የዘንዶዉ መንፈስ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች መሃከል ሰላም እና አብሮ ማምለክ እንዳይኖር ለምን ፈለገ?

 የዘንዶዉ መንፈስ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች መሃከል ሰላም እና አብሮ ማምለክ እንዳይኖር ለምን ፈለገ? በለንደን የተከናወነዉን የዘንድሮዉን የትንሳዔ በዓል ገጽታ እንደማሳያ:-

-ዘንድሮም የትንሳዔ በአል በለንደን ክርስቲያኖች ዘንድ በልዩነት: ተኮራርፎ በማምለክ: እና አንድን ቤተክርስቲያን ከዚህ እስከዚህ ሰዓት እኛ ቀሪዉን እናንተ በሚል አሳዛኝ ሁኔታ እንዲያልፍ ተደርጓል::

-በሚያሳዝን መልኩም አንዱ ወገን አንዱ በፖሊስ ሀይል የጸሎት ስነስርአቱን ባልጨረሰበት ሁኔታ ሰዓቱ ደረሰ : ፍርድ ቤት የገደበላችሁ ሰዓት ይሄን ያህል ነዉ በመባባል በክርስቲያኖች መሃከል ሳይሆን በአህዛብ መሃከል የማይገባ ድርጊት እና ጥላቻ ሲራመድ ተስተዉሏል::

-ከዚህ ሁሉ የክርስቲያኖች መለያዬትና ጸብ ጀርባ ደግሞ በዘንዶዉ መንፈስ የሚመራዉ ሀይል ቆሟል:: አንዱን ወገን በመወገን : ቡድነኝነትን በማበረታታት: በአማኞች መሃከል ፖለቲካዊ ጥላቻን በመዝራት: እክርስቶስ ቤተክርስቲያን ዉስጥ የዲያቢሎስ ስራ የሆነዉ የዘር ቆጠራ እንዲገባ በማድረግ: ጳጳስ ሳይሞት ጳጳስ አይሾምም የሚለዉን የቤተክርስቲያኗን ህግ በመሻር: የቤተክርስቲያኗን ሲኖዶስ በመቆጣጠር እና ክርስቲያኖች እንዳይግባቡ በማድረግ የዘንዶዉ መንፈስ የተሳፈረባቸዉ ሀይሎች ሁሉንም ክፋትና ወንጀል በክርስቶስ ቤተክርስቲያን ላይ ፈጽመዉባታል::


-በኢትዮጵያዉያን ብሄረሰቦች መሃከል የተዘራዉ የጥላቻ መርዝ ያለ ምክንያት አይደለም:: ኢትዮጵያን ለማጥፋት እንጅ::ለምሳሌም በኦሮሞ እና በአማራ ማህበረሰብ መሃከል ወያኔ የሰነጠቀዉን የጥላቻ ስንጥቅ ለመድፈን አሁን ያሉት ፖለቲከኞች ሁሉ ካቅማቸዉ በላይ እስኪሆን ድረስ ወደ ሰማይ እንዲጉን አድርጎታል::በትግሬ እና በአማራ ህዝብ መሃከል አለመተማመን ፈጽሞ እንዲሰፍን ከበሮ ሲደልቅ የኖረዉ ወያኔ የቤት ስራዉ ተሳክቶለታል::በኦሮሞዎችና በሶማሌዎች መሃከል: በኦሮሞዎች እና በሲዳማዎች መካከል: በኦሮሞዎች እና በትግሬዎች መሃከል: በአኝዋክና በንዌር መሃከል: በሶማሌና በአፋር መሃከል እንዲሁም በብዙ ኢትዮጵያዉያን ማህበረሰቦች መሃከል ጥላቻ እና መለያዬትን በደንብ አድርጎ ወያኔ ዘርቷል::

-ይባስ ብሎም ሙስሊም ኢትዮጵያዉያን እና ክርስቲያን ኢትዮጵያዉያን አብረዉ እንዳይኖሩ ገና ስልጣን ላይ ሲፈናጠጥ ወያኔ በርካታ የጥላቻ ፕሮፖጋንዳዎችን ሰርቷል:: በጣም እጅግ በጣም የተሳካለት የልዩነት ስብከቶችን በደንብ አድርጎ በትዉልዱ ዉስጥ ረጭቷል::

-ኦርቶዶክ ተዋህዶ ፈጽሞ ትወድም ዘንድ አንዴ የአማራ ብቻ ነች: አንዴ የትግሬ ነች: አንዴ የጉራጌ መሸሸጊያ ነች እያለ ኦርቶዶክስ ኢትዮጵያዉያን የመጨረሻ እንዲጠላሉ እና እምነቷም እንድትጠፋ ሁሉንም ስራዎች ሰርቷል::አሁንም እየሰራ ነዉ::

