ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ

ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ

††እንኩዋን ለቅድስት ክርስቶስ ሠምራ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ። ††
ኢትዮጵያዊቷ ጻድቅ ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ በሸዋ ክፍለ ሀገር በቡልጋ አውራጃ ልዩ ስሟ ቅዱስ ጌየ በተባለች ሀገር እግዚአብሔርን ከሚፈሩ ደጋግ ሰዎች በግንቦት 12 ቀን ተወለደች፡፡ የአባቷ ስም ቅዱስ ደረሳኒ የእናቷም ስም ቅድስት ዕሌኒ ይባላል፡፡አኒህም ሰዎች ቅድስት ክርስቶስ ሠምራን ከወለዱ በኋላ በደም ግባቷና በጠባይዋ እየተደሰቱ የእግዚአብሔርን ሕግጋትና ሥርዓተ ቤተክርስቲያንን በማስተማር አሳደጓት፡፡

ባደገችና ለአቅመ ሔዋን በደረሰች ጊዜ የንጉሥ ባለሟል ለሆነ ስሙ ሠምረ ጊዮርጊስ ለተባለ ሰው በ ሕግ አጋቧት፡፡ከዚህ በኋላ ከሕግ ባሏ ከሠምረ ጊዮርጊስ አስራ አንድ ልጆችን ወለደች ከእነዚህም መካከል ዘጠኙ ወንዶች ሁለቱ ሴቶች ነበሩ፡፡ በዚያ ዘመን የነበረው ንጉሥ ገብረመስቀል በጸሎትሽ አስቢኝ በማለት 174 አገልጋዮች፣ብዙ ፈረስና በቅሎ እንዲሁም ለነገሥታት ሚስቶች የሚገባ ከሐርና ከወርቅ የተሠራ ልብስና የወርቅ ጫማ ላከላት፡፡ነገር ግን እሷ ይህን ሁሉ ክብር አልፈለገችም ይልቁንም ለዓላማዬ እንቅፋት ወይም ውዳሴ ከንቱ ይሆንብኛል እንደዚሁም ወርቁ ጌጡ ተሸጦ ለነዳያን ይመጸወታል ነገር ግን እነዚህን አገልጋዮች ምን አደርጋቸዋለው እያለች ወደ እግዚአብሔር አመለከተች፡፡

ከጥቂት ቀናት በኋላ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ፊቱ እንደ ፀሐይ እያበራ ሦስት ኅብስት በእጁ ይዞ የእግዚአብሔር ባለሟል ክርስቶስ ሠምራ ሆይ እነሆ ይህን ኅብስት ተመገቢ እግዚአብሔር በቸርነቱ ብዛት ሰጥቶሻል አላት፡፡እሷም ፈጣሪዋን አመስግና ኅብስቱን ከመልአኩ እጅ ተቀብላ ተመገበች መዓዛ ጣዕሙም ሰውነቷን አለመለመው፡፡በዚህም የተነሳ እስከ ሦስት ቀን እህል ሳትበላ ውኃ ሳትጠጣ ቆየች ኃይለ መንፈስ ቅዱስ በሰውነቷ አድሮባታልና፡፡

