፲ ጀዲ መሬት (ንስር)

፲ ጀዲ መሬት ንስር
Edit
10ኛው ኮከብ ጀዲ መሬት ፡፡

ይህ ኮከብ በሐምሌ ወራት በምሥራቅ በኩል በመንፈቀ ሌሊት ይወጣል ፡፡ ኮከብ ጀዲ በንስር ወይም በሸረሪት ይመሰላል ጀዲ መሬት ደባይ መሬት (ዋልካ ) መሬት ማለት ነው ጀዲ ነገር ወዲ ይባላል ፡፡

ይህ ኮከብ ያለው ሰው እንደ ንስሩ ፈጠን ነው ፍርሃት የለውም አደጋ ጣይ ጨካኝ ኩርፍተኛ ባልንጀራውን አክባሪ ጨዋታ ወደጅ ነው ወዳው ካልተበቀለ ቂም አይዝም ፡፡ ጽህፈት መሰንቆ የጌታቤት እርሻ ክፍሉ ነው ፡፡ በደባይ (ጥቁር) መሬት ይኑር ከብት አፈ ጭቃ ፈንዝማ ይረባለታል በሰው ዘንድ አይለማመጥም ዝምተኛ ነው ብቸኝነት ይወዳል ራሱን ማዋረድ አይወድም ግን ሰው ይወደዋል ለሰው ከቶ አድሎ የለውም ቀጥያለ ሀቀኛና እሙን ነው ትንሽ እለህ አለበት በእልኩ ከትልቅ አደጋ ይደርሳል ክፍሉ ጠይም ሰው ነው ስንደዶ ከሚበቅልበት ቦታ ይኑር ልቡ ብሩህ እግዚአብሔርን ፈሪ ሕልሙ የታመነ ነው ከፍ ያለ ማሰብ አለው ሥጠታው ነውና የጅሥራው ይደነቅለታል በምቀኞች ብዙ ጊዜ ይንገላታል ይቀኑበታል ይመክሩበታል በመጨረሻ ግን ያሸንፋል አትክልትነ እረሻ በጥቁር መሬት ይሆንለታል ተጸጻች ምሕረተኛ ቸር ይቅር ባይ ነው ምቀኛ እና ሌባ አንድ ጊዜ ንብረቱን ይዘርፉታል በልቡ ትዕቢት ያበዛል እስከ ዘመነ ሽምግልናው ድረስ እጅግ ዘማዊና ቅንዝረኛ ነው በሴት ነገር ተከሶ በፍርድ ቤት ይቆማል በሴት ነገር የተነሳ በእጁ ነብስ የጠፋል በብርቱ እልከኛ ነው አዛኝም ነው የኋላ ኋላ ወደ አባቱ ርሰት ይመለሳል ጥቁር ነገር ሁሉ ክፍሉ ነው በሽምግልና ዘመኑ መጠጥ ያበዛ እንደሆነ ዓይኑ ይጠፋል ጤናው ይሰናከላል የራሱ ጠጉር ሽልት ነው በቀኝ እጁ ምልክት አለበት ሀብታም ነው መኳንንት የወዱታል ፡፡

ሳይደኸይና ሳይበለጽግ በልክ ሆኖ ደሰታና ኀዘን እየተፈራረቀበት ይኖራል ጸሎቱ ግን ስሙርና የተወደደ አስብ ያለው ነው ፡፡ ስደት ያገኘዋል ዕድሉ ነውና በሰው አገር ይከብራል በመመላለስ ሀብት ያገኛል የመለእክት ጉዳይ ይከናወንለታል ባሕርዩ እጅግ ንጹህና የዋህ ነው ገንዘብ ይወዳል ንፍግ ግን አይደለም መቆጠብን ያውቃል ዓለማዊነትን ይወዳል እስከ ሽምግልና ዘመኑ ድረስ ዘማዊነት አያጣውም እጅግ ቅንዝረኛ ነው መጻሕፍት ለመጻፍ ቅኔ ለማስተካከል ስጦታ አለው የተማረ እንደሆነ ማንበብና መተርጎም ጽሕፈትም ክፍሉ ነው እሳት ይለክፈዋል ውሃ ሙላትና መብረቅ ያስፈራዋል ፡፡ ዓይኑ እንደ መነጽር ነው ልቡ ብሩህ የክርስቲያን ወዳጅ የአረመኔ ጠላት ነው ቂጥኝ ንዳድ ውጋትና ኩፍኝ ያስፈራዋል ሌሊት በዝናም ወደ ደጅ አይውጣ በ22 ዓመቱ ይታመማል በ፶ ዓመቱ ሞት ያስፈራዋል ፡፡

