የድረሱልኝ ጥሪ: ከአወቀ አባተ ገበየሁ

የድረሱልኝ ጥሪ: ከአወቀ አባተ ገበየሁ
አወቀ አባተ ገበየሁ

የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጂት ( መኢአድ ) የአዲሥ አበባ የህዝብ ግንኙነት አላፊ የነበረው አወቀ አባተ በአረመኔው ወያኔ የአማራን ህዝብ ህዝባዊ እምቢተኝነት በመምራት እና በማሥተባበር በሚል ተከሥሶ በነ ንግሥት ይርጋ መዝገብ 4ኛ ተከሣሽ ነበረ።የካቲት ሰባት 2010/አም ከአፓርታይዱ አገዛዝ ከማጐሪያ ቤቱ ተለቋል። በማእከላዊ ማሰቃያ ቤት እያለ ከፍተኛ ኢሰባዊ ድርጊት ተፈፅሞበታል።ከዚህም መካከል አካላዊና ስነ አእምሮአዊ ጉዳት ተፈፅሞበታል። ከዚህም መካከል ለ4 ወር ሙሉ በጨለማ ቤት ውስጥ ለሊት ለሊት እየወሰዱ እጅግ ከፍተኛ ድብደባ ፈፅመውበታል።

እጅና እግሩን በማሰር ለ4ቀን ቶርቸር በመስቀል ባደረሱበት የአካል ጉዳትና በወቅቱ ተገቢውን ህክምና ባለማግኘቱ ለከፍተኛ ህመም ተጋልጧል። ከማዕከላዊ ወደ ቅሊንጦ ከወረደ ከብዙ ስቃይና እንግልት በኋላ ለጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ሪፈር ተፅፎለት ።ጥቁር አንበሳ ሆስፒታልም አስፈላጊውን ምርመራ ከአደረገለት በኋላ ሰርጀሪ(ኦፕራሲዎን )መደረግ አለበት በማለት ወረፋ እየጠበቀ ይገኛል።

ሆኖም ግን ከወህኒ ቤት መልሥ ችግሮቹ ላካፍላችሁ ግድ ይለኛን። ለሁላችንም ሡሪ አውሦ አትቀመጡበት ከሚል ዲሞክራት ሠውሮ የሚበጀውን ፈጣሪ ያድርግልን። ለሁሉም ነገር ተሥፋ አለን ግን በሥብዕናችን ባሞራላችን በማንነታችን ላይ ከመቀለዳቸው አልፎ በእያንዳዳችን ላይ ያደረሡብን በደል ቢያጥቡት የማይንጻ ቢቀቡት የማይሽር የህሊና ቁሥል አሣድረውበታል ። በእሥራት ወቅት የደበደቡት ያሠቃዩት ዛሬ ድረሥ መቀመጥ መጓዝ በሀይል መተንፈሥ አቅቶታል። ማለትም አሥረው የደበድቡት መቀመጫው ይደማል የእግሩ ታፋ ደም ቋጥሮ ለመራመድ ተቸግሯል። ወደ ህክምና ቢሄድም ወጩ ከአቅሙ በላይ ሆኖ ገንዘብ በማሠባሠብ ላይ እንገኛለን።


አወቀ አባተን ለመርዳት የምትፈልጉ የሚከተለዉን አድራሻ ተጠቀሙ::

ቀጥታ ሀገር ቤት በተከፈተለት አካዉንት ለመላክ የምትፈልጉ ወገኖች የባንክ አካዉንት 1000064362376 የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አየር ጤና ቅርንጫፍ።
ከአሜሪካን ሀገር ወይም ከሌሎች የምዕራብ ሀገራት እርዳታችሁን መለገስ የምትፈልጉ እና እርዳታዉ ተሰብስቦ እንዲላክ የምትፈልጉ ወገኖች ደግሞ በሚከተለዉ አድራሻ መላክ ትችላላችሁ::
Direct deposit:
Citibank:
Routing # 021000089
Acct # 4988664154Check: Mail to Zeni. (Please write cash on check)
85-19 164 street
Jamaica Hills, N.Y 11432
የእርዳታ እጃችሁን እንድትዘረጉለት በእግዚሀቤር ስም እንጠይቃለን።
የአወቀ አባተ ገበየሁ ስ/ቁ 251-966114319

ድል ዲሞክራሲና ፍትህ ለሚናፍቀዉ መላዉ የኢትዮጵያ ህዝብ !!!!!!