ከዕለታት አንድ ቀን እንዲህ ሆነ፣ከአገልጋዮቿ መካከል አንዷ ምግባሯ የከፋ ነበርና በጣም ስላበሳጨቻት በዚያች አገልጋይ አፍ ውስጥ የእሳት ትንታግ ጨመረችባት ያም የእሳት ትንታግ እስከ ጉሮሮዋ ዘለቀና አገልጋይዋን ገደላት፡፡ በዚህ ጊዜ ብጽዕት ክርስቶስ ሠምራ ደንግጣ ወደ ሌላ ክፍል ገባችና ኃጢአቷን ለእግዚአብሔር እየተናዘዘች እጅግ በጣም አዝና ጥፋቷ እንደ ጸጸታትና እግዚአብሔር አምላክም በእጇ የሞተችውን አገልጋይዋን ከሥጋዋ አዋህዶ ቢያስነሳላት ያላትን ገንዘብና ሀብት ትታ ባላት ዘመኗ ሁሉ አገልጋዩ እንደምትሆን ብጽዓት /ስዕለት/ አደረገች ፡፡ እግዚአብሔርም ጸሎቷን ሰምቶ አገልጋይዋን አስነሳለት ፡፡ እሷም ”ልመናዬን ቸል ያላለ ቸርነቱንም ከእኔ ከባሪያው ያላራቀ አምላክ ይክበር ይመስገን ብላ በታላቅ ምስጋና እግዚአብሔርን አመሰገነች ፡፡ ከዚህ በኋላ እናታችን ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ አስቀድማ የገባችውን ቃል አስባ ልብሰ ምንኩስናዋን አዘጋጀች፡፡ ከዛም አገልጋዮቿን ጠርታ ወደ ቤተክርስቲያን እንሄድ ዘንድ ተዘጋጁ አለቻቸውና አብረዋት ሄዱ፡፡

ከዚያም እንደ ደረሱ አንድ አገልጋይዋንና ሕፃን ልጅዋን አስቀርታ ሌሎቹን ወደ ቤት መለሰቻቸውና የሚያልፈውን ዓለም በማያልፈው ዓለም ለመተካት ጉዞዋን ጀመረች፡፡

ጉዞ ወደ ደብረ ሊባኖስ
ያ በልስላሴና በእንክብካቤ የኖረ እግር ከመንገዱ ብዛት እንደዚሁም ከእንቅፋቱ የተነሳ ፈለግ ሲያወጣ ሥጋውን እየቆረጠች ስትጥለው ደሙ እንደ ጎርፍ ውኃ ይወርድ ነበር፡፡በዚህ ዓይነት ችግርና የፀሐይ ሀሩር ከአሰበችው ከደብረ ሊባኖስ ገዳም ደረሰች በዚያም አስቀድማ ያዘጋጀችውን ልብሰ ምንኩስናዋን ለብሳ ከሴቶች ገዳም ገባች፡፡ይዛው የተሰደደችውን ሕፃን ግን ወንድ ስለሆነ ከደጅ ላይ አስቀምጣው ገባች ሕፃኑ ግን ምርር ብሎ ያለቅስ ነበር ምክንያቱም ከእናቱ ከመለየቱ በተጨማሪ ጊዜው ጨልሞ ነበር፡፡ከመነኮሳቱ አንዲቷ ሕፃኑ ሲያለቅስ ከሚያድር ብላ ወደ በአቷ ልታስገባው ስትል የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ነጥቆ ወስዶ ሄሮድስ ካስፈጃቸው ሕፃናት ጋር በገነት አስቀመጠው፡፡ታኅሳስ 29 ቀን ተወልዶ በ 3 ዓመቱ ታኅሳስ 12 ቀን ብሔረ ብጹአን ገባ፡፡

