በአማራና በኦሮሞ ልዩነት ላይ እንጀራዉን ሲጋግር የነበረው ወያኔ ሲገሰጥ ቆሌው ተገፈፈ!

በአማራና በኦሮሞ ልዩነት ላይ እንጀራዉን ሲጋግር የነበረው ወያኔ ሲገሰጥ ቆሌው ተገፈፈ!

ኢትዮጵያዉያን ክብራችንን እንደ አባቶቻችን በደማችን አስመለስን። አሸናፊዋ ሰንደቅ አላማችን ለሶስተኛ ጊዜ ጠላቶቹዋን አሸንፋ በክብር ተዉለበለበችበባእዳን ግፊትና እርዳታ ኢትዮጵያን ብቻ ሳይሆን አፍሪካን ጭምር እንዲያተራምስ የተፈጠረው የወሮበላው ወያኔ ቡድን ሰሞኑን አንድ እጡን ዱብ ያደረገ ክስተት ተፈጠረ። እድሜና ጤና ለሃገር ወዳድ ኢትዮጵያዉያን! ወያኔ ከመደንበርም አልፎ ልቡን ነስቶታል። ለመሆኑ ያች እጹን ያስጣለችው ሚስጥር ምንድናት? አባቶቻችን “ስነልቦና” ሲሏት ዘመኑ ተመራማሪዎች ደሞ “Physcology” ይሉታል:: ይህ የጥፋትና የልዩነት ኣስተሳሰብን መፍጠርና ህብረተሰብን በማዋረድ እንዴት ባለመተማመንና በልዩነት ወጥመድ ዉስጥ አስብገብተው እየዘረፉና እያሰቃዩ መግዛት እንዲችሉ የዘረጉት ወጥመድ ነበር:: የነዚህ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ የተጫኑ ጸረ ህዝብ የልዩነትና ያለመተማመን ዋና ዋና መገለጫዎቹ የሚከተሉት ናቸው::

  1. ህብረተሰብን በዘር በቁዋንቁዋና በሃይማኖት ማደራጀት
  2. ጸብ የሚያስነሳ ክልል  ደም የሚያፋስስ የዉሸት ድንበር  (Arificial Border) መፍጠር
  3. የተለያዩ የዉሸት ሰንደቅ አላማዎችን ማሰፋትና ለነገዶች በማከፋፈል የአንድነት ምልክት (common icon) እንድይኖራቸው መበተን
  4. ታሪክንና ሌሎች ዋጋ ያላቸዉን የአንድነት እሴትንና ማንነት ማጥፋት ወይም በማስጣል ትንሽ አድርጎና አዋርዶ መግዛት ናቸው።

በነገራችን ላይ እነዚህ ሁሉ በኮሎኒሊስቶች የተሞከሩና ከህንድና ከቻይና በስተቀር ብዙ ሃገሮችን ያስጎበደዱና ማንነታቸውን ጥለው እንዲዋረድ ያደርጉ ናቸው። ወደ ዋናው እጥ ኣስጣይ ሚስጥር እንመለስና ወያኔ እንዴት የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ ከፍ ብሎ ሲዉለበለብና የሱ ድሪቷምና መተታም የባንዳ ባንዲራ ተሽቀንጥሮ ሲጣል እንዲህ እጡ ዱብ ብሎ ብርክ ያዘው? ከሁሉም በላይ ወያኔን እጡን ያስጣለውና የቆጠቆጠው ይህ ሰሞኑን አዲስ አበባና ባህርዳር ላይ ከልቡ ዉጥ ደብቁዋት የነበረችዉን የነጻነትና የክብሩ ምልክት የሆነችዉን ህጋዊዋንና ታሪካዊዋን የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ ህዝቡ የኔ ናት ብሎ ከዳር እስከዳር ይዞ መዉጣቱ ብቻ ሳይሆን ለሰንደቅ አላማችን ያለዉን ፍቅር እስከ ግማሽ ኪሎሜትር አሰርቶ ከተማዉና አየሩን ሁሉ በኢትዮጵያዊነትና በአንድነት ስሜት መንፈስ በመሙላቱ ነው።

የወያኔ ሸፍጥና ሙዋርት ዋና መቋጠሪያው ያ የሰይጣን ምልክት ያልበት የባንዶች ጨርቅ መሆኑ ታወቀ!! አክራሪ ወያኔዎችና ጀሌዎች እንዲሁም ተቃዋሚ መስለው ያደፈጡ እንደ እነ አብርሃ ደስታ ጭምር አማራ እና ኦሮሞ እንዲጣሉ ብዙ የፕሮፖጋንዳ ስራዎች እየሰሩ ሳያፍሩ እንደጨረባ በመጮህ መርዛቸዉን እባዶ ቦታ ላይ በመርጨት ላይ ናቸው። የኦሮሞ ወጣቶች ደሞ አንጀታቸዉን የሚበጥስ መልስ ሰጥተዋቸዋል። ዐማራና ኦሮሞ እንዳትዘናጉ:: እወቁበት!! ሃገሩም ሆነ ድሉ የናንተ ነው!!