፱ ቀውስ  እሳት (ጅብና አውራሪስ)

፱ ቀውስ  እሳት (ጅብና አውራሪስ)

 

ይህ ኮከብ ከ8 ከዋክብት ጋር በታኅሣሥ 11 ቀን በዕርበተ ፀሐይ የሚወጣ ነው ፡፡ ቀውስ እሳት ረመጥ ወይም የተዳፈነ እሳት ይባላል ፡፡ በጅብና በአውራሪስ ይመሰላል ፡፡

ይህ ኮከብ ያለው ሰው ደስታውንና ኀዘኑን ጥቅሙንና ጉዳቱን ለሰው አይነግርም ምሥጢሩ ሁሉ ሥውር ኃይሉ ድብቅ ጻድቅ መንፈሳዊ እግዚአብሔርን ፈሪ ጾምና ጸሎትቱ ሥሙር ነው ፡፡ ብቸኝነትን ይወዳል ልቡ ቅን ነው ምስቱ ትሞትበታለች ወይም ትፈታዋለች ገርና ቅን ሰው አማኝ ነው በገርነቱ ትዳሩን ያሰናክላል ሓሳብ ያበዛል አይፈጸምለትም ነገር ይረዝምበታል ቶሎ አይቆረጥለትም በቁም ነገራምና ትንቢተኛ ይሆናል አስቀድሞ እንደሚያሸንፍ ሳይገምት በቶሎ ለጠብ አይነሳም በሰው ነገር ዘልሎ አይገባም ገርነት አለዉ ራሱን አኩሪ ተመካሒ ብልህ ጥበብ አዘጋጅ ለሴት ገራምና የዋህ ነው በትንሽ ነገር አዝኖ በትነሽ ነገር ይደሰታል ፡፡ ጥፋትና ስህሰተት ሞመልቶታል ፡፡

አይነሣም እንጅ ከተነሳ እነኳን ሰውንና ፈጣሪውንም የደፍራል ከያዘ አይለቅም ዓይኖቹም ልሞች ናቸው ድምጹ ለሰው ደስ የሚያሰኝ ነው በቤተ -መንገሥት ይኑር ቀይ ነገር ክፍሉ ነው ፡፡ ከጥቁር ከብት ወድቆ ይሰበራል በዓይኑና በፊቱ ልዩ ምልክት አለበት ብዙ ልጆች ይወልዳል አብዘኛዎቹ ሤቶች ይሆናሉ ሶስት ዕድል አለው ከ3ቱ እንኳ ቢይዝ ሃብታም ይሆናል አንዱን ካልያዘ ግን ተራ ሰወ ሆኖ ይቀራል ፡፡

ሰው ያማዋል ሓሜት ልብሱ ነው ቀጠሮ አፍራሽ ነው በሴቶች ዘንድ ተወዳጅ ነው እድፋም ልብስ አይሆነውም ዘወትር ነጭ ይልበስ ሰው ሁሉ ይፈራዋል ገራም ነው የኋላ ኋላ ምንኩስና ክፍሉ ነው የሽንት ምጥ ይስፈራዋል ፡፡ ብዙ ምቀኛች ይነሡበታል ያባርሩታል ሥራውን ያሰናክሉበታል ነገር ግን በማሰናከላቸው ይጠቀምበታል ብርቱ ነኝ ባይ ነው ነገር ግን ወዳጆቹ ያስሸንፉታል ዘመዶቹ አይወዱትም እርሱም ከዘመድ ይልቅ በእድን ይጠቅማል ነገር ይቈሰቁሳል የቈሰቆሰው ነገር እሰከ ዳር ሳይደር አያርፍም ቀይ ነገር ክፍሉ ነው በቀ ይቦታ ይኑር ለጤናውና ለኑረው በገጠር ይመቸዋል ክፍሉ ግን ከተማ ነው በምሥራቅ ይኑር ፡፡

