ዘራፊዉና ወንጀለኛው ጸረ አምሃራ (አብቁተ) ድርጅት

የአማራ ብድር እና ቁጠባ ተቋም (አብቁተ) :- በባለሞያዎች ኮድ “ዘራፊዉና ወንጀለኛዉ ተቋም” የሚል ልዩ ስም እንዳለዉ ያዉቃሉ ?
ሸንቁጥ አየለ
 አብቁተ (የአማራ ብድር እና ቁጠባ ተቋም) በአለም ላይ የሌለ ዘራፊ እና ወንጀለኛ ድርጅት ነዉ ::ይሄን የኮድ ስም ያወጡለት ባለሞያዎች ናቸዉ :: ባለሞያዎች ለምን “ዘራፊዉና ወንጀለኛዉ ተቋም” የሚል ስም እንዳወጡለት የተወሰነዉን የታሪክ ክፍል አብረን እንቃኝ::

-ለአርሶአደር በ18% ወለድ በግዳጅ ብድር የሚያበድር ነዉ:: ይሄም በአለም ላይ ታይቶም ተሰምቶም የማይታወቅ ወለድ ነዉ:: ለምሳሌ “OUTREACH SERVICES AND SUSTAINABILITY: THE CASE OF AMHARA CREDIT AND SAVING INSTITUTION BY: FEKADU YEHUWALASHET; ADDIS ABABA UNIVERSITY COLLEGE OF MANAGEMENT, INFORMATICS AND ECONOMIC SCIENCE MASTER OF BUSINESS ADMINISTRATION” የሚለዉ ጥናት እንደሚተነትነዉ “The interest rate charged by ACSI on loan is 18% for both installment and term loans which is somewhat higher than the interest rate of banks (11.5%, CBE)””

-ይሄ ጥናት ብቻ ሳይሆን በርካታ ጥናቶች አብቁተ የሚያበድርበት የ18% ወለድ ዘረፋም ወንጀልም ነዉ::የመክፈል አቅም ለሌለዉ አርሶ አደር ይሄን ያህል ወለድ መቆለል ገበሬዉን ወደ ድህነት አዘቅት መግፋት ነዉ ብለዉ ቢከራከሩም ክልሉን የሚገዙት ሰዎች ጥላቻ በተሞላዉ ልባቸዉ ስለህዝቡ የሚናገሩ ባለሞያዎችን እያሳደዱ ማጥፋት ዋናዉ ስራቸዉ ነዉ::

-በአለም ላይ አንድ የወለድ መጠን ከ10-15% ሲደርስ ህዝብ አመጽ ይወጣል::በበርካታ ሀገራት ወለድ በአማካይ ከ 1% እስከ 5% ነዉ:: አብቁተ ግን ከአማራ አርሶ አደር 18% ያለ ይሉኝታ ይዘርፋል:: ገበሬዉ መክፈል ሲያቅተዉ ይደበደባል:ይታሰራል: ቀዬዉን ለቆ ይሰደዳል::

– ይሄ ብቻ አይደለም ያለዉን ንብረት በሙሉ ሸጦ እንዲሰጥ ይደረጋል::ከዚያም በዉርደት ቤቱ እንዲፈርስ ይደረጋል:: መከረኛ የአማራ አርሶ አደር ወዴት ይሄዳል? ደቡብ ቢሄድ በጥይት እንደ ዝንጅሮ ያባርሩታል::ወደ ኦሮሚያ ቢገባ አገርህ አይደለም ይሉታል:: ወደ ሱማሌ ቢሰደድ ወይም ወደ አፋር ቢሰደድ ታምራት ላይኔ እንዳደረገዉ አማራን አሳዳችሁ ግደሉ ብለዉ የወያኔ ባለስልጣናት አዋጅ ያሳዉጁበታል::

