ድርጊቶችን ባግባቡ መግለጽ
| ጠላ ይጠመቃል | ገንፎ ይገነፋል |
| ጠጅ ይጣላል | አረም ይታረማል |
| አረቄ ይወጣል | ቅቤ ይነጠራል |
| እሸት ይጠረጠራል | ንፍሮ ይቀቀላል |
| ፈረስ ይጋልባል | ቆሎ ይቆላል |
| በቅሎ ይሰግራል | እንጀራ ይጋገራል |
| ስጋ ይቆረጣል ይዘለዘላል | ሎሚ ይመጠጣል |
| ዉሃ ይቀዳል | እንጨት ይፈለጣል ወይም ይሰበራል |
| አጥር ይታጠራል | በቆሎ ይጠበሳል ውይም ይቀቀላል |
| ድንጋይ ይካባል | ማሺላ ይቆረጣል |
| አብሲት ይጣላል | ጤፍ ይታጨዳል |
| ወጥ ይፈላል | ሸንኮራ አገዳ ወይም ጥንቅሽ ይመጠጣል |
| ሙቅ ይሞቃል | አልጋ ይነጠፋል |
| ነጋሪት ይጎሰማል | በገና ይደረደራል |
| ከበሮ ይመታል | ዳቦ ይደፋል |
