“ዓማራ የለም” እያልክ ለምታላዝንና እራስህን ለምታታልል አናሳ አስተሳሰብ ላለህ ሁሉ!

“ዓማራ የለም” እያልክ ለምታላዝንና እራስህን ለምታታልል አናሳ አስተሳሰብ ላለህ ሁሉ!

 

ዓማራ “የለም” እያልክ ለምታላዝንና እራስህን ለምታታልል አናሳ አስተሳሰብ ላለህ ሁሉ!
ጥንታዊዉ የአማራ የስልጣኔ ፈለግ

የማንንም ወንጀልና ትንሽነት ለመሸፈን ሲባል ዓማራ በዓማራነቱ ከመደራጀትና ወንጀለኞችን ለፍርድ ከማቅረብ የሚያስቆመው ምንም ምድራዊ ሃይል የለም። ተስፋ ቁረጡ። እንዲያዉም ዓማራዉን ይበልጥ በራሱ ማንነት እንዲደራጅ ያደርገዋል። አማሮች ሲተርቱ “የደንቆሮ ለቅሶ መልሶ መልሶ ይላሉ”። አሁንም ያንኑ ያረጀና ያፈጀ ጸረ አማራና ጸረ ኢትዮጵያ ድርሰታቸዉን ከአንድ አናሳ ብሄር የተዉጣጡ እስስቶች “ዓማራ የለም” በማለት ሽምጥጥ አርገው ክደው በመጻፍ ላይ ናቸው።

ከዚያም ኣልፎ የአማራዉን ታሪክ አንደቅራቅንቦ ዓማርኛ እንኩዋን መናገር ለማይችሉ ነገዶች ሊመጸዉቱና ሊያሸክሙአቸው እየባተሉ ነው። የተማረ ዜጋ ስለፍትህ ስለ እኩልነትና ስለ ደሞክራሲይ ይጽፋል። የኛ አናሶች የአማራን ታሪክ ቀደው መጣል ስላልቻሉ ለዓገው ሊያሽክሙት ጎንበስ ቀና አያሉ ነው። ወንድም ባትሆኑ ያገሬ ልጆች! ሌላው ቀርቶ አማሮችን በመልካቸው ትለዩአቸው የለምን?

ለምሆኑ እነዚህ አማራ “የለም” እያሉ በራሱ በአማራው ቁዋንቁዋ የሚጽፉና ሌሎች ተደራጅተው ዓማራውን እየገደሉ እያዋረዱ እንዲኖሩ የሚፈልጉ እነማን ናቸው? ይህንን በምርምርና በትንተና በመታገዝ መጠቆም አለብን።

፩. በትንሽነትና በበታችነት የአእምሮ ጉዳት የደረሰባቸው (በራሳቸው ነገድ የሚያፍሩ)

፪. ሆን ብለው የትዮጵያ ህዝብ ደህንነቱ እንዲናጋና ሰላም አጥቶ አርስ በርሱ ሲጋደል እነርሱ ለዘመናት የቋመጡለትን ሃብቱን በጸራራ ጸሃይ ለማዘረፍ የተቀጠሩ በአብዣኛው ከአናሳ ብሄረሰቦች ተመልምለው በባእዳን ስር የሚሰሩ ቅጥረኞች ናቸው።

፫.የወያኔ የሻቢያው ተስፋዬ ገብረእብና የነሱ ተላላኪው ኦነግም አንዳንድ ጊዜ በድብቅ አንዳንድ ጊዜ ደግሞ በግልጽ ይህንን ከታሪክ ዉጭ የሆነ ዉሸት ህዝብን ለማተራመስ ያራግባሉ።

እስካሁን ድረስ የአማራን ማንነት ለመጋፋት የሚጽፉና ተጨባጭ ታሪኮችን ለመካድ የሚውተረተሩ ባብዣኛው ስሜታቸዉን ለማስታገስ ትልቁን ዓማራ “የለም” በማለት ትልቅ ለመሆን ያለ አቅማቸው የሚንጠራሩ የትንሽነት ወይም የበታችነት ተጠቂዎች ናቸው።  የዓማራው ታሪክ በመላው ኣለም የሚታውቅና በጽሁፍ የተቀመጠ (Documented) ነው።

ፕሮፌሰር ሪቻርድ ፓንክረስትም ታሪክዊ ዓማራ የዛሬዉን አዲስ አበባ ብቻ ሳይሆን የትናንቱን አክሱምና የመጀመሪያዉን የሰለጠነ የሰው ልጅ አስተዳደር ዘ ዳአማትን የመሰረተ መሆኑን በግልጽ ጽፈዋል። የተወደዳችሁ አንባብያን ታዋቂዉ የታሪክ ተመራማሪ በፕሮፌሰር ሪቻርድ ፓንክህረስት ስለ ዓማራ የጻፉትን ከታች ያለዉን መገናኛ በመጠቀም እንድታነቡና እዉነቱን እንድትረዱ እናሳስባለን።

