የአድዋ ጦርነትና የኢትዮጵያዉያን ድል

The videos above present the History and the Victory of Ethiopia at Adwa: የአድዋ ጦርነት ታሪክና የኢትዮጵያዉያን ድል: The epic war was waged between Ethiopia and Italy on 01 March 1896 which ended with defeating the Italian army in the Northern part of Ethiopia. The cause of the war was the invasions of Italy against the sovereign State of Ethiopia to impose its colonial rule.

Ethiopians and other peace loving Community members Celebrated the 124 Anniversary of this historic date at the Kentish Town Congregational Church in London on 07 March 2020. The Event was organised by Moresh Amhara Wegene and the Amhara Association in the UK. The History and legacy of the Victory of Ethiopia at the Battle of Adwa has thought an important lesson for the peace loving International Community that Independent Nations can defend themselves from external aggressive dictator led Countries.

The victory of Ethiopia led by the courageous Emperor Menelik against the unjust war of Fascist Italy has been inspiring enslaved African and Asian people all over the world since 01 March 1896. Today the first independent Flag of Ethiopia is considered to be a symbol of freedom and justice across the globe. Happy Victory Day for Ethiopians, Africans and for All Peace Loving International Community. Click here to watch Amazing related Video https://www.youtube.com/watch?v=qylye…

የአድዋ ጦርነትና የኢትዮጵያዉያን ድል 

የካቲት 23 ቀን የቅዱስ ጊዮርጊስ ለት በ1888 ዓ.ም (እደ ኤሮፓ አቆጣጠር ማርች 1 ቀን 1896 ዓ.ም) የዓለምን የፖለቲካ አቅጣጭና በዘር ላይ የተመሰረተዉን ኢሰብአዊ ግንኙንት የለወጠ የፍትህና የመከላከል ጦርነት ኢትዮጵያ ዉስጥ አድዋ በሚባለው ቦታ ላይ ተካሄደ። ጦርነቱ የተካሄደው በእብሪት ከኤሮጳ ባህር ኣቁአርጦ በመጣው የኢጣሊያ ጦርና ዓለም ከተፈጠረች ጀምሮ ሀግሩ ዉስጥ በሚኖረው የኢትዮጵያ ህዝብ መካከል ነበር።

ኢትዮጵያዉያን በጀግናና በብልህ ንጉሳቸው በዳግማዊ ምኒልክ ስር ተሰባስበው ዘመናዊ መሳሪያ ታጥቆ የመጣዉን ወራሪ ጦር ቅስሙን በመስበር የሃገራችውን ነጻነት አስከብረው መላው በባእድ አገዛዝ ስር የሚማቅቀው የአለም ህዝብ ተስፋ እንዲኖረው አድርገዋል:: ዳግማዊ ምኒልክ ኢትዮጵያ እንድታድግና ዜጎች እንዲጠቀሙ አስደናቂ የልማት ስራወችን በማከናወን ህዝቡ በሰላምና በስርአት እንዲኖር ኣድርገዋል። በሌላ በኩል በጠላትና በደጋፊዎቹ ጸረ ሰላም እና ጸረ እኩልነት ሃይሎች ጎራ ከፍተኛ ድንቃጤን ከመፍጠሩም በላይ አንዳንዶቹም ቂም ከመያዝ አልፈው በረቀቀ መንገድ ሀዝቡን በመከፋፈል ለመጉዳት ከፍተኛ ተንኮል ሸረቡ:: የሁለተኛዉን የዓለም ጦርነት ኣጋጣሚ በመጠቀም በድጋሚ ወረራ አካሂደው አሰቃቂ የሆነ ኢሰብአዊ ድርጊት ፈጸሙ። ከዚያ ወዲህ ያለው ትዉልድ ታሪኩን እንዳያዉቅና እንዳይጠነቀቅ የዉሸት ጽሁፎችን በሀገር ዉስጥና በዉጭ ሃገር ሰዎች በማጻፍና በመበተን እልሀቸዉን በረቀቀ ስልት መወጣት እንድሚፈልጉ አሁን ያለዉን የኢትዮጵያ ሁኔታ በጽሞና ለሚከታትል ስዉር ሊሆንበት አይችልም። እነዚህ ሁለት የእብሪት ዎረራወች ታሪክ እራሱን ይደግማል የሚለዉን እንዳንረሳ ማስጠንቀቂያ ናቸዉ።

