፩፩ ደለዊ ነፋስ (በሬ)

፩፩ ደለዊ ነፋስ (በሬ)

ይህ ኮከብ በጥር 12 ቀን ከደቡብ ይወጣል በበሬ ይመሰላል ደለዊ ማለት ሁሉን አደላዳይ ወይም ኃይለኛ ማለት ነው በጎሽ በአንበሳም ይመሰላል ፡፡ ይህ ኮከ ብ ያለው ሰው ብርቱ ኃይለኛ ጠብ አጫሪ (ወዳጅ) ትምክሕተኛ ነው ያሰበውን ካላደረገ አይመለስም ትጉ ሰራተኛ ፍጥረት ነው ለኑሮው በፊቱ ላብ (ወዝ) ይታገላል ሥራም ይወዳል ብርቱ ደም ከአፍንጫው ያነስረዋል ሣቅ ያበዛል አንገቱን አቀርቅሮ ያሄዳል በገንዘቡ የተነሣ ይቆጣል የፊቱ ዐወራረድና የግንባሩ አኮመታተር በሬ ይመስላል ደም ግባታም እና ተወዳጅ ግርማ ያለው መልክ አለው እርሻ ክፍሉ ነው በግ ይረባለታል ነጭ ነገር ይሆነዋል ጨዋታ አዋቂ ነው መለማመጥን አይወድም እንጅ መኳንንት ያፈቅሩታል ፡፡ ጌታ ይሆናል ገንዘቡ ለልጁ አይተርፍም እንቅፋታም ነው በ15 በ፴ በ፵ ዓመቱ ይጠንቀቅ የልብ ሕመምና ሳል የሰፈራዋል ቀይ አረመኔ በግራጇ ምልክት ያለባት ሴት ቢያገባ ይወልዳል ትሆነዋለች የአባቱን ዕርስት ይወረወሳል ብዙ ልጆች ይወልዳል ዘማዊነት አለው እስከ ዘመዶቹ ማውሰብ ይደርሳል ፡፡

መልከ ቅን ተወዳጅ ነው ዘመኑን ሁሉ በሰላምና በደስታ ይኖራል ከሴት ፍቅር የተነሳ ከትልቅ አምባጓሮ ይደርሳል ሁልጊዜ መጠንቀቅ የሚገባው ከደም ነስርና ከውጋት ሕመም ነው ደለዊ ነፋስ የመሬት ሰራተኛ ብቻ አይደለም የጥብቅነትና ንግድ ሥራም እድሉ ነው ነገር ግን በሰው ዘንድ ስሙ በክፉ ይነሣል ፡፡ ፍርድና ርትዕ ምርመራም ያውቃል ንግግሩና አንደበቱ ተወዳጅ ነው መተቸትና ማስረዳት መተርጎምም ያውቃል ጠባዩ ብርቱ ነው ሐሰትም ቢሆን በተናገረው ይጸናል ጥልቅና እሩቅ የሆነ ምሥጢር ያውቃል እግዚአብሔርን ይፈራል የጉራና የመግደርደር ባሕሪይ አለው ወረተኛ ነው ገንዘብ ያባክናል ያገኛል ያጣል ሃብታም ነው ብዙ መከራ አያገኘውም ከመከራና ከፈተና ለመውጣት ብልህነት ተሰጥቶታል ወዳጅና ጠላት ባእድና ዘመድ አይለይም ቂም የለውም እንደ ርግብ የዋህ ነው አይሆንለትም እንጅ ንጹሕና ጌጠኛ ልብስ ይወዳል እድፋም ልብስ አይሆነውም የባዕድ አገር ዕድሉ ነው ባለ ጸጋ ይሆናል በተወለደበት አገር ግሰን ጠላት ይበዛበታል ሰጥቶ አይመሰገንም ለአጭር ጊዜ በድኅነት ላይ ይወድቃል ተበድሮም ቢሆን ሰውን መምሰል ይወዳል የሰው ምክር አይሰማም በአደጋና በጭንቅ ጊዜ ይሸበራል አይችልም ይጃጃል ወላዋይ ነው ሳያስበው በአጋጣሚ ብዙ ገንዘብ ያገኛል ፡፡ በሐሰት ይምላል ነገር ይጠብቃል እኔ ያልሁት ይሁን ይላል ሰውን ይንቃል ያቃልላል በምስራቅ አገር ክፍል አለው የኮሶ ምች የስፈረዋል ፡፡

