የመኢአድ ፕሬዝዳንት የሆኑትን የአቶ ማሙሸት ዓማረን መፈታት አስመልክቶ ከደጋፊወቹ የተሰጠ ማሳሰቢያ

የመኢአድ ፕሬዝዳንት የሆኑትን የአቶ ማሙሸት ዓማረን መፈታት አስመልክቶ ከደጋፊወቹ የተሰጠ ማሳሰቢያ

 

ለመኢአድ ቤተሰቦችና ደጋፊዎች በሙሉ:

የመኢአድ ፕሬዝዳንት የሆኑትን የአቶ ማሙሸት ዓማረን መፈታት አስመልክቶ ከደጋፊወቹ የተሰጠ ማሳሰቢያ
ህጋዊዉ የመኢአድ ፕሬዝዳንት አቶ ማሙሸት ዓማረ

በቅድሚያ የመኢአድ አመራሮች፤ በተለይም ፕሬዘዳንታችን አቶ ማሙሸት አማረ በመፈታቱ እንክዋን ደስ አላችሁ እያልን፤ እሱንም በደህና ከመላው ቤተስቦችህ ጋር ተቀላቀልክ እንላለን።

የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅትን ከተመሠረተ ጊዜ ጀምሮ፤ ከአሥራ ሶሥት  ዓመታት በላይ፤ ድርጅቱ የቆመለትን ዓላማ ላማራመድ በተለያየ መልኩ ያላሰለስ ጥረት አድርጋችኋል። ድርጅቱም ምንም እንክዋን ከተለያዩ አቅጣጫዎች ከፍተኛ ለህሊና የሚከብድ ጥቃትና የጥፋት ዘመቻ ቢፈጸምበትም በቆራጥ አመራሮቹና በአባላቱ ከፍተኛ መሥዋእትነት አሁን ያለንበት ደረጃ ደርሰናል። መኢአድ ህብረ ብሄራዊ ድርጅት ሲሆን በመላው ሀገሪቱ በመዋቅር የተዘረጋና በኢትዮጵያ ሕዝብ የታቀፈ ነው። ዘረኛው መንግሥት የመወገዱ ሂደት የመጨረሻው ሰዓት ላይ ነው። ሀይላችንን አጠናክረን ወደፊት መግፋት አለብን። ቆራጥና በእሳት የተፈተኑ የመኢአድ መሪዎች ስላሉ የኢትዮጵያ ትንሣኤ ከተባበርን በቅርቡ እውን ይሆናል።

እንደሚታወቀው የትግራይ ነፃ አውጭ ግንባር መኢአድን ጨርሶ የሚያጠፋው መስሎት ጠቅላላ አመራሩን ለእስር ዳርጎአል። በትናንትናው ዕለት ከድርጅቱ መሥራቾች አንዱና የአሁኑ በጠቅላላው አባላት የተመረጡት ፕሬዘዳንት አቶ ማሙሸት አማረ ከሥር ተፈተዋል። የቀሩትም የአመራር አባላት በቅርቡ ተፈተው ድርጅቱ የቆመለትን ዓላማ ለማራመድ ትግሉን በኅይል እንዲያቆሙ ከተገደዱበት ጊዜ አንስቶ የተቅዋረጠውን እንቅስቃሴ ለማስቀጥል እንደሚሠሩ በተደጋጋሚ አረጋግጠውልናል።

ስለሆነም የድጋፍ ማህበራችን ከሥር ለተፈቱትም ሆነ በቅርቡ ለሚያድርጉት የፓለቲካ እንቅስቃሴ የገንዘብም ሆነ የቁሳቁስ ድጋፍ እንድናደርግ ይጠበቅብናል። ስለሆነም አቅማችሁ የሚችለውን የገንዘብ  እርዳታ እንድታደርጉ ከአደራ ጭምር እንጥይቃለን። ይኅንንም እርዳታ ለወ/ሮ ዘነበወርቅ በሚከተሉት ዲፓዚት አካውንትና ወይም ቼክ ከሆነ በሚከተለው የፓስታ አድራሻ  ላኩልን።

በዚህ ኢሜል ያልተካተቱና እናንተ ለምታውቅዋቸው ደጋፊዎች ሁሉ ይኅንን ጥሪ በማስተላለፍ ረገድ እንድትተባበሩን በትህትና እንጠይቃለን።

Please go to Ethiopia.org and read about Mamushet.

Direct deposit:

Citibank:

Routing # 021000089

Acct #       4988664154

Check:  Mail to Zeni. (Please write cash on check)

85-19 164 street

Jamaica Hills, N.Y 11432

Long live AEUP, long live Ethiopia

Seleshi