የአማራዉን የረጅም ጊዜ ደህንነትና ጥቅም የሚያስጠብቅ ፖሊሲ እና አቅጣጫ ዝም ተብሎ የሚለፈፍ ጉዳይ አይደለም

 

 

 

 

የአማራዉን የረጅም ጊዜ ደህንነትና ጥቅም የሚያስጠብቅ ፖሊሲ እና አቅጣጫ ዝም ተብሎ የሚለፈፍ ጉዳይ አይደለም

የአማራዉን የረጅም ጊዜ ደህንነትና ጥቅም  የሚያስጠብቅ ፖሊሲ እና አቅጣጫ ዝም ተብሎ የሚለፈፍ ጉዳይ አይደለም ።

መለከ ሃራንና አንዳንድ መሰል ተከታዮቹን በሚመለከት ስጋት አለኝ። መጀመሪ ፖስት ሲያደርግ የአማራዉን ብሶት በደንብ የገለጸና አማራዉን ማደራጀት ያስፈልጋል ብሎ ሌሎች አማራዉን ለማዳን ከተነሱ ሰዎች ጋር አንድ አይነት አመለካከት ያለው መስሎ ስለታየን የአንድንዶቻችንን ቀልብ ስቦ ነበር። ነገር ግን ብዙም ሳይቆይ የአማራዉን ታሪክ የአገዉና ኤርትራ ድረስ የሚገኙ የሌሎች ነገዶች አድርጎ በመጻፍ ከፍተኛ ዉዥንብር ለመንዛት ሲሞክር ታይቶአል።

ይህም ብቻ አይደለም የአማራ ጠላት ኢትዮጵያ ናት! አማራው ኢትዮጵያን ካላጠፋና ካልተገነጠለ ነጻ አይወጣም በማለት ያለማፈር ጽፎአል። ይህ አደገኛ በመሰሪነት ወይም በየዋህነት ላይ የተመሰርተ ጸረ አማራና ጸረ ኢትዮጵያ ተንኮል በተለይ ዓማራው በከፍተኛ ጥንቃቄ ማየት ያለበት ጉዳይ ነው። ምክንያቱም የአማራዉን የረጅም ጊዜ ደህንነትና ጥቅም ከፍተኛ አደጋ ላይ የሚጥል ብዙ ዉስብስብ ነገሮችን የያዘ ጉዳይ ስለሆነ ፖሊሲ እና አቅጣጫ ዝም ተብሎ የሚለፈፍ ጉዳይ አይደለም።

አማራዉና ኢትዮጵያ አይገነጣጠሉም ምክን ያቱም ሃገሩን ኢትዮጵ ብሎ ካባቱ በተሰጠው ስጦታ የሰየመው የአማሮች አባት (የዐማርኛን ወይም የግእዝ ፊደልን የቀረጸው) ኢትኤል ነው። ስለዚህ የአማራ ሃገሩ “ኢትዮጵያ” ናት። ዓማራ የኢትዮጵያ ባለቤት እንጅ እንግዳ አይደለም። ምናልባት ወያኔ ኢትዮጵያ ዉስጥ የነዛው ፕሮፓጋንዳ ባለማወቅ ኢትዮጵያ የሌላ ነገድ አጽመርስት መስላ ለነ መለከ ከታየቻቸው ስላልሆነ ታሪክን መማር አለባቸው።

በታሪክም ብቻ ሳይሆን በተጨባጭ ዛሬ አማራው ከሁሉም ነገዶች በላይ ከፍተኛውን ቁጥር ይዞ ይገኛል። ከአማራና ከሌሎች ነገዶች የተዋለዱ ከአጠቃላይ የህዝቡ ቁጥር ሲሶዉን ይይዛሉ። እነ መለከ አማራውን እንገነጥላለን ሲሉ ኢትዮጵያዊ እውቅናውን ሁሉ በመግፈፍ ትዉልዱ ሁሉ አቅጣጫ በሌለው መንገድ እንዴሄድና ሌሎች ጸረ ኢትዮጵያን እጃቸው አስገብተው ታሪኩን ባህሉንና ማንነቱን እንደተመኙት ለማጥፋት ነው። እንዲያዉም አማራው በእዉነተኛና በሚታየው ጠላቱ በወያኔ ላይ እንዳይነሳ አቅጣጫ በማስለወጥ ራሱን በራሱ እንዲያጠፋ የተነደፈ አደገኛ የወያኔ የሻቢያና የኦነግ የትግል አካል ነው።

ዓማራ ሃገሩ እነ ባሌን አርሲን ሁሉ ይጨምራል። ዐማራ ትልቅ ነው። አማራ በመጽሃፍ ቅዱስ ሳይቀር ታሪኩ የተጻው በሃገሩ በኢትዮጵያ ስም ነው (ፊደሉም ማነነቱን በትክክል ይገልጸዋል)። የአማራው የወደፊት ደህንነቱና ጥቅሙ የሚጠበቀው ኢትዮጵያ ሃገሩ መሆኑዋን ተገንዝቦ እጁ ዉስጥ እንደገና በማስገባት እራሱንንና ሌሎች አብረው መኖር የሚፈልጉ ወንድሞቹን እንደታላቅነቱ በሰላም መምራት ሲችል ብቻ ነው።

ሌላው ጥያቄ “አንዳንድ ብሄረሰቦች ቢገነጠሉስ?” የሚል ነው። አማራው አብሮ ለመኖር ካሁን በሁዋላ ጥቅሙንና ደህንነቱን የሚጠብቅ ጠንካራ ድርጅት መመስረት አለበት። ባለፈው አይነት አንድነትም አይተበተብም:: ለዚህም እንደ አሁኑና እንዳለፈው ግዜ ማንም ተነስቶ እንዳይጨፈጭፈው ነቅቶ የሚጠብቅ ትዉልድ መቅረጽ አለበት። ምክንያቱም የአማራዉን ረጅም ጊዜ ደህንነትና ጥቅም ከፍተኛ አደጋ ላይ የሚጥል ብዙ ዉስብስብ ነገሮችን የያዘ ጉዳይ ስለሆነ ፖሊሲ እና አቅጣጫ ዝም ተብሎ የሚለፈፍ ጉዳይ አይደለም። ከዚያ ዉጭ አንዳንድ ነገዶች ለመገንጠል ቢፈልጉ እንኩዋን አማራው የቃል ኪዳን ሃገሩን “ኢትዮጵያን” አይለቅም። ጠላቶቹ ሲያልሙ ይኑሩ እንጂ የአባቶቹን ሃገር የታሪክ ማህደሩን ማንነቱን ክብሩንና ማእረጉን ለማንም በትኖ ባይተዋር አይሆንም!:

በበለጠ ለመረዳት “ቤተዓማራ  ኢትዮጵያን” ይጎብኙ!

በእዉቀት ዓለሙ