ንዳድ ያስፈራዋል ዓይኑንና ጥርሱን እንደቁረጥማት ያመዋል እነጀራው በሽበት ነው ነጭና ቀይ በግ ዳልቻ ፍየል ይረድ የኣማኑኤልን ጠበል ይጠጣ በ2 ወይም በ12 ዓመቱ ምታትና የጉሮሮ ሕመም አለበት የቡያ የርግብ የምጥማጥ የሸላ የፍልፈል ሥጋ ሥረ ብዙ ዳበዛ ጽጌረዳ ሥራቸውን ከነዚያ ሥጋዎች ጋር አንድነት ደቁሶ ይታጠን ፡፡ በማቴዎስ እስራት ያስፈራዋል በመሥከረምና ታኅሣሥ የካቲት ነሐሴ ዓርብ ሮብ ይጠንቀቅ ክፉ ነገር ያገኘዋል መብረቅ ያስፈራዋል ፡፡ በዘመነ ዮሐንስ ቅዳሜ ቀን ይሾማል በ፵ ዓመቱ መቅሰፍት ና የሰው ልሳን ጭምር ያስፈራወል ፡፡ ነገሀር በአሰበ ጊዜ ልቡ ይዘራል በእግሩና በእጁ ምልክት አለበት በዘመነ ማቴዎስ ሰኔ 12 ቀን ዕንቅፋት ያገኘዋል ጥቁር ፍየል ይረድ ዓሣ በሰሊጥ አሰርቶ ይብላ በታመመ ጊዜ ነጭ ዕጣን ሎሚ የዓሣና የከርከሮ ሥጋ ቀቅሎ ይብላ መረቁንም ይጠጣ ፡፡

በተቆጣ ጊዜ ጀርባውን ያመዋል ሐሳብ የበዛል ነቀርሳ ያስፈራዋል መድኃኒቱ የአሜራ ሥር የዋንዘ ሥረነ ቅረፊት አሳርሮ በቅቤ ለውሶ ከሚያመው ለይ ያድርግ ፡፡ በሰኔ ወር እንደሳል ያመዋል ያርክ የሚባል አስማት ኤኮስን ጨምሮ በነጭ ዶሮ ፊኛ ጽፎ ይያዝ ፡፡

እጁን ቁርጥማት ያመዋል ዓይነ ጥላው በነጭ ፍየል ወይም በነጭ በግ ብራና አለቦ ስምነሰ 4ቱ ኤኮሳትን ሱስንዮስንና ጸሎተ ንድራን ከነዚያ ከተጻፉት ሥሮችና ሥጋዎች ጋር ቀምሞ ይያዝ የሚመለከቱት ዛሮች ቆስጤ ጅጀኖ ከውላጅም ኩርንችትና በጣሳ ናቸው በቀኝና በግራው እየተዘዋወሩ ያበሳጩታል ሴት ዛር ታድርበታለች ዓይኑን ትተናኮለዋለች ደም አስመስላ ታፈዝበታለች እግሩን ራሱን ጫንቃውን ልቡን ያመዋል ጆሮውንም ያደነግዘዋል ለዚህ ሁሉ አስቀድሞ የተጻፈውን መድኃኒትና ዓይነጥላውን በይዝ ይሻለዋል ፡፡ ጭዳው ዳልቻ ፍየል በግ ዶሮ ነው ክፍለ ፈረሱ ቡላ ሐመር አፈ ሹሌ ቡላ በቅሎም ይጫን ፡፡

ዕኩይ ዕለቱ ሐሙስና ቅዳሜ ነው ሠናይ ዕለቱ ረቡና ዓርብ ነው ፡፡ በዘመነ ማቴዎስ የሰኔ ተክለሃይማኖት ዕለት ያስፈራዋል ፡፡ ጋብቻው ሑት ሰንቡላ ገውዝ ፀሩ ሸርጣን ሰውር አቅራብ ነው ፡፡ማእከላዊ ጀዲ ሐመል ሚዛን ናቸው ፡፡ በዘመነ ማቴዎስ በ፷8 ዓመቱ ቅዳሜ ቀን ይሞታል ፡፡

ቀውስ እሳት ኮከብ ያላት ሴት የሆነች እንደሆነ ፡፡

ላህይዋ መልካም ነው ደም ግባት አላት ሳቂተኛ ትሆናለች ዓይነ ዘማ ናት ሆዷ ቂመኛ ነው ግን በቶሎ ትመለሳለች የሰውን ባህሪ መጣኝ ልበ ብልህ ናት ልክ አዋቂ ቤቷን ወዳጅ ወዳጇን አፍቃሪ ቁም ነገራም ናት ደጋግ ልጆች ትወልዳለች ሆዷን ልቧን ዓጥኗን ያማታል በወሊድ ደም ያገኛታል የርግብ ሥጋ በሰሊጥ አዘውትራ ትብላ ፡፡ በደም ግባቷ ትመካለች ጥርሰ መልካም ናት ማን ይበልጠኛል ትላለች ዕድሜዋ ፷ ዘመን ነው ፡፡