ጀግናን መምከር ይቻላል?

ጀግናን መምከር ይቻላል?

ሸንቁጥ

ጀግናን መምከር ይቻላል?

ይሄ መልዕክት ለጀግኖቹ ነዉ::በተግባር እየተጋደሉ ላሉት:: ብዙ ጊዜ ጀግናን መምከር ከባድ ነዉ:: እንዴዉም አንዳንዴ የሚነሳዉ ጥያቄ ጀግናን መምከር ይቻላል? የሚል ነዉ:: ምክንያቱም ጀግና ጀግና ነዋ::ሞት አይፈራ::ልቡ ተራራ::እምነቱ ሙሉ::ድንጉጥ አይደል:: እርምጃዉ እንዳንበሳ::

ቢሆንም ጀግና ሲመከር ቢያደምጥ ደግሞ ጥበበኛ ይሆናልና ከዚህ በታች ያሉትን ነጥቦች ጀግኖች ቢያላምጧቸዉ ጥሩ ነዉ::በትግል ወቅት ነገሮች ድብልቅልቅ ይላሉ::እናም ንጹሁ ዉሃ እና መርዛማ ዉሃዉን በጥንቃቄ ማጥለል ይገባል::ጀግናና ቱሪናፋዉን መለዬት::ምናምንቴ እና እዉነተኛ የህዝብ ልጅን ለማበጠር ረዘም ያለ ጊዜ መዉሰድ ይገባል::በተለይም አሁን ሀገራችን እንደገባችበት ዘመን ሁሉ ትግሉ ባንዳ ሲበዛበት ነገሮች እየጠነከሩ ይሄዳሉ::…ማን እንዳስበላህ ሳታዉቅ እጎንህ ቁጭ ብሎ እንደ ወዳጅ ይሰልልሃል::እንደ ቁራ ድምጹን ከፍ አድርጎ ስለ ህዝብ እየጮህ በጎን ከጠላት ጋር ያንሾካሹካል::

እናም በማንኛዉም የትግል ሂደት ወቅት ከትግል ሁሉ መሰረታዊዉ መመሪያ የታጋዮች ደህንነት ጉዳይ ነዉና በዚህ ዙሪያ ከፈተኛ ስራ ሊሰራበት ይገባል::እናም ጀግኖች ሆይ በጠላት መረብ ዉስጥ ላለመያዝ የሚከተሉትን ነጥቦች በጥንቃቄ አጢኗቸዉ:-

1-ከወያኔ ንክኪዎች እራሳችሁን አርቃችሁ ጠብቁ::የወያኔ ንክኪዎች ለትግሉ ይጠቅማሉ ብላችሁ እንኳን ብታስቡ ከነዚህ አይነት ሰዎች ጋር መገናኘት ያለባችሁ በሶስተኛ እና አራተኛ ደረጃ ግንኙነት እንጅ እራሳችሁ አትገናኙ
2-ቶሎ ቶ አድራሻ እና የስልክ መሰመራችሁን ለዉጡ
3-ቢቻል ስልክ አትነጋገሩ::ከማንኛዉም ሰዉ ጋር ግንኙነታችሁ በሌላ ስልት ይሁን
3-እራሳችሁ ስረ መሰረቱን አጣርታችሁ የታጋዩን ማንነት በራሳችሁ የደህነት መስመር አስጠንታችሁ ካልሆነ ወደ እናንተ ቡድን አትቀላቅሉት::ወይም ወደ እርሱ ቡድን ሄዳችሁ አትቀላቀሉ
4-ከዉጭ ሀገር ስለሚመጣ አንዳንድ የድጋፍ እና የሀብት እገዛ ብላችሁ በዉጭ ሀገር ከተደራጁ እና ምንነታቸዉ በደንብ ካልተጣራ ሀይላት ጋር ግንኙነት አትፍጠሩ

5-የጅምላ ትግል የሚባል ነገር የለም::እንደ እንሰሳ ይሄ ነገዴ ነዉ ይሄ ጎሳዬ ነዉ እያላችሁ የጠላቶቻችሁ አራጆች እጅ እንዳትወድቁ በጥንቃቄ ተጓዙ::አስተዉሉ እያንዳንዱ የኢትዮጵያ ብሄረሰብ እየታረደ እና እየተገደለ ያለዉ ከአብራኩ በወጡ የጎሳዉ አባላት ነዉ::ስለዚህ በጅምላ ጎሳዬ ነዉ: የወንዜ ልጅ ነዉ የሚል አካሄድ ፈጽማችሁ ለደቂቃ እንዳታስቡት