– በጣም አሳዛኙ ታሪክ ደግሞ አርሶ አደሩ ብድር እንዲወስድ የሚደረገዉ በግዳጅ እና ላላቀደዉ አላማ ሊያዉለዉ በሚችልበት ሁኔታ ዉስጥ ሳለ ነዉ:: ለምሳሌ የአንድ አመት (የዛሬ ሁለት አመት መሆኑ ነዉ) የብአዴን ሪፖርት እንደሚተነትነዉ በክልልሉ ሰላሳ አንድ ሽህ አነስተኛና ጥቃቅን ማህበራት ተቋቋሙ ተብሎ ከበሮ ከተመታ ብኋላ በአመቱ ሰላሳ ሽህ የሚሆኑት የአነስተኛ እና ጥቃቅን ተቋማት ፈረሱ ተብሎ በራሱ በገዥዉ ሚዲያ ለህዝብ ሪፖርት ቀርቧል::

-እንግዲህ በግዳጅ እንዲበደሩ የተደረጉት ሰላሳ አንድ ሽህ ማህበራት ፈርሰዋል ማለት ነዉ:: የተበደሩት ብድር ግን አባላት ላይ ያናጥርባቸዋል::እያንዳንዱ አባል ታንቆ ይመልሳል:: ይሄ እንግዲህ ተደራጁ : ስራ ፈጠሩ እየተባለዉ የሚለፈፈዉ ብቻ ነዉ::

-ከዚህ ዉጭ ግን በክልሉ ያለዉ እያንዳንዱ አርሶ አደር ደግሞ እንደ ግለሰብ ብድር በግዳጅ እንዲወስድ ይደረጋል:: የሚወሰደዉን ብድር ምንም ሳይሰራበት ከ18% ወለድ ጋር በግዳጅ እንዲመልስ ይታሰራል:ይደበደባል:ይሳደዳል : በመጨረሻም ቤቱ እንዲፈርስ እና ከርታታ ለማኝ እንዲሆን ይደረጋል:: አብቁተ ዘራፊ ድርጅት ብቻ ሳይሆን ወንጀለኛ ድርጅት ነዉ የሚሉት ባለሞያዎች ለዚህ ነዉ::

-አንድ ምሳሌ ለማከል የአብቁተ የወልድ መጠን ወንጀልም ገፈፋም ነዉ ሲሉ በአማራ ምርምር ማዕከል ስር የሚተዳደሩ በርካታ ተመራማሪዎች ጥናት ለክልሉ ባለስልጣናት አቅርበዉ ነበር::በተለይም ዛሬ አንዳንድ ደንቆሮዎች የሚያሽሞነሙኑት አያሌዉ ጎበዜ የሚባለዉ ባለስልጣን ይሄን ጥናት ያቀረቡ ሰዎችን እርምጃ አስወስዶባቸዋል::አንዳንዶቹም አርፈዉ እንዲቀመጡ ማስጠንቀቂያ ተሰጧቸዋል::አንዳንዶቹም ቀስ ብለዉ ክልሉን ለቀዉ ለነብሳቸዉ ወደሌላ የሀገሪቱ ክልል ሸሽተዋል::ሞያተኞች ዝም አላሉም::ግን ሞያ ሞያን በማያከብር እና ጥላቻን በልቡ በቋጠረ ሀይል ስር እየተዳደሩ አንድም ሀይል አይኖረዉም::

-ይሄ ሁሉ ሆኖም ድርጅቱ የሚገፈዉ ገንዘብ የት እንደሚገባ አይታወቅም:: እንደሚታወቀዉ ኦዲት እንዳይደረግ የራሱን ቢሮ በድማሚት እንዲያወድም ከባለስልጣናት መመሪያ የተሰጠዉ እና የፈጸመ ድርጅት አብቁተ ነዉ::

For comparison purpose:

1. Commercial Bank of Ethiopia (11.5%)
2. Oromiyaa Credit and Savings (11.50%)
3. Dedebit Credit and Saving Tigray (15%)
4. SIDAMA Microfinance Institution (15%)
5. Amhara Credit and Savings Institution (18%)

Some of the sources :
1. ttp://etd.aau.edu.et/bitstream/123456789/2428/3/Fekadu%20Yehuwalashet%20Final%20Thesis.pdf 2. http:// ://www.microfinancegateway.org/…/mfg-en-paper-loan…