ይህንን የበታችነት ስሜታቸዉን የ1966 አቢዮትም ሊያጥብላቸው አልቻለም። በደርግ ጊዜ ዓማራን ነፍጠኛ ትምክህተኛና የመሬት ከበርቴ እያሉ የፈጸሙትን ግፍ ዓማሮች ለሃገራቸዉ ለኢትዮጵያ ህዝብ ደህንነትና ጥቅም ሲሉ ሊያሳልፉት ቢሞክሩም የተረሳ መስሎአቸው ወይስ ወንጀላቸዉን ዓማራው እንዳያነሳ “የለም” በማለት እናዘናጋው ብለው ነው?  አንዴ ከወያኔ ጋር ሌላ ጊዜ ደሞ ከተቃዋሚ ጋር እንደእስስት በመለዋወጥ በሁሉም አቅጣጫ ሰው ሲገሉና መርዛቸዉን በመጻፍ ጭምር ሲረጩ የነበሩ ወንጀለኞች ሁሉ ዓማራ ዝም ስላለ “የለም” እስከማለትና የሰዉን ዘር እስከመካድ ደርሰዋል። ይኸ ደሞ ዉሎ አድሮ እንደሚያስጠይቅ ቢያስፈራቸውም ቢያዉቁት ጥሩ ነው!!!!!

“አሳ ጎርጉዋሪ ዘንዶ ያወጣል የሰው ፈላጊ የራሱን ያጣል”። ዛሬም በወያኔ ዘመን የሚሰቃዩ አናሳ ብሄረሰብ ተብለው በዞንና በክልል አጥር እንደፍየል ታስረው መሬት ጠቦአቸው እያለ አማራ ባሰፋው መሬት ላይ ሰፍረው ተጨባጭ የተጻፉ ታሪኮችን መካዳቸው ወዴት የሚወስዳቸው ይመስላችሁዋል?  ባለቤቱ ዓማራ ተቀምጦ የራሱን ታሪክ እንኩዋን የማያዉቅ ወይም የሚደብቅ ሰው ስለ አማራም ሆነ ስለ ሌላው ህዝብ ማዉራት ይችላልን?

የራሳችሁን ታሪክ እየጠየቃችሁ ወይም የዉጭ ጸሃፊዎችን ስለምታመልኩ የነሱን ጽሁፍ እያነበባችሁ አቅሙ ካላች ብትጽፉ ጥሩ ነው። የአማራ ታሪክ በራሱ በአማራው ገድልና በመጽሃፍ ቅዱስ ላይ ከክርስቶስ ልደት በፊት ጀምሮ በዓማሮች አባት በኢትኤል (ኢትዮፕ) ሳይቀር የተጻፈ ነው:: የአማራ ታሪክ በአርኪኦሎጅ እንደሉሲ ተቆፍሮ ወይም በአፈታሪክ መንደር ለመንደር እየተዞረ በስማ በለው ተጠይቆ በግምት የተጻፈ አይደለም።

“ኢትዮጵያ የለችም” በማለት 26 አመት ከዘባረቁ በሁላም ኢትዮጵያንና አማራዉን ማጥፋት ስላልቻሉ አሁን ደግም ዘዴአቸዉን ለወጥ አድርገው “ዓማራ የለም” በማለት በእንዳሻው መዘባረቃቸዉን ቀጥለዉበታል። በመጨረሻም አማራው በእነሱ ትንኮሳ የተነሳ እንዴት እንደሚጠናከርና እነሱ ደግሞ ከአላዋቂ አስተማሪያቸው ከላጲሶ ጋር እንዴት እያነሱ እንድሚሄዱ እናያለን።

ድል ለተበዳዩ የኢትዮጵያ ህዝብ

ዉርደት ለዘረኞችና ቅጥረኛ የታሪክ ቀበኞቸ 

 

ፕሮፌሰር ሪቻርድ ፓንክረስት ስለጥንታዊው የዓማራ ስልጣኔ ባለቤትነት

Belachew Tintagu

Belachewtintagu@yahoo.com

ስለ ታላቁ የኢትዮጵያ የታሪክ ተመራማሪ ስለ ፕሮፈሰር ሪቻርድ ባንክረስት ለማንበብ ከታች ያለዉን መገናኛ ይጠቁሙ

http://www.raceandhistory.com/Historians/pankhurst.htm