ዚአከ ለዚአየ ዚአየ ለዚአከ

ዚአከ ለዚአየ፤ ዚአየ ለዚአከ (አንተ ለኔ እኔ ለአንተ)

ካነበብኳቸው ስለ አብሮነት ጠቀሜታ የሚያወሱ ፅሁፎች ምርጡን እና አስተማሪውን ታሪክ ላካፍላቹ፡ አንድ ንጉስ ገንፎ የመብላት ፈተና አዘጋጀ። ገንፎውን መብላት የሚቻለው ሁለት ሆኖ ነበር። ለመመገቢያነት የተሰጡት የእንጨት ማንኪያዎችም በጣም ረጃጅሞች ነበሩ። መጨበጥ የሚቻለው ደግሞ ከማንኪያዎቹ እጀታ ጫፍ ላይ ብቻ ነበር። ብዙ ተወዳዳሪ ለመሸለም ሁለት ሁለት እየሆነ ቢሞክርም መጉረስ ቀርቶ ማንኪያውን አፉ ማስጠጋት የቻለ አልነበረም። በመጨረሻ ሁለት የቅኔ ተማሪዎች ቀርበው እንዲህ ተባባሉ፡ ፊት ለፊት ተራርቀው ተቀምጠው፡ “ዚአከ ለዚአየ፡ ዚአየ ለዚአከ” ትርጉሙም ” አንተ ለእኔ፡ እኔ ላንተ” ተባብለው እየተጎራረሱ በልተው አሸንፈው ተሸለሙ።
አበቃሁ።
ልብ ያለው ልብ ይበል።
ምንጭ፡ አንጋረ ምሳሌ ዘግእዝ
በአፈወርቅ ታረቀኝ