6-መግለጫ እንድትሰጡ ቃለ መጠይቅ እናድርግላችሁ የሚላችሁን ሁሉ አትቅረቡ::በተለይም በዉጭ ሀገር ትግል ላይ ሳይሆን ንግድ ላይ ያተኮሩ ልዩ ልዩ ሀይሎች እንዳሉ በደንብ መገንዘብ ያስፈልጋል::

7-የወያኔ የስለለ አቅምን በቀላሉ አትመልከቱት::በማንኛዉም አቅጣጫ እንደሚመጣ አስተዉሉ::በሴት: በገንዘብ: በመረጃ ማወናበድ: ታጋይ በመምሰል: በሀሰተኛ ማንነት እና በልዩ ልዩ መንገድ ይመጣል

8-በተቻለ መጠን የታመኑት እና የተፈተኑት ታጋዮች ዙሪያ ብትሰባሰቡ መልካም ነዉ::ወይም እነዚሁኑ የታመኑ እና የተፈተኑ ታጋዮችን በናንተ ዙሪያ ማሰባሰብ ብትችሉ ጥሩ ነዉ

9-የስራ ክፍፍል ላይ በጥንቃቄ ብትሰሩ መልካም ነዉ::አንዱ ሰዉ ሁሉን ነገር ሊሆን አይችልም::የግንኙነቱንም:የድጋፍ ማሰባሰቡንም: የግንባር ተጋድሎዉንም: የህዝባዊ ቅስቀሳዉንም ስራ ሁሉ አንድ ሰዉ ሊሰራዉ አይችልም:: ይሄን የሚያደርግ ከሆነ በወያኔ እጅ የመዉደቅ እድሉ ሰፊ ነዉ::

10-ከስሜት የጸዳ እና በአዕምሮ የተቀመመ የትግል ስልት እና ስትራቴጅ ላይ አተኩሩ::ይሄን የትግል ስልትና እስትራቴጅ ሳትነድፉ በጅምላ ከተገኘዉ ጋር ሁሉ አትግበስበሱ::ኢትዮጵያ አሁን በዉጭም በዉስጥም በብዙ ጠላት የተወጠረች ሀገር ስለሆነች እናንተን እዉነተኛ ጀግኖቹን ሊያጠፉ የሚያደቡት ወያኔዎቹ ብቻ አይደሉም::የኢትዮጵያ ጠላቶች ሁሉ ናቸዉ::እናም ወያኔን ተቃዋሚ ነኝ እያለ የሮጠዉ ሁሉ የጠላቴ ጠላት በሚል ቀመር ወዳጃችሁ ሊሆን እንደማይችል በደንብ አስተዉሉ::

11-በወያኔ የተከፋ እና ወያኔን ያማ ሁሉ የወያኔ ጠላት ነዉ ብላችሁ አትመኑ::ዛሬ እድገት ተከለከልኩ ብሎ ወያኔን ሲያማ አድሮ በማግስቱ እድገት ሲያገኝ ወያኔ ሽህ አመት ይንገስ የሚለዉ ተከፋሁ ባይ እጅግ ብዙ ነዉ

12-ህዝባዊ አደራን ከዳር ለማድረስ እና ህዝብን ከፈጽሞ ባርነት ነጻ ለማዉጣት ጀግንነት በጥበብ መታሸቱ ቁልፍ ነዉ::ከጀመርከዉ ብኋላ ሁለት ልብ መሆን አይቻልም::ጀግናም ሁለት ልብ አይደልም እና በዚህ እረገድ ግማሹን የትግል መስመር ሄዶታል::ሆኖም የቀረዉ ግማሽ ጉዞ መንገዱን በመሄድ ሂደት ዉስጥ ያሉትን እዉነታዎች አንድ በአንድ ነቅሶ ቀድሞ ለማወቅ በሚደረገዉ ቅድመ ዝግጅት ላይ የተንተለጠለ ነዉ::