የመጀመሪያ ሚስቱ ትፈታዋለች ከብዙ ጭቅጭቅ በኋላ በደህና ይኖራሉ ቤተ ሰዎቹና ጎረቤቶቹ ይመቀኙታል እግር ብረት የስፈራዋል በብረት ቁስል ያስፈራዋል ፀሐይ ታይወጣ መጓዝ አይመቸውም ዘፈንና ዜማ ይወዳል ቁምነገራም ነው ሀሰት አይወድም ቀይ ሴት ዘመዱ በጉሽ ጠላ ወይም በስዴ እንጀራ በዘመነ ማቴዎስ በግንቦት ወር መድኃኒት ታደርግበታለች ፡፡ በጀርባውና በጭኑ ምልክት አለበት አንድ ጊዜ እግሩን ብርቱ ቁስል ያመዋል ፡፡ መጋኛ ቀኝ እግሩን ጉልበቱን ወገቡን ያመዋል ሆዱን ይነፋዋል የዛር ውላጅ ያስፈረዋል የሰው ዓይን ይወጋዋል የሚመለከቱት ዛሮች ብረ አለንጋ ሰይፍ ጨንገር እንቁላል ናቸው ዋስ አጋች የመባል ዛርም ገና ሲወለድ በደም ላይ ጀምሮ ቁራኛ ሁኖ ይጠባበቀዋል ጠቋርም ይወጋዋል ሁለመናውን ይልሰዋል በጥቁር ፍየል ብራና መርበብተ ሰሎሞንንና መስጥመ አጋንንትን መ ፍትሔ ሥራይንም አስጽፎ ይያዝ ዳልቻ ወይም ጥቁር ገብስማ ዶሮ ወይም ነጭ ዶሮ ጭዳ ብሎ ይረድ ፡፡

ምንጊዜም ሲያመው ለሕመሙ የሚበጀው ቡይት ወፍ ዓሣ ሰሊጥ አፍርንጅ በጥቁር ላም ወተት እያማገ ይብላ ፡፡ የበቀለ ቀንድ የቁልቋል ሥር የዘምባባ ሥር አንድ ላይ ደቁሶ በመሃል እራሱ በጥቶ ያግባ የቡያ የእረግብ ሥጋ የሪያ ሥጋ የአውራሪስ ቀንድ አንድ ላይ አድርጎ ይታጠን ኤፍራን ቀለም ነጭ እጣን አበ ሱዳ በጠጅ አንፍሮ ይጠጣ ፡፡ ኮከበ ግጥሙ ሐመል ሚዛን ሸርጣን ናቸው ፀሩ ቀውስ ገወዝ አሰድ ነው መእከላዊ ደለዊ ሰውር አቅራብ ነቸው ፡፡ ዘመነ ማርቆስ የስፈራዋል ከወሮችም የካቲትና መጋቢት ግንቦት አይሆኑትም ኅዳርና ታኅሣሥ ግጥሙ ነው ሮብና ዓርብ ቀን አይሆነውም ሰኞና ቅዳሜ ግጥሙ ነው በዘመነ ማርቆስ በግንቦት 13 እሁድ ቀን በ፸ ዓመቱ ይሞታል ቢጸልይ ቢያዝን ቢያሳዝን ፹ ይሞላዋል ፡፡

ጀዲ መሬት ኮከብ ያላት ሴት የሆነች እንደሆነ፡

በጥርስዋ ላይ ምልክት አለባት ሃብታም ናት ጥሪትና እራት አላት ልጆች ትወልዳለች አንድ ልጅ ይሞትባታል ደግነትና ቸርነት አላት የዋህነት አለባት ሰውነቷን ችላ ትለዋለች ሰውን አማኝ ናት ግን ወዳጆቿ ይከዷታል ንፉግ ናት የኋላ ኋላ ትቸገራለች አረመኔ ባዳ ያገባታል ፡፡ በወሊድ ደም ያስፈራተል የደም አብነት ትያዝ በጥቁር ፍየል ብራና አስማተ ሰሎሞንን ከእሪያ ሥጋ ጋር አስጽፋ ትያዝ በ፵ እነ በ፶ ዓመቷ ሞት ያስፈራታልና ትጠንቀቅ ፡፡

የሚመለከቷት ዛሮች ቁርጠትና ሚሚት ናቸው በአንገቷ ኮልባና መዳብ ቀለበት ብታስር ይሻላታል ቡሃ በግ ጭዳ ብላ አሳርዳ በደሙና በፈርሱ ትታጠብ ፡፡