ለዚህ ነው ታሪክን መማርና ማወቅ ያለብን በተገኘው ድል ለመኩራራትና ለመጠቀም ብቻ ሳይሆን ታሪክ እራሱን መድገሙ ስለማይቀር ለመዘጋጀትም ጭምር ነው:: በዚህ በብዙ ሺህ የኢትዮጵያዉያን መሰዋእትነት በተገኘው ድል ኢትዮጵያ አለኝታና ተስፋ ከመሆን አልፋ ለአፍሪካና ለሌሎች በባርነት ቀንበር ስር ለሚማቅቁ ህዝቦች የበኩሉዋን ድርሻ አበርክታለች። በዚህ የተንሳ ብዙ ሃገሮች ነጻ ሲወጡ የሰንደቅ አላማዋን ህብረ ቀለም ይወስዳሉ:: ጣሊያኖች በድጋሜ ኢትዮጵያን በወረሩበት ወቅት የኢትዮጵያኖችን ስነልቦናና ክብር ለመንካት ሰንደቅ አላማዋችንን ከተሰቀለበት ቦታ እያወረዱ ይረግጡት እንደነበረ በታሪክ ይታወቃል። ምንም እንኩአን የኢትዮጵያ ህዝብ ባይቀበላቸዉም ዛሬ የባንዳ ልጆች (ወያኔወች) ፋሽስቶች ካደረጉት ለወጥ አድርገው አባቶቻችን ተሰዉተው ያስረከቡንን ህጋዊና ታሪካዊ ሰንደቅ አላማችንን ባእድ አካል እመሃል ላይ በመለጠፍ የኢትዮጵያ ህዝ እዉቅና ያልሰጠዉን ባንዲራ በመስቀል ተደብቆ የቆየዉን ጸረ ኢትዮጵያ ድርጊታቸዉን በዉስጥ አርበኝነት በመፈጸም የህዝቡን ስነ ልቦና ከመጉዳትም አልፈው የዲሞክራሲያዊ መብቱን በመንፈግና ነፍሰገዳዮችን በማሰማራት ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ረገጣን በማካሀድ ላይ ናቸዉ።

በዚህ የተነሳ መልካቸዉን ቀይረዉ በመጡት የዉስጥ ከሃዲወችና በነጻነት ወዳዱ ሰፊዉ የኢትዮጵያ ህዝብ መካከል በአሁኑ ሰአት የከረረ ትግል በመካሄድ ላይ ነው። የአድዋን ድል ኢትዮጵያዉያን ይደግሙታል:: ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!! አመሰግናለሁ!!

ፉከራ

ፉከራ በተግባር (በዉጊያ) ላይ ሆኖ ስለሚፎከር ባብዛኛው በስድ ግጥም ይገለጣል።

ዱብ ዱብ ባይ እንደበረዶ

በልጅነቱ በርሃ ለምዶ

ይምጡባይ ይሰብሰቡ ባይ

ሲሰበሰቡ አንገዋሎ ጣይ

ሽለላ

ሽለላ ኧረ በለው በለው ኣስኪደው በዋንዛ

በናት ሃገርና በሚስት የለም ዋዛ

ተው ተመለስ እሱ ነው ድንበሩ

የጀግኖች መኖሪያ አይነካም በሩ

የሐዘን ግጥሞች

የወንድ ልጅ እናት ታጠቂ በገመድ

ልጅሽን አሞራ እንጂ አይቀብረው ዘመድ

የበልጂጉን የጦር መሳሪያ ምዩዚዩም ተንቀሳቃሽ ምስል ለማየት ከታች ያለዉን መገናኛዉ ይጠቁሙ https://www.youtube.com/watch?v=qylye…