፭ አሰድ እሳት (አንበሳ)

፭ አሰድ እሳት (አንበሳ)

 

፭ አሰድ እሳት አንበሳ
Edit
ይህ ኮከብ በሐምሌ 26 በምሥራቅ የሚወጣ ነው አሰድ እሳት የመብረቅ እሳት ማለት ነው አሰድ የያዘውን አይሰድ ፡፡ አሰድ ፀሐይ ዕንቁ ባህርይ ይባላል ፡፡ በአንበሳ ይመሰላል ይህ ኮከብ ያለው ሰው የፊቱ አወራረድ አንበሳ ይመስላል ፡፡ ቁመቱ ድልድል ነበሱ ነጹህ ከእናቱ ማሕጸን የተመረጠ ልቡ የዋህ ገጹ ፍሱሕ ጥርሱ ፍንጭት ፡፡ ትልቅ ግርማ የዓይን አለው ጠላቶቹ ሲያዩት ይፈሩታል ይለማመጡታል በሴራ የመከሩበትን ሁል ጊዜ ያፈርስባቸዋል ማናቻውንም ነገር ቢፈልግ ለማግኘት ይቻለዋል የገንዘብ ስሱ ነው ጥቂት ነገር ይበቃ አይመስለውም ቁጡ ነው ቶሎ ይመለሳል ጠላት ይበዛበታል ግን አይሸነፍም ፡፡

እጅግ ምቀኛና ቀናተኛ ነው የሰውን ነውር ያወራል ኃጢአቱ ብዙ ነው በምጽዋት ይሰረይለታል ዘማዊ ነው ከዝሙት ብዛት የተነሣ ዓይኑን ያስፈራዋል ይሉኝተኛና አንደበታም ነው መንፈሳዊ መስሎ መታየትን በሰው መመስገንና ውዳሴ ከንቱን ይወዳል ፡፡ በእጁ ጥፍር ከላይ ወደታች ጥቁር መስመር አለው ድንገተኛና አደገኛ ነው ምሥጢርና ሴራ ክፍሉ ነው ስሙ በክፉ ይነሳል ውስጠ ደግ ወዳጁን ጠቃሚ ነው ዘመዱን አይጠቅምም ገንዘቡን ለባእድ ያባክናል ገፊ ነው ዘመዶቹና ወዳጆቹን ከሸኘ በኋላ ብቻውን ይቀራል ፡፡

ጊዜ ካነሳው ጋር ወዳጅነት ይገጥማል ገንዘቡን ከሰው ገንዘብ ጋር ማቀላቀል አይሆንለትም ኃይለኛ በኃይሉ ተመካሒ ነው እርሻና ቤተ-መንግሥት ክፍሉ ነው ሹመት ያገኛል ርኩስ ከብት ላም ንብ ይሆንለታል 3 ሚሰት ያገባል ከሶስተኛይቱ ደግ ልጅ ይወልዳል ሐሙስ ቀን መሰናክል ያገኘዋል ሁለት ጊዜ እሥራት ያገኘዋል ግን በቶሎ ይፈታል ለጋስ ነው የትም ቢሔድ የሰው ፍቅር አለው ሰጥቶ አይመሰገንም ጠላቱን ይወዳል በሸንጎ ሲቆም ረትቶ ይገባል ሰውነቱን እያሳበጠ ያመዋል ኮሶም እየደፈነ አያሽረውም እግዚአብሔርን ፈሪ ዓይነ ቅንዝረኛ ነው ጥቁር በግና ነጭ ዶሮ ይረድ ሰሊጥ አሣ ኤፍራን ቀለም በአንድነት አሰርቶ ይብላ መ ረቁንም ይጠጣ ከፀጕሮቹም 7 ቀን ይታጠን ፡፡ ከእዳሪ ውድቀት የተነሳ ሕመም ያስፈራዋል ዓይኑን ራሱን ያመዋል ዓርብና ቅዳሜ ከሰሰዉነቱ ደም አያጣዉም መ ድኃኒት አይጠጣ መንገድም አይሂድ የሰው ገንዘብ አደራ አያስቀምጥ አጥፊው ነው ሚስቱ በደም ትሞ ትበታለች ሴት ጋኔን በወጉቡ በልቡ እየገባች ታመዋለች 3 ጊዜ ገንዘቡ ይጠፋበታል እረሱም እየታሰረና እየተፈታ ይኖራል ሢሳይ አያጣም ገንዘቡን ለዘመዶቹ መስጠት አይወድም ከሚሰጥ ቢሰርቁት ይወዳል ዉሸቱን ነገር አሾክሹኩልኝ ይላል ልጆች ይወልዳል ጥቂቶች ይሞቱበታል ያልታወቁ ሰዎች ነጥቀው እንዳያጠፉት ያስፈራዋል ፡፡ በሀፍረቱ ለይ ምልክት አለበት በእግሩና በራሱ የሰው ዓይን ያስፈራዋል ጫጫታ የምትባል ዋናዋ የዛር ውላጅ ትሸምቅበታለች በዓይኑና በብልቱ ትገባዋለች ሌሊት በህልሙ ትገናኘዋለች ቀኝ እግሩን ጉልበቱን ወገቡን ራሱን ዓይኑን ልቡን እየላሰች ታመነምነዋለች ለዚህች መድኃኒቷ የቁለቋልና የሎሚ ተቀጽላ የአመራ ሥር ከርቤ ጨምሮ አንድነት በአዳል በግ ብራና በነጭ ጨርጬቤ አስጽፎ ይያዝ ከመድኃኒቶቹ ጋር በአንድ ላይ ይያዝ ፡፡

