፪ ሠዉር መሬት (ዝንጀሮ)

፪ ሠዉር መሬት (ዝንጀሮ)

ይህ ኮከብ  በሚያዝያ 16 ቀን  በዐዜብ  በኩል  የሚወጣ  ነው ፡ ይህ  ኮከብ ያለው  ሰው እጅግ  ገራም  ነው  ምስጢራዊ  ባሕሪ   አለው  ያደረገው ነገር ሁሉ  አይታወቅበትም  ምክንያቱም  ኮከቡ  ድበቅ ወይም  ሥውር ስለሆነ  ነው   ፡፡  እጅግ  ጌጥ  ይወዳል  ገንዘብ  በጣም  አይገባውም   እንጅ   ገንዘብ  ማውጣት  ጭንቁ  ነው  ንፉግ ነው  ፡፡ ሐብቱ  ሥውር  የኋላ ኋላ  ነው  በሰውነቱ ተመካሒ  አፈጻድቅ  ነው  ቅናትና  ምቀኝነት  አሉበት  ሲያውቅ አለዓዋቂ  ይመስላል  አንደበቱ ዝግተኛና  ልዝብ  ነው ቀልድና ጨዋታ  እድሉ ነው  እርሻ  ንግድ  ቤተ-መንግሥት   ይሆንለታል  ሰላማዊ   ነው  ኩሩ  መስሎ  ይታያል  ከሰው  ጋር  በቶሎ  አይላመድም   በቤተሰቦቹ  ላይ  ኃይለኛ  ገዥ  ነው ፡፡

ከበታቹ  ያሉትን   ያጠቃል   ፍርሃት  አያውቅም  ልበ-ሙሉ  ነው ወረተኛና  ውለታ ቆጣሪ  ብልህ  ነው ፡፡  ነገር  ግን  ሰው  አያምነውም  እርሱም  ሰው አያምንም  ለሁሉ  ተተራጣሪ   ነው  ፡፡ ከአሰበው  አይመለስም   የሰው  ምክር  አይቀበልም   ራሱን  ከፍአድርጎ  ገማችና  እኔ እበልጥ  ባይ  ነው  በተግባሩ  ሁሉ  አምላክን  ይለምናልና   ይረዳዋል  ጠላቶቹን ሁሉ  በጸሎት ድል   ያደርጋቸዋል  ፡፡  በኋላ ዘመን  ገንዘብ  ያለቅበታል  በጥቂት  መጠጥ  ይሰክራል  ሆዳም  ነው በመብልና  መጠጥ ሥራይ  ያስፈራዋል  የሚያደርጉበትም  ዘመዶቹ ናቸው  ወደ  ዘመነ  እርጅናው  የዓይን  ሕመም  ያስፈራዋል  በጋብቻው  የታመነ  ነው  የተባረኩ  ልጆች  ይወልዳል  እድሉ  በአንድ ድንገተኛ ነገር ነው  4 ልጆች  ይወልዳል  መሓላ  አየሆነውምና በእውነትም ቢሆን  አይማል ፡፡

ክፍሉ ነጭና  ቀይ መሬት  ነው  መሸጥ መግዛት መለወጥ  ሹመት  ክፍሉ ነው  ማስተዳደርና  ሥርዓት  ያውቃል  ቆላ አገር  አይሆነውም  ደጋ  ይስማማዋል   በዘመነ  ማርቆስ  ጥቅምትና ግንቦት  ሩቅ  አገር  አይሒድ  ቅስፈት  ያገኘዋል  ከሚወልዳቸው ልጆች  አንዱ  ሕመምተኛ ይሆናል  ሰው  ሲሞት  ሬሳ  አይገንዝ  ታስሮ ይፈታል  በዘመነ  ማርቆስ መጋቢት  ወር ሹመት ያገኛል  በዘመነ  ማርቆስ  ሩቅ አገር አይሒድ ጥቅምትና  ግንቦት  ቤት  አይለውጥ ቅስፈት  ያስፈራዋል  ሰውነቱ  ኃያልና  ደፋር ነው  እንዴ አይነት እያደረገ  ያመዋል   ሆዱ እንደ ሥራይ  የገለባበጥበታል  ጥሬ  ርጥብ ሥጋ  አይወድለትም  ጠብሶና ቀቅሎ  ይብላ  ቅናትና  ምቀኝነት  አሉበት  ተመካሒ  ሕለሙ እሙን  ነው ፡፡