በዘመነ ማርቆስ በጥቅምት ወር ያመዋል መድኃኒቱ ቀይ ወይም ነጭ ዳልቻ በግ ገብስማ ዶሮ ይረድ እውነተኛ ነው ዋስ መሆን አያምርበትም በትንሽ ነገር ንጉሥ የሆነ ያህል ይደሰታል ፡፡ ደለዊ ከዘመዱ ጋር አይኖርም እርሱም ዘመዱን አይወድም መቃብሩንና ሬሳውን ሊያይ አይፈቅድም ፡፡ የሚመለከተው ዛር ብር አለንጋ ነው የእግሩን ጫማ ጫንቃውንና ጉልበቱን ያመዋል ከደጁ ሥራይ ይጣልበታል አስቀድሞ ለዚህ የሚሻለው የቀይ ከላድማ ፍየል ቀይና ገብስማ ዶሮ ይረድ ቀይ ወይም ነጭ የአዳል በግ አርዶ መረቁን ይጠጣው በብራናውም ትምህርተ ኅቡአትንና ስመ አምላክን ኤኮስንና አካስን አስጽፎ ይያዝ አሳና ሰሊጥ ወገርትና ምስርች ጠንበለልም ሥራቸውን ሰናፍጭም ቅጠሉንና ፍሬውን እነዚህን ሁሉ በአንድነት አሰርቶ መረቃቸውን ይጠጣ ፡፡

ሆዱን ያመዋል በማርቆስና በሉቃስ ዘመን በጥቅምት ወር ዓርብ ቀን ያስፈራዋል ተጻራሪዎቹና ለሞት የሚያደርሱት ዛሮች ሰይፍ ጨንገር ወሰን ገፊ ጠቋር ዲራጎቶች ናቸው መድኃኒቱ ከላይ የተጻፈው ነው ፡፡

ፀረ ኮከቦቹ ሸርጣን ሰንቡላ ጀዲ ናቸው የክፍል ኮከቦቹ ደግሞ አሰድ ሰውር አቅራብ ማእከላዊ ሁት ገውዝ ቀውስ ናቸው ፡፡ ከዘመን ሉቃስ ከወር የካቲትና ጥቅምት አይሆነውም ፡፡ መልካም ቀኖቹ ሰኞና ሐሙስ ነው ፡፡ ክፉ ቀኖቹም ሮብና ዓርብ ናቸው ፡፡ የእድሜው ልክ ፷5 ዓመት ነው ቢያዝን ቢጸልይ ቢያሳዝን ፸5 ይሞላዋል ፡፡ በዘመነ ሉቃስ ነሀሴ 13 ቀን የደብረ ታቦር ዕለት ይሞታል ፡፡

ደለዊ ነፋስ ኮከብ ያላት ሴት የሆነች እንደሆነ ፡፡

እግርዋ ቀጭን መልከ ደማም ትሆናለች ቁም ነገረኛ ወላድ ሃብታም ባለ ብዙ ፍሬ ትሆናለች የሰው ፍቅር አላት ነገር ግን ትነሽ ቀን ትቀነዝራለች በወሊድ ጊዜ ደም የስፈራታል ዕጣንና ከርቤ ትታጠን ፡፡ እጅዋ ለመስጠት ቸርና ለጋስ ናት የተናገረችውና ያሰበችው ፈቃድዋ ካልሆነ በጅ አትልም ደግ ምክርና የነገር አመላለስ ታውቃለች በነጭ የአዳል በግ ብራና ትምህርተ ኅቡአትንና ኤኮሳትን አስጽፋ ትያዝ ደጋግ ልጆች ተወልዳለች በቤት አያያዝ ታውቅበታለች ቁጠባና ብለሕነት ዕድልዋ ነው ፡፡

ዕድሜዋ ከ55 እና ከ፷ አይበልጥም (አያለፍም) ፡፡