፩ ሐመል እሳት (ድብ)

፩ ሐመል እሳት (ድብ)

ለማንበብ መግቢያዉን ይሙሉ (Login)

[wpforms id=”10268″]

ሐመል እሳት  የእሳት ነበልባል ማለት ነው፡ ከመጋቢት 14 ቀን ጀምሮ   ማታ ማታ ይወጣል  ይህ ኮከብ ያለው ሰው እንዴ ኮከቡ ብርሃን አእምሮው  ብሩህ  ነው እጅግ  ኃይለኛና  ደፋር ነው የአንደበት ስጦታ አለው ደግነትም አያጣም ከፍያለ ሐሳብ አለው  ከሽመግልና  ጊዜው  አስቀድሞ ባለ ዘመኑ  መርሳትና መዘንጋት የለውም አደረገዋለሁ ይሆንልኛል ብሎ  የወጠነው ሥራና ነገር ሁሉ ይከናወንለታል   ወደአሰበው ለመድረስ  ብዙ መሰናክል ያገኘዋል  ነገር ግን  በሐሳቡ ቆራጥነት ሁሉንም በመጨረሻ ያሸንፋል ፡፡

ኮከብ እሳትነቱን  የሚያጠፋው   የለውም አድመኛ  ነው  ተንኮለኛ ግን  አይደለም  ሴትን  ይፈራል  እጅግ ለጋስ  ነው  ተበድሮም ቢሆን ይሰጣል ወዳጅና  ጠላቱን  መምረጥ  አያውቅም ለባልነጀራነት ዝቅተኞቹን  ይመርጣል ሳያጠና  ሳያገኝ ይነራል ፡፡ ገንዘቡ ይመጣና  ይሄዳል እጁ አመድ አፋሽ  ነው ሰጥቶ አይመሰገንም  ቅንዝረኛ ነው ከ40 ዓመት በኋላ ባለጸጋ ይሆናል ፡፡ ሰፊ   ዝና አለው ከብዙ ሰው ጋር ይተዋወቃል ፡፡

የወለደው አይባረክለትም  እስከመግደል  ድረስ  ይሻዋል  የሽምግልና ዘመኑን በትካዜ  ይገፋዋል  ምናልባትም የረጅም ጊዜ እስራት ያገኘዋል  ፡፡ በእልኩ  ምክንያት ዕደሉን ያበላሸዋል ቂመኛና  ተበቃይ  አይደለም  በዳኝነትና ጽሕፈት ዕውቀቱ  ከፍ ያለ ነው  ነገር መተቸትና ማስተካከል ያውቃል ሕልሙ የታመነ ነው  ንጉሥና መኳንንት ያፈቅሩታል   አፈከባድ ሀብታም ነው በ4ቱም ማእዘን ሰው ሁሉ ይሰግድለታል፡፡  በዘመነ ማቴዎስ ሞት ያስፈራዋል  በጥቅምት  ወር ሆዱን ፣ራሱን  ግራ እገሩን ያመዋል ፡፡

ሥራይ ያስፈራዋል  በ15ናበ22  ዓመቱ ፡ ክፉኛ ይታመማል ፡ በ50 ዓመቱ ክፉ ነገር  ያገኘዋል  በዘመነ ሉቃስ  በመስከረምና ህዳር በሚያዚና ሐምሌ ውጋትና ሳል ያመዋል  በታመመጊዜ የዝግባ ቅጠል  ዘፍዝፎ  ይታጠብ  ሙጫውንም  ይቆርጥም   ጋኔን ና አንበሳ  አጥፊው  ነው  ሲታመም ጽጌረዳና ሰሊጥ  የእርግብ ሥጋ  ይብላ  መረቋንም ይጠጣ  ክንፏንም  ይታጠን ፡፡ 

