የጸረ ኢትዮጵያዉያንና የጸረ አፍሪካዉያን የጥቃት ኢላማ የሆነችዉ የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ 

የጸረ ኢትዮጵያዉያንና የጸረ አፍሪካዉያን የጥቃት ኢላማ የሆነችዉ የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ 

የጸረ ኢትዮጵያዉያንና የጸረ አፍሪካዉያን የጥቃት ኢላማ የሆነችዉ የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ 
የኢትዮጵያ

አንዳንድ ሰዎች የኢትዮጵያን ሰንደቅ አላማ ጉይ እንደቀላል ነገር ሊቆጥሩት ይችሉ ይሆናል። እዉነታው ግን ሰንደቅ አላማችን የኢትዮጵያዉያን አንድነት ብቻ ሳይሆን ክብርና ሉአላዊነታችንን ያዘለች ነች። ኢትዮጵያዉያን ሁላችንም ልብ ብለን ማየት ያለብን ሃገራችንን ለመበተንና የአንድነት ታሪካችንንና ክብራችንን ገፎ ለማዋረድ የዉስጥም ሆኑ የዉጭ አስመሳይ የዲሞክራሲ ታጋዮች ያለ ህዝቡ ፍላጎትና እዉቅና የሚከተሉትን ህገወጥና ከፋፋይ ተንኮሎችን በማጠንጠን ላይ መሆናቸውን ነው። ይህንን ጸረ አንድነትና ጸረ ሰላም ደባቸውን እዉን ለማድረግ በሚከተሉት የሃገራችን እሴቶች ማንነቶችና መገለጫዎች ላይ አሁንም በጠ/ሚ አቢይ አህመድ ጊዜ ከፍተኛ የጥፋት ዘመቻ በመካሄድ ላይ ነው።

፩. ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለአፍሪካና ለመላው ጭቁን ህዝብ ባለዉለታ የሆኑ ሰዎችንና አንጸባራቂ ታሪካችንን ከቅኝ ገዝዎች ጋር በማበር ማንኩዋሰስና ስማቸዉን ማጥፋት። ለምሳሌ አጼ ምኒልክንና ጎበናን።

፪. አወዛጋቢና ጥቅም የሌለው የክልል ካርታ በመስራት በዚያ የተነሳ የኢትዮጵያ ህዝብ እርስ በርሱ እድሜ ልኩን እየተራረደና እየደኸዬ የባእዳን ጥገኛና ባሪያ ሆኖ ሃብቱን እየተዘረፈ እንዲኖር ማመቻቸት

፫. የተለያየ ቀለም ያለዉን ጨርቅ በመስፋትና ብሄር ብሄረሰብ በማለት ቡድን ለይቶ የጎሪጥ እንዲተያይና የአንድ እግር ኩዋስ ቡድን ያህል እንኩዋን የአንድነት አላማ እንድይኖረው ማድረግ። ይህ ማለት የኢትዮጵያ ህዝብ እንደ ነጻ ሳይሆን እራሱን እንደ አዲስ ከባርነት እንደወጡ ሃገሮች አይቶ ማንነቱን ክብሩንና ታሪኩን አዉልቆ እንዲጥልና እንዲዋረድ ማድረግ። ይህም የኢትዮጵያ ህዝብ በባእዳን አልተገዛንም ነጻ ህዝብ ነን እንዳይል የሞተላትንና የክብሩ ምስክር የሆነችዉን ሰንደቅ አላማዉን በማስጣል የተገዥነትና የበታችነት አስተሳሰብን ያለጦርነት እንዲቀበል ለማድረግ ነው።

ይህን ከህዝባችን ፍላጎት ዉጭ በጥቂት ዘረኞችና ኢትዮጵያን በሚጠሉ ፋናቲኮች የሚካሄደውን አደገኛ አፍራሽ አካሄድ በተለይ እዉነተኛ የኦሮሞ ወንድሞቻችን ማክሸፍና ክብራቸውን መጠበቅ አለባቸው። የኢትዮጵያ ህዝብ ከኮንሶ እስከ አርባ ምንጭና ወላይታ ሶዶ ; ከከምባታና ሃድያ እስከ ጉራጌየ; ከናዝሬት እስከ አዲስ አበባና ደብረ ብርሃን; ከመላው ወሎ እስከ መላው ሸዋ;  ከመላው ጎንደር እስከ መላው ጎጃም ከመላው አፋር እስከ ድሬዳዋ የማነቱ መገለጫና የአንድነትና የነጻነት ምልክቱዋን ሰንደቅ አላማዉን እዉቅና መስጠቱን በሚያስደንቅ ሁኔታ ገልጾአል።

እስካሁን ድረስ ይህንን ሃቅ በማየት ጠ/ሚ አብይ እዉቅናዉን ተቀብለው ስራ ላይ ማዋልና ህዝቡ በአንድ አላማ በአንድ በሚያዉቃት ሰንደቅ አላማ ስር እንዲሰባሰብ ከማድረግ ይልቅ የተምታታና ብዥታን የሚፈጥር እንዲያዉም ሰንደቅ አላማችንን የሚጋፋ አይነት መግለጫ መስጠታቸው የነበረንን ተስፋ የሚያዳፍንና ሃገራችንን ለከፍተኛ አደጋ ሊያጋልጥ የሚችል የታላቁ ሴራ አካል ነው ለማለትየሚያስደፍር ጊዜ ላይ ደርሰናል:: አሁን በኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ ላይ የተከፈተው ጥቃት ወሳኝ ስለሆነ የኢትዮጵያ ህዝብ በምንም አይነት የማያዉቀዉን ባእድ አካል አሽቀንጥሮ በመጣል ክብሩን አንድነቱን ሰላሙንና ነጻነቱን መጠበቅ አለበት።

ድል ለተበዳዩና ለነጻነት ወዳዱ የኢትዮጵያ ህዝብ