፰ አቅራብ ዉሃ (ነብር)

፰ አቅራብ ዉሃ (ነብር)

፰ አቅራብ ዉሃ ነብር
Edit
ይህ ኮከብ ኅዳር 8 ቀን ከ8 ከዋክብት ጋር በመንፈቀ ሌሊት የሚወጣ ነው ፡፡ አቅራብ ውሃ ማለት ግድብ ውሃ ዓዘቅት ማለት ነው በነብር እና ዝሆን በጊንጥም ይመሰላል ፡፡

ይህ ኮከብ ያለው ሰው ወዳጅና ጠላቱን አስተካክሎ ይወዳል ገራምና ለጋስ ነው ሠጥቶ አይመሰገንም ቁጡ አትንኩኝ ባይ ጨካኝ ዘማዊ አባይ ነው ጸሎቱ ይሰምርለታል ከፍተኛ ባሕሪና የተሰወረ ምሥጢር አለው መሰሪ ነው የወጠነውን ነገር ሁሉ ከፍጻሜ ለማድረስ ይሆንለታል ብዙ ጠላቶሀች ይነሱበታል ብዙ ትግልና ፈተና ይደርስበታል የጠላቶቹን ተነኮልና ወጥመድ ቆርጦ ይጥላል ብርቱ ኃይለኛ ነው የጥላቶሀቹን መውደቅ ያያል ደሥታና ኀዘን መውደቅና መነሣት ሀብትና ድኅነት ይፈራረቁበታል እንደነብር ዘወትር ጠርጣሪና ንቁ ነው ቁጥብ ነው እንክልፍ እስቲከለክለው ድረስ ከፍ ያለ ሃሳብና ምኞት አለው ፡፡

በ፴ ዓመቱ ዓይኑን ይጋርደዋል በእጁ ነብስ ያጠፋል ለኩነኔ የተገባ ነው ልቡበ ክፉ ቂም ያዥ ተበይ ነው ከወደደ በቶሎ አይጠላም ከአል መሀነኮሰ አይጸድቅም በ፶ ዓመቱ የመነኮሰ እንደሆነ ምሥጢረ እግዚአብሔርን ለማየት ይበቃል ሀብቱ እንደገና ይፈላል 7 ልጆች ይወለልዳል ጥቂቶች ይሞቱበታል በገርምስና ዘመኑ እግዚአብሔርን እነኳ አልፈራም ይላል አንደበቱ ደፋር ልቡ ጨካኝ ነው በሐሰት ሰውን ይረታል ትጉህ ጸላይ ነው የአባቱንና የእናቱን ገንዘብ ይወርሳል እጀ እርጥብ ሢሳያማ ነው እራት አያጣም ፍጹም ክፍሉ እረሻና የእጀ ሥራ ነው ሌሊት በሓሳቡ ሁሉን ሲከናውን ያድራል መሬት ሲነጋ ግን የሚጨበጥ ነገር የለውም ምሥጢሩ ለብቻው ነው ለሰው ማታለል መሸንገልና መደለል ዕድል ነው በአንደበቱ ደግ ባልንጀራ ይመስላል ነገር ግን ልቡ ከዳተኛ ተንኮለኛ ነው ፡፡

ኃየለኛና ኩሩ ነገር ወዳጅ ወረተኛ ሓሰተኛ ዓይነ ደረቅ ነው በተወለደበት አገር አይደላውም በሰው አገር ይሾማል ክፉ ቃል ቢናገርም ይደነቅለታል ስለ ጥቅሙ ሲል ይታገሳል እንጅ ቁጣ የባህሪዩ ነው የሚበልጠውን ሰው ሲያይ ዓይኑ በቅንዓት ደም ይለብሳል ጥዳሩ ይሰናከልበታል ፡፡ አጋጊጦ መታየት ይወዳል ገንዘብ ያባክናል ለጋስ እየተባለ ሊመሰገን ይፈልጋል ከ፵ ዓመቱ በኋላ ጠባዩ ይለወጣል ንፉግ ቆጣቢ ይሆናል ማንንም አያምንም ጠርጣሪ ሞገደኛና ተከራካሪ ነው ፡፡ ለሚስቱ ምቹ አይደለም ግምባሩ ገፊ ነው ቤተ ሰዎቹን ይሸናል ግራ እግሩን ያመዋል ከፈረስ ከገደል ከዛፍ ወድቆ መሰበሀር የስፈራዋል አንድ ጊዜ ከትልቅ ፈተና ይገባል ይህን ፈተና ዘልቆ ግን ከትልቅ ደረጃና መዕረግ ይደርሳል ለዘመዶቹ ረጅና መመኪያ ይሆናል በሽምግልና ዘመኑ ዘመዶቹንና ወገኖቹን ይጠቅማል ፡፡

