ አለበት። ይህንን በጣም ቀላል የሆነ እንደ ህዝብ የሚገባዉን ቀላል አገልግሎት መገንባት ካልቻሉ በሚቀጥለው አመት ዉስጥ የአካባቢው ህዝብ ተሰብስቦ አማራጭ እርምጃዎችን መዉሰድ አለብት።

ጠ.ሚ. አብይ ም.ጠ.ሚ ደመቀና አቶ ለማ ከጅሩ ዝብ ጋር
የሰሜን ሸዋ ህዝብ ጥያቄ
የጅሩ መረሬ ሽብራ እሸት

በነገራችን ላይ ከጅሩ (እነዋሪ) እስከ አለም ከተማ ያለው እርቀት አጭር ስለሆነ ወደ ወሎና ወደ ጎጃም ብሎም ወደ ጎንደር ለመሄድ አቁአራጭ መንገድ በመሆኑ በክልሉ ዉስጥ የሚገኙትን አራቱን የአማራ ዞኖች በቀላሉ ለማገናኘትና አካባቢው ዉስጥ ወደ ፊት የልማት ስራዎችን ለማካሄድ ከፍተና መሰረት ከመጣሉም በላይ ዜጎች ከተጉለትና ከጅሩ ወደ መርሃቤተ ዘመድ ለመጠየቅም ሆነ ለለቅሶ ሲሄዱ በዠማ ወንዝ እየተወሰዱ ህይወታቸው እንዳይጠፋ ይረዳል። ከዚህ በፊት ጠቅላይ ሚንስቴር አብይም ሄደው የህዝቡን ሁኔታ አይተው ስለተመልሱ የአሁኑ የስራ ግብኝት ተግባራዊ እንደሚሆን ተስፋ እናደርጋለን። እባካችሁ ህዝቡን በድጋሜ አታሳዝኑት!!