የደምሰው አየለ ግጥሞችና ሌሎች ቁምነገሮች

አትጠገብ ደምሰዉ

ሦስት አመት ሆነሽ፡፡

ሳላይሽ ያዬሁሽ፡-

በአይኖቼ ሳላይሽ

ድምፅሽን ሳልሰማሽ

በናትሽ ሆድ ሆነሽ

ማን አንቺን አሳይቶኝ፣ ማን አሰምቶኝ ነው አትጠገብ ያልኩሽ፣

ፈገግታሽ፣እርጋታሽ፣ሰላምታሽ፣ፊትና ቁመናሽ

እንዲያው በድምሙ ትርንፍሽ መሆንሽ

የማትጠገቢ ድንቅ ስጦታዬ ነሽ፣

ስሜ እንኳን ሳልጠግብሽ ፣

አይቼ ሳልጠግብሽ፣

ሁሌ እንደናፈቅሁሽ፣

ሶስት ወር አስቆጠርሁ አንችን ተለይቼሽ፣

አንችም ከተወለድሽ ሶስት አመት ሆነሽ፣ ልደትሽን አከበርሽ፡፡

ይታዬኛል ሌላ

የአዕምሮሽ ልዕልናሽ

የጥበብ ሥጦታሽ

የሰው ሁሉ ፍቅርን እያጎናፀፈሽ

ይታዬኛል ደሞ ሰው ሁሉ ሳይጠግብሽ

አትጠገብ ሲሉሽ፣ ትናገር ትምጣልን እያሉ ሲመኙሽ

በከፍታ ማማ፣ ጣሪያ ላይ ተቀምጠሽ

ጓደኛ፣ ዘመድሽ፣ ያለም ህዝቦች ሁሉ

ወደ ላይ ወደ አንቺ እየተመለከቱ አትጠገብ ሲሉ፣

አኔም፡-

 ለፈጠረኝ አምካል፣ ለፈጠረሽ አምላክ ለእናቱ ለድንግል፣ ለመላክና እና ለቅዱሳን ሁሉ የሉሄ በማለት

ምስጋና እያቀረብኩ ይታየኛል ያኔ ነብሴ ስትደሰት፡፡

ሰኔ 18 ቀን 2015 ዓ.ም

ለአትጠገብ በአባቷ ደምሰው ተፃፈ

XXXXXXXXXXXXXXXXXXXXXXXXXXXXXXXXXXXXXXXXXXXXXXXXXXXXXXXXXXXXXXXXXXXXXXXXXXXXXXXXXXX

ሞትን አሸነፉት፡፡

በጥበብ ተሞልተው የጥንት አባቶችህ

ሞት ጥላ ነው አሉህ

የሚሄድ ከጎንህ

ፍትሀት አልብሶህ

ሳትኖር እየኖርህ

ለሰከንድ ሳይረርቅህ

በህሌና ዳኛ እየኮረኮመህ

በህሉሌና ሆነህ ሰው ካልሆንኩ ስትል 

በስጋህ አቁሞህ፣ በፍርሃት ወደቅህ አሳነሰህ ከትል

ማነስህ ሳያንስህ፣ መፍራትህን እያወቅህ 

ሌላ ሞት ለመሞት እንዳልፈራ ሆነህ ደግመህ ትዋሻለህ፣

ሙት ሆነህ በቁምህ ለረጅም አመታት ስትሄድ ትኖራለህ፣

     አንዴ  ማርኳል እና እሱ እንደሁ አይምርህ

     በምድር ላይ አዋርዶህ፣

     በውሸትህ ብዛት ከሰማይ ቅዱሳን ለይቶህ፣ ነጥሎህ

     በድል ማማ ቆሞ ወደ ሲኦል ላከህ

ደሞ በሌላ ፅንፍ

ጀግኖቹ

የድል አጥቢያዎቹ

ያባቶችን ምክር ስንቅ አድራጊዎቹ

ሞት ጥላ እንደሆነ፣እንደነገሯቸው

እውነትን ፈለጉ ሞት እንዲገጥማቸው

እሱም አረመኔው መቼ ሊምራቸው

እውነትን በማፍቀር፣ ለእውነት በመፅናት አረፈ ስጋቸው

ግን፡-

ህዝብ አከበራቸው፣ህዝብ ጮኸላቸው አልሞቱም አላቸው

ከፍ አለ ነብሳቸው። በከፍታ ማማ ተቀምጠው አያቸው

የሰማይ መላዕክት እያሸበሸቡ ሲወስዷቸው አይቶ እንዳልሞቱ አውቀ ተበሳጨባቸው

 ለእውነት በመቆም፣ ወደ ሞት በመሄድ ሞትን አሸነፉት መሰከረላቸው