የአማራዉን የወደፊት ራእይና የትግል ስልት በሚመለከት የቤተዓማራ ኢትዮጵያ አቁዋምና አቅጣጫ

የአማራዉን የወደፊት ራእይና የትግል ስልት በሚመለከት የቤተዓማራ ኢትዮጵያ አቁዋምና አቅጣጫ

የአማራዉን የወደፊት ራእይና የትግል ስልት በሚመለከት የቤተዓማራ ኢትዮጵያ አቁዋምና አቅጣጫ

በ”ቤተዓምሃራ ኢትዮጵያ (BeteAmhara Ethiopia)” ገጽ ላይ ብዙ ጊዜዓማራው በጀመሪያ መደራጀትና እራሱን መከላከል እንዳለበት ቁልጭ ተደርጎ ተገልጾአል። አይደራጅ የሚሉትም ሆኑ ይደራጅ ግን ይገንጠል የሚሉት ሁለቱም የወያኔና የኦነግ ጸረ ኢትዮጵያ ግርፎች ናቸው። ምክንያቱም ሁለቱም ዓማራዉን የሚያዋርዱ ብቻ ሳይሆን ሁሉንም ኢትዮጵያዉያን ሰላም እንዲያጡ በተንኮል ላይ የተዋቀሩ ሃሳቦች ስለሆኑ ነው።

ድርጅት ራእይ ያስፈልገዋል። ራእዩን ከግብ የሚያደርስ ስልትና ዘዴ ደግሞ መቀመር አለበት። ለምን አንዳንድ ሰዎች መልሰው መልሰው ስለመድራጀት እንድሚያወሩና ሰዉን እንደሚያሰለቹ አላዉቅም። ዓማራ መደራጀት አለበት። እየተደራጀም ነው። መደራጀቱንም ማንም ምድራዊ ሃይል ሊያቆመው አይችልም።

አማራ የሚደራጀው ራሱ ሃገሩን ያካፈላቸዉና ያስተማራቸው ዘረኞች ግፍ ስለፈጸሙበት ብቻ ሳይሆን የተነጠቀዉን ሃገሩን ለማስመለስና ሁለተኛ ኢትዮጵያ ዉስጥ ንጹሃን ወገኖቹ በማንኛዉም ዉስጣዊም ሆነ በዉጭ ሃይል ግፍ እንዳይፈጸምባቸዉ ጠንካራ የአባቶቹን አስተዳደር ከዘመናዊ አሰራር ጋር አጣጥሞ ለመዝርጋት ነው። አንዳንድ የበግ ለምድ የለበሱ ተኩላዎች እንደሚሉት ከኢትዮጵያ ከሃገሩ ጋር ሊዋጋና ተገንጥሎ ለወያኔና ለኦነግ ኢትዮጵያን ጥሎ ስደት ለመሄድ አይደለም። እንደ አናሳ መድረሻ ቢስ ጎሳ በገዛ ሃገሩ ራሱን ዝቅ አያደርግም።

በቁጥርም ሆነ ኢትዮጵያንም በማስተዳደር ዐማራ የታላቆች ታላቅ ነው። ከአማራው የተወለዱና ለሱ የሚቆረቆሩ (እሱን የሚከተሉ) በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰላማዊ ዜጎችም በመላው ኢትዮጵያ ዉስጥ እንዳሉ መዘንጋት የለብንም። እንገነጠላለን የሚሉ ካሉ ግን ከየት እስከ የት እንደሚገነጠሉ ካወቁ ይሞክሩት።

ዓማራው የሚታገለው የአባቶቹን ሃገር ኢትዮጵያን ሊከስና የራሱን ክብር አዉልቆ ለመጣል አይደለም:: ስለዚህ እነ ተንኮሉ እንደሚያወናብዱት ዓማራ የሚታገለው ከሃገሩ ከኢትዮጵያ (ከመሬቱ) ጋር ሳይሆን እሰራዉ ቤት ዉስጥ ገብተው ወንጀል ከፈጸሙት ከወያኔና ከሌሎች መሰል አናሳ ዘረኞች ጋር ነው።

https://www.facebook.com/groups/1671005363174915/?ref=bookmarks