ሠናይ ዕለቱ ሰኞ  ማክሰኞ  ቀዳሚት ፡ እኩይ ዕለቱ ረቡዕ  ዓርብ  እሁድ ነው መድኃኒቱ በአዳል በግ ወይም በነጭ ፍየል ብራና መፍትሔ ሥራይ ለዓይነ ጥላ መርበብተ ሰሎሞንን ለመእሰረ አጋንንት አንድም ሰይፈ መለኮትን አጽፎ  ይያዝ ቀይና  ነጭ  በግ ይረድ  ቀይ ዘርዘር ዶሮ ይረድ  አምበላይ አፈ ሹሌ ፈረስ ይጫን  ቤተ -መንግሥት ፣ ንግድ ፡ እርሻ ክፍሉ ነው ፡፡   ቁሙ ነዊህ(ረጅም) ገጹ ፍሱሕ  ነው ፡፡

ዓይኑ እንደ ኮከቡ  ብሩህ  ነው  4 ሴት ያገባል 3 ልጆች ይወልዳል  አባት እናቱን  አይቀብርም  ነጫጭ  ነገርና ከብቶች ይሆንለታል ምቀኛ  እንደ ጦር  ይነሳበታል ለጊዜው  ልቡ ይፈራል ያመነታል  የኋላ ኋላ  ግን  በድፍረት ተነስቶ  ጠላቶቹን ሁሉ ድል ያደርጋቸዋል፡፡  ለጊዜው ቁጡ ነው  ኋላ ግን  ፈጥኖ  ይመለሳል ርኅሩህ  ነው  ጥቂት  ዘመን  ዘማዊነት   አለበት  የሴቶች በሽታ  የስፈፈራዋል በፊት  ሀብት  ያገኛል በመካከል ይደኽያል  እስከ 40 ዓመት መቅሰፍት  ያስፈራዋል  ከ፵ ዓመት  በኋላ ግን ሀብትና ዕድሜ  በብዙ  ያገኛል  ቀይ ነገር ሁሉ  ክፍሉ  ነው  በቀይ መሬት  ይኑር ፡፡

የሴት መድኃኒት  ያስፈራዋል ጠላቱ  እጅግ  ብዙ ነው  ወደ እግዚአብሔር ጸሎት  ያዘውትር  ምጽዋቱና  ጸሎቱ ይሰምርለታል  ደዌ ያስፈራዋል  ሴሰኛ ነው  ሲታመም  መድኃኒቱ ቀይና  ነጭ  የጥቁር ቡሃ በግ አርዶ  ሓሞቱን ይጠጣ  እሳትና ውሃ  ሙላት  አጥፊው ነውና ይጠንቀቅ እኩይ ወረኁ  ጥቅምት  በዘመነ  ማቴዎስ ሮብ ወይም ዓርብ  ቀን በጀምበር ግባት በ፹2 ዓመቱ ይሞታል ፡፡

           ሐመል ኮከብ ያላት ሴት የሆነች  እንደሆነ፡፡

እግረ  ወልሻሻ ዓይነ መልካም  ናት  በጥርሷ ምልክት አለባት  ወደመስራቅ ትሔዳለች  ፀጉረ መልካም  ደረቅ  ተቀያሚ   በልቧ ቂም ቋጣሪ  ናት መልኳ ደማም  ናት  ክንዷ ጥርሷ ፀጉሯ ያምራል  ወንዶች በፍቅር መኝታ ይወዷታል  ልጆች ትወልዳለች በኋላ ግን  ማህፀኗን ሾተላይ  ይመታታል በሥራዋ  ተመካሒ  ራሷን አኩሪ ናት ቅናትና  እብለት  ወረትም  አለባት  ሆዷን  ያማታል  ከ40 ዓመት  በኋላ  ሰውነቷ ይበርዳል  ተራክቦን  ትተዋለች  ወደምስራቅ አገር ብትቀመጥ  ይሻላታል  ዕድሜዋ ፸ ዘመን ነው ፡፡