የመኖሪያ ክፍሉ ከተማ ቤተ- መንግሥት ነው ማቴዎስና ማርቆስ ተከታታይ ዘመኖች ክፍሉ አይደሉም በነዚህ ዘመኖች ይህን ጽሕፈትና ዕነዚያን ተቀጽዎች የነጭ ወሰራ ዶሮ ደም እየነከረ በኣመት በኣመት እያነገሰ ይያዝ የውሃ ሙላት የስፈራዋል ቅዳሜና እሁድን አክብሮ ተጠንቅቆ ይዋል ፡፡ ቀይ አረመኔ የሆነች ጋላ ሴት የግባ ይወልዳል ይከብራል ፡፡ ኮከበ ግጥሙ ሠውር አቅራብ ደለዊ ነው ፡፡ ፀሩ ሁት ጀዲ ሸርጣን ፡፡ ማዕከላዊ ሰንቡላ ገውዝቀውስ ናቸው መልካም ወራቶቹ ታኅሣሥና የካቲት ክፉ ወሩ ግነቦት ከፉ ቀኑ አርብ ነው፡፡ በ10 ፣ በ24፣ በ፴ ፣ በ፵ ፣ዓመት ያስፈራዋል ፡፡ በማቴዎስ ወይንም በማርቆስ በሰኔ ወይንም በነሐሴ ዓርብ ቀን በ79 ኣመቱ በድንገት ይሞታል ፡፡

አሰድ እሳት ኮከብ ያላት ሴት የሆነች እንደሆነ ፡፡

መኳንንት ያፈቅርዋታል አካሏ ንጹሕ ጥርሰ መልካም ናት ዘማዊነት አለባት ጥቁዉር ሰዉ ክፍልዋ አይደለም አጥፊዋ ነው የቂጥኝ ዕግል ያስፈራታል በመስከረምና ጠቅምት ዓርብና ቅዳሜ ቀን ሩቅ አገር አተሒድ ትጠንቀቅ አንድ ከወለደች በኋላ ማህፀኗ ቶሎ ፍሬ አይዝም እንደመካንነት ይከጅላታል ወንድ በመኝታ ያፈቅራታል የቤት አያያዝ ታውቃለች መብልና መጠጥ ትችላለች ለቤተሰብ መልካም ደግ የዋህ ናት የጥቁር ሰው ዓይን ያሰፈራታል የእጀ ሰብእ መድኃኒት ጨርጨቤ አስጽፋ ትያዝ ፡፡