የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጅና ታላቁ አርበኛ ጀነራል ጃጋማ ኬሎ ማረፋቸው ተሰማ

የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጅና ታላቁ አርበኛ ጀነራል ጃጋማ ኬሎ ማረፋቸው ተሰማ።
የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጅና ታላቁ አርበኛ ጀነራል ጃጋማ ኬሎ

የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጅና ታላቁ አርበኛ ጀነራል ጃጋማ ኬሎ ማረፋቸው ተሰማ ::ሃገራችን ኢትዮጵያ አስደናቂ ገድል የፈጸሙ ትልልቅ ሰዎች ፈልቀዉባታል። በነዚህ ጥቂት አስተዋይና ጀግና ሰዎች ድካምና መሰዋእትነት ነው ህዝቡዋ በዉርደት በባእዳን ከመገዛትና ማንነቱን ከመነጠቅ የዳነው። ከነዚህ ትዉልድ ለዘላለም ከሚያስታዉሳቸው ባለዉለታ አባቶቹ አንዱ ጀኔራል ጃጋማ ኬሎ ናቸው።

አይበገሬዉና ባለግርማ ሞገሱ ጃጋማ ኪሎ የኢትዮጵያ ህዝብ በአንድነትና በነጻነት እንዲኖር ከፍተኛ አስተዋጽኦ አድርገዋል። ኢትዮጵዉያን የጀኔራል ጃጋማ ኬሎን አኩሪ የጀግንነት ስራና ዉለታ ለዘለአልም ሲዘክሩት ይኖራሉ።

በወጣትነት ዘመናቸው በርሃ ለብርሃ የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጅና ታላቁ አርበኛ ጀነራል ጃጋማ ኬሎ ማረፋቸው ተሰማ።በመንከራተት አቅማቸው ከደከመም በሁዋላ የህዝባችን አንድነት እንዳይሸረሸር በመምከርና በማስተማር የወያኔ የዘር ፖለቲካን ያረገቡና አቅም ያሳጡ የአማራዉና የኦሮሞው አንድነት መሰረቱ እንዳይናጋ የጠላቶቻችንን ምኞት እንዲተን ያረጉ የጦር ሜዳ ጀግና ብቻ ሳይሆኑ የኢትዮጵያ ህዝብ አንድነት ምልክታችንም ጭምር ናቸው።

ለዉድ ቤተሰባቸውና ለመላዉ የኢትዮጵያ ህዝብ መጽናናትንና ጥንካሬን ይስጥልን። የጀግና ስም ከመቃብር በላይነው:: የአባታችንን ነፍስ በገነት ያኑርልን። አሜን!!