የምንኩስና ሕይወት
ከዕለታት በአንደኛው ቀን እናታችን ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ ቆማ ስትጸልይ ቅዱስ ሚካኤል መጥቶ በክንፉ ተሸክሞ ከጣና ደሴት አደረሳት፡፡ ከዚያም ሰውነቷ ተበሳስቶ የባህር ዓሳሣ መመላለሻ እስከሚሆን ድረስ እንደ ተተከለ ዓምድ ሆና ሳትወጣ በባህሩ ውስጥ ዓስራ ሁለት ዓመት ቆማ ስትጸልይ ኖራለች፡፡ከዕለታት አንድ ቀን በጣና ማዶ መዕቀበ እግዚእ የሚባል አንድ ሰው ነበረና መልአከ ጽልመት ወደ እሱ ዘንድ መጥተው ፈጣሪውን ክደህ ይህን ዕፅ በሰውነትህ ብትቀብር ሞትና እርጅና አያገኝህም አለው፡፡እሱም እሽታውን ስለገለፀ መልአከ ጽልመት በሰውነቱ ዕፁን ቀብሮለት ሄደ፡፡ዳግመኛም ከዕለታት አንድ ቀን ወደ ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ ዘንድ መጥቶ “ሰላም እልሻለው በጸሎትሽም ተማጽኛለሁ የፈጠረኝን እግዚአብሔርን እስከ መካድ ደርሼ ብዙ ኃጢአት ሰርቻለውና”አላት፡፡በዚያን ጊዜ ፈጥና ተነስታ ወደ ቤተክርስቲያን ሄደችና ስለዚህ ሰው በፍጹም ኀዘን በ መሆን ወደ ፈጣሪዋ አመለከተች፡፡

በዚህ ጊዜ ጌታችን መጥቶ ወዳጄ ክርስቶስ ሠምራ ሆይ ለእዚህ ሰው ምህረት አይገባውም የምገድል የማድን የምቀስፍ ይቅር የምል አምላክ እኔ እያለሁ ፈጣሪውን ክዶ በሰይጣን ምክር ተማምኖአልና አላት፡፡ በዚህ ጊዜ እናታችን ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ በእግሩ ስር ተደፍታ አንተ መዓትህ የራቀ ምህረትህ የበዛ ፈጣሪ ሆይ ማርልኝ ሁሉ ይቻልሃልና ስትል አጥብቃ ለመነችው፡፡ሁሉን የፈጠረ ጌታም እለ አንቺ ፍቅር ምሬልሻለው አላት፡፡ከዚህ በኋላ ማእቀበ እግዚእን ጠርታ ኃጢአትህን ይቅር ብሎሃል አለችው፡፡ከዚህ በኋላ ከራስ ጸጉሩ እስከ እግር ጥፍሩ የተቀበረውን ዕፅ ሰውነቱን ፍቃ ስታወጣለት ደሙ እንደ ቦይ ውኃ ወረደ በዚያው ነፍሱ ከሥጋው ተለይታ ከማኅበረ ሰማዕታት ጋር አንድ ሆነች፡፡ከዚህ በኋላ ለቅድስት ክርስቶስ ሠምራ እግዚአብሔር አምላካችን ስድስት ክንፎች በሰውነቷ ላይ ማለትም ሦስቱ በቀኝ ጎኗ ሦስቱ በግራ ጎኗ በቀሉ በዚህም እግዚብሔርን ፈጽሞ አመሰገነች፡፡ 

እግዚአብሔርም ጸሎቷን ሰምቶ አገልጋይዋን አስነሳለት ፡፡ እሷም ”ልመናዬን ቸል ያላለ ቸርነቱንም ከእኔ ከባሪያው ያላራቀ አምላክ ይክበር ይመስገን ብላ በታላቅ ምስጋና እግዚአብሔርን አመሰገነች ፡፡ከዚህ በኋላ እናታችን ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ አስቀድማ የገባችውን ቃል አስባ ልብሰ ምንኩስናዋን አዘጋጀች፡፡ ከዛም አገልጋዮቿን ጠርታ ወደ ቤተክርስቲያን እንሄድ ዘንድ ተዘጋጁ አለቻቸውና አብረዋት ሄዱ፡፡ ከዚያም እንደ ደረሱ አንድ አገልጋይዋንና ሕፃን ልጅዋን አስቀርታ ሌሎቹን ወደ ቤት መለሰቻቸውና የሚያልፈውን ዓለም በማያልፈው ዓለም ለመተካት ጉዞዋን ጀመረች፡፡ ታመጣው ዘንድ ወደ ሲኦል ይዘሃት ሂድ አለው፡፡