– ዉጊያዉ መንፈሳዊ ነዉ::ኢትዮጵያ እምትባል ሀገር እንድትኖር የማይፈልገዉ ዘንዶዉ ነዉ:: በህዝባችን መሃከል ጥላቻ እንዲነግስ የሚታገለዉ ዘንዶዉ ዋና አላማዉ በምድር ላይ የእግዚአብሄር በአላት የማይታሰብበት: የእግዚአብሄር ምልክት የጠፋበት የአዳም ዘር ለመፍጠር ነዉ:: ወያኔን የተሳፈረዉ ርኩስ መንፈስ ይሄዉ የዘንዶዉ መንፈስ ነዉ::የዘንዶዉ መንፈስ ጥላቻ እና ልዩነት ዋናዉ መገለጫዉ ነዉ::

– እግዚአብሄር እቅዱ ግን ሌላ ነዉ:: የእግዚአብሄር እቅድ ግን የዘንዶ እራስን መቀጥቀጥ ለኢትዮጵያ ሰዎችም መንፈሳዊ ሀይልን ማልበስ (ይሄን ሲያመሰጥረዉም ምግብ መስጠት ይለዋል) ብሎም የእግዚአብሄር ምልክት እና መታሰቢያ ከአዳም ልጆች እንዳይጠፋ ኢትዮጵያን ምክንያት ማድረግ ነዉ:: ኢትዮጵያም ፈጽሞ አትጠፋም::የእግዚአብሄር ናትና:: በኢትዮጵያዉያን መሃከል ሁሉ የተዘራዉ ጥላቻ ይሻራል::
መዝሙር 74 ይሄን መንፈሳዊ ዉጊያ እንዲህ ይተርከዋል::

3. ጠላት በቅዱሳንህ ላይ እንደ ከፋ መጠን፥ ሁልጊዜም በትዕቢታቸው ላይ እጅህን አንሣ። 4. ጠላቶችህ በበዓል መካከል ተመኩ፤ የማያውቁትንም ምልክት ምልክታቸው አደረጉ። 5. እንደ ላይኛው መግቢያ ውስጥ በዱር እንዳሉም እንጨቶች፥ በመጥረቢያ በሮችዋን ሰበሩ። 6. እንዲሁ በመጥረቢያና በመዶሻ ሰበሩአት። 7. መቅደስህን በእሳት አቃጠሉ፤ የስምህንም ማደሪያ በምድር ውስጥ አረከሱ። 8. አንድ ሆነው በልባቸው በየሕዝባቸው። ኑ፥ የእግዚአብሔርን በዓሎች ከምድር እንሻር አሉ። 9. ምልክታችንን አናይም ከእንግዲህ ወዲህም ነቢይ የለም፤ እስከ መቼ እንዲኖር የሚያውቅ በኛ ዘንድ የለም። 10. አቤቱ፥ ጠላት እስከ መቼ ይሳደባል? ስምህን ጠላት ሁልጊዜ ያቃልላልን? 11. ቀኝህን በብብትህ መካከል፥ እጅህንም ፈጽመህ ለምን ትመልሳለህ? 12. እግዚአብሔር ግን ከዓለም አስቀድሞ ንጉሥ ነው፥ በምድርም መካከል መድኃኒትን አደረገ። 13. አንተ ባሕርን በኃይልህ አጸናሃት፤ አንተ የእባቦችን ራስ በውኃ ውስጥ ሰበርህ። 14. አንተም የዘንዶውን ራሶች ቀጠቀጥህ፤ ለኢትዮጵያ ሰዎችም ምግባቸውን ሰጠሃቸው።

እናም የእግዚአብሄር እቅድ የዘንዶ እራስን መቀጥቀጥ ለኢትዮጵያ ሰዎችም መንፈሳዊ ሀይልን ማልበስ (ይሄን ሲያመሰጥረዉም ምግብ መስጠት ይለዋል) ብሎም የእግዚአብሄር ምልክት እና መታሰቢያ ከአዳም ልጆች እንዳይጠፋ ኢትዮጵያን ምክንያት ማድረግ ነዉ:: ኢትዮጵያም ፈጽሞ አትጠፋም::የእግዚአብሄር ናትና::

ወደ ሮሜ ሰዎች
3፥22
እርሱም፥ ለሚያምኑ ሁሉ የሆነ፥ በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን የሚገኘው የእግዚአብሔር ጽድቅ ነው፤ ልዩነት የለምና፤

10፥12
በአይሁዳዊና በግሪክ ሰው መካከል ልዩነት የለምና፤ አንዱ ጌታ የሁሉ ጌታ ነውና፥ ለሚጠሩትም ሁሉ ባለ ጠጋ ነው፤
——–
በለንደን በዘንድሮ በዓል ላይ የተከሰተዉን አሳዛኝ የልዩነት ክስተት ለመመልከት ከዚህ በታች ያለዉን ቪዲዮ ይጫኑ

https://www.youtube.com/watch?v=-DYBP4OkHR4