ሌጊዎን የሚባል ጋኔን በፊትና በኋላ ይከተለዋል ከሴት መድኃኒት ይጠንቀቅ ቡዳ ቁስል ቁርጠት ቁርጥማት ያመዋል ሚስቱን በደም ያስፈራታል እጁን እግሩን ራሱን ያመዋል ከዘመነ ማርቆስ ወደ ዘመነ ሉቃስ ሲሸጋገር በመጋቢት ሮብና ዓርብ ቀን የምታት በሽታ ያገኘዋል መድኃኒቱ የዶሮ ኩስ የሚባል ዕፅ ጉመሮ የአረገፍጋፎ የእነዚህን ሥር 7 የጊነጥ ራስ የምጥማጥ ሥጋ የፍየል ቀንድ አንድ ላይ ቀምሞ 3 ቀን ይታጠን ፡፡ ይታጠን ከነዚህ መድኃኒቶችም ቀንሶ በአምሳያ ላም ቅቤ ለውሶ 7ቀን ገላውን ይቀባ ፡፡ ግንቦትና ጥቅምት ሕመም ያስደነግጠዋል መበድኃኒቱ ጉመሮ ጊዜዋ ምስርች ይታጠን በጀጥቁር ፍየል ብራና ሓፁረ መስቀልና ቆÅርያኖስን አስጽፎ ጊንጥ ጨምሮ ይያዝ ዓሣና ሰሊጥ አብስሎ ይብላ አጥንቱንም አንቀጸ ብርሃንን አስደግሞ ይታጠን ፡፡ የከረጥ ተከጽላ ይያዝ ፡፡ በተወለደ በ2 በ35 በ፵ ዓመቱ በርቱ ሕመም ያስፈራዋል መድኃኒቱ ጥቁር ዱልዱም ዶሮ የጥቁር ገብስማ ዶሮ ጭዳ አድርጎ የቅድሙን መድኃኒቶች በዶሮው ደም ነክሮ ከትቦ ቢይዝ ደግ ይሆንለታል ፡፡

ሠናይ ወርኁ መስከረም ኅዳር ታኅሣሥ ጥር እኩይ ወርኁ ጥቅምት የካቲት መጋቢት ሠናይ ዕለቱ ሰኞ ማክሰኞ ሐሙስ ፡፡ እኩይ ዕለቱ ዓርብ ሮብ ነው ፡፡ ኮከበ ፀሩ ሓመል ገውዝ ሚዛን ነው ፡፡ ግጥሙ ደለዊ ሠውር አሰድ ፡፡ ማዕከላዊ ቀውስ ሸርጣን ሰንቡላ ናቸው ፡፡

በዘመነ ዮሐንስ በጥቅምት ወር እሁድ ቀን በ፸7 ዓመቱ ይሞታል ያዘነ የተከዘ የጸለየ እነደሆነ ግን እስከ ፹5 ይቆያል ፡፡

አቅራብ ውሃ ኮከብ ያላት ሴት የሆነች እንደሆነ ፡፡

ማሕፀኗ ስፉሕ ነው ብዙ ልጆች ትወልዳለች ሾተላይ ይጸናወታታል ከጋኔን የተቀላቀለ የዛር ውላጅ ይመለከታታል ልጀችም ይሞቱባታል ለጊዜው ቁጡ አኩራፊ ሆዴ ባሻ (ገር) ናት ኋላ ግን ቻይ ቶሎ ተመላሽ ነት ፡፡ ሃብቷንም ፊት አሳይቶ ኋላ ያጥርባታል ጕርሻ ትወዳለች ደረቅ ናት ነገርዋ ለሰው አይጥምም ፊተ ረጅም ናት ቅንዝረኛነት አታጣም ፡፡ ከክንፉና ከእግሩ ጥቁር ያለበት ነጭ ዶሮ ጭዳ ትበል ፡፡ በጥቁር ፍየል ብራና ሓፁረ መስቀል አስጽፋ ትያዝ ዕድሜዋ ፷5 ዓመት ነው ፡፡