ጋብቻው  አሰድ  አቅራብ  ኅብሩ  ሚዛን ቀውስ  ሐመል  ነው  እኩይ  ዕለቱ  ረቡዕ  አርብ እሁድ  ነው  የአርብ  ቀን  ያስፈራዋል   ነጭና   ቀይ  አርዶ  በደሙና ፈርሱ  ይታጠብ በ9 ዓመቱ  ያመዋል  በ፵ ዓመቱ  ግን  ሞት የስፈራዋል   ከወንጌለ  ዮሐንስ  ወሃሎ አሃዱ ብእሲ የሚለውን  አጽፎ  ይያዝ   ከበሽታ ሁሉ  ለጥፋት  የሚያደርሰው ዋና ፀሩ ተስቦ ነው ለዚህ መጠበቂያው  ቢሆን በሚዳቋ ቢታጣ  ግን  በነጭና  ቀይ የፍየል  ብራና  አቅዳፌርን  አጽፎ  መያዝ ነው ፡፡ የሚመለከቱት  ዛሮች ጢሞቴዎስና ብር  አለንጋ ከውላጅም  ደም  ቀለቡና  ዋስ አጋች ናቸው ራሱንና ዓይኑን ልቡን  እየከፈለ  ያመዋል  በግራ ዓይኑና  በግራ  እግሩ   ምልክት  አለበት    ሴት ጋኔን አለችበት   ሌሊት በህልሙ    ታስደነግጠዋለች   ሌሊት ልብሱን  ታስጥለዋለች ምቀኛ ሆና  ሃብቱን  ትዘጋበታለች   እረሷን ለማስለቀቅ  የሚበጀው ጊዜዋ  ጉመሮ ዕጣን የጅብ  አር  ዋግራ  ድብርቅ  አለቲት   የዶሮ   ላባ  እነዚህን  በአንድነት  ይታጠን   ስመ  አምላክና  ወንጌለ ማርቆስ   ድርሳነ  ሚካኤልንም በሌሊት  ውሃ  እያስደገመ  ከነዚያ መድኃኒቶችም  በውሃው  ጨምሮ ይታጠብ  ፡፡

ሠናይ  ወርኁ  ታኅሣሥ  እኩይ  ወርኁ  ጥቅምት  ጥር  ግንቦት  ነውና  ይጠንቀቅ  ቁርጥማት ወይንም ቂጥኝ   ከጥቁርሴት  ያስፈራዋል   መድኃኒቱ  ጣዝማ ሰሊጥ ጊዛዋ በማር  ይዋጥ  ፡፡   ከልከሎሳ  የሚባል  ጋኔን  በተወለደ  ዕለት  አይቶታልና በታመመ  ጊዜ  ያብዳል  ፡፡  መድኃኒቱ  ነጭ  በግ  ቀይ  ዶሮ   የበሬ  ቀንድ አርባ  ቀን  ያልሞላው  የመቃብር  አፈር   በአንድነት   አሳርሮ  ውሃ  በአልነካው  ቅቤ አድርጎ በ4 ማእዘን  መንገድ  ላይ  ቁሞ  ይቀባ ከእራሪውም  በጠጅ  አንፍሮ  ሶስት ቀን  ይጠጣና    ይለቀዋል  ፡፡

በእግሩ ቁርጥማት  ይሰማዋል   በራሱ  በልቡ  በሆዱ  በሽታ  ይገባበታል  ለዚህ ሕመም  መድኃኒቱ   ዋግራ ድብርቅ አልቲት ሮብ  ቀን  ሰብስቦ ከጥቁር  ስንዴ ጋር በጨው አንፍሮ ለቀይ በግ  ሰባት ቀን ማብላት ነው  ከዚህ በኋላ  በጉን  አርዶ በደሙ ታጥቦ  ሥጋውን  ቀቅሎ  መረቁን  በስንዴ  እንጄራ  እየፈተፈተ  ይብላ  ከእህልም  ስንዴ  ግጥሙ  ነው ከመረቁ  ይጠጣ ቀይ ዶሮ  ወሰራ ጭዳ ይበል  ሞቱ  በዘመነ  ማርቆስ በ፸ኛ  ዓመቱ   በወርኃ  ጥቅምት  ሮብ  ቀን  ነው ፡፡

             ሠውር መሬት  ኮከብ ያላት  ሴት የሆነች  እንደሆነ   

ዕውር   ደም  ይመታታል  ዓይኗ  ቀላ  ያለ ጥሩ  ነው  ቀናተኛ ናት  አመንዝራነት   አለባት ባሏን  በእጁ ነብስ  እስኪያሳልፍ  ድረስ   ታስቀናዋለች ቅዳሜ   ቀን  አይሆናትም  ደም   ከፈሰሰበት  ሥፍራ  አትድረስ  በመቃብር የሚኖር  ከልከሎሳ  የሚባል ጋኔን  ይፃረራታል  ግራ  ዓይኗን  ያማታል   ሆዷን  እያላመጠ   ደም  እንደ  ውሃ   ይፈሳታል እግሯን  ይቆረጥማታል  ሰኔ እና  ጥቅምት  አይሆናትም አቅዳፌርን  በእንስት  ሚዳቋ  ብራና  አጽፋ  ትያዝ ፡፡

የጥቁር  ገብስማ  ዶሮ ጭዳ  ብላ ሥጋውን   ትብላ  መረቁንም   ትጠጣ   ከዚህ  በኋላ  የደም  ጽሑፍና  አቅዳፌርን   ጨምራ  ትያዝ  ሰውነቷ   በፊቷ  ደነዳና  ነው ፀጉሯ  ልስልስ  ነው   ስስት  አለባት ቁምነገርና  ሃይማኖትም  ይገኝባታል  ፡፡