እዛ እንደ ደረሰች ለዲያቢሎስ ልተስታርቀው እንደመጣች ነገረችው እሱ ግን ጭራሽ አጁዋን ይዞ ወደ ሲኦል ወረወራት በዚህ ጊዜ ቅዱስ ሚካኤል በያዘው ሰይፍ አስጣላትና በቅዱስ ሚካኤል ክንፍና ለእሷም በተሰጣት ክንፈ ረድኤት ከሲኦል ዓስር ሺህ የሚያክሉ ነፍሳት ይዘው ወጡ፡፡ከዚህ በኋላ ወደ ፈጣሪዋ ሄዳ አቤቱ ፍርድህ የቀና ምህረትህ የበዛ ነው እያለች ለጌትነቱ ክብር ሰገደች፡፡ከዚህ በኋላ እናታችን ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ በቁመቷ ልክ ጉድጟድ አስቆፈረችና ሦስት የተሳሉ ጦሮች በፊቷ፣ሦስት ጦር በኋላዋ ፣ ሦስት ጦር በቀኝ ጎኗ፣ሦስት ጦር በግራ ጎኗ ተከለች፡፡አንዲት መበለትም ጠርታ የፊጥኝ ወይም የኋሊት በገመድ እንድታስራት አደረገች፡፡

ከዚህ በኋላ ስለ ዓለም ሁሉ ትጸልይ ጀመር፡፡በምትሰግድበትም ጊዜ ጦሩ እየወጋት ከቁስሉ የተነሳ ጦሩ የወጋት ገመዱ የከረከራት መላ ሰውነቷ ሸቶ ተልቶ ለዓሥራ ሁለት ዓመት ተጋድሎ አደረገች፡፡ ዜና ዕረፍቷ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምንና ሌሎች ቅዱሳንን ሁሉ አስከትሎ ወደ እናታችን ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ ዘንድ መጣ፡፡ አንዲህም አላት ወዳጄ ክርስቶስ ሠምራ ሆይ ዛሬ ከዚህ ከሚያልፈው ዓለም ወደ ማያልፈው ዓለም አሳርፍሽ ዘንድ መጥቻለው አላትለ፡፡ድካምሽ ወደ ዕረፍት ፣ኀዘንሽም ወደ ደስታ ችግርሽም ወደ ብልጽግና ተለውጦልሻል አላት፡፡በዚህ ጊዜ አቤቱ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ እኔ ባሪያህ በፊትህ ባለሟልነትን አግኝቼ እንደሆን አንድ ነገር እንድናገር ፍቀድልኝ አለችው፡፡እሱም ትናገሪ ዘንድ ፈቅጄልሻለው አላት፡፡አቤቱ ሥጋዬ የሚቀበርበት ቦታ ወዴት እንዲሆን ታዛለህ አለችው፡፡መቃብርሽ በዚህች ንጉል በምትባል ደሴት ይሆናል አላት፡፡ ከዚህም አምላካዊ ል በኋላ በነሐሴ 24 ቀን የአባታችን የአቡነ ተክለሃይማኖት መታሰቢያ በዓል በሚከበርበት ዕለት ነፍስዋ ከሥጋዋ በክብር ተለየች፡፡

በዚህ ጊዜ ቅዱሳን መላእክት በዝማሬና በእልልታ ቅድስት ነፍሷን አሳረጟት፡፡እናታችን ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ ከዚህ ዓለም በሕይወተ ሥጋ የኖረችው ሦስት መቶ ሰባ አምስት ዓመት ነው፡፡

የተሰጣት ቃልኪዳን
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለእናታችን ለቅድስት ክርስቶስ ሠምራ የገባላት ቃልኪዳን የሚከተሉት ናቸው፡፡እውነት እውነት እልሻለው በፍጹም ደስታ መታሰቢያሽን ያደረገ በመንግሥተ ሰማያት አስደስተዋለው፡፡በችግሩ ወይም በጭንቁ ጊዜ በመታመን።