ዓማራ ኢትዮጵያና አንድነት

ዓማራ ኢትዮጵያና አንድነት

ዓማራ ኢትዮጵያና አንድነትእስካሁን ድረስ አማራ ሆነው መሰረታዊ እዉቀት ያላቸው ሰዎች አማራ በስሙ አይደራጅ ወይም ብሄረተኝነቱን አያሳድግ ራሱን አይከላከል ብለው የጻፉትን አላየሁም። ታዲያ እንዳንድ ቤተ አማራ ነኝ የሚሉ አሳሳቾች ዘለው ኢትዮጵያን የሚዘረጥጡበትና የአማራዉን ታሪክ ባህልና ማንነት ለመበታተን ለምን ይተጋሉ?

ለምንድነው የአማራዉን መደራጀት ከኢትዮጵያና ከአንድነት ጋር እያገናኙ ዉዥንብር የሚነዙት?? የነሱ ሃሳብ አሁን የተበደለዉና ዘሩ ሳይቀር እንዲጠፋ የተደረገው አማራ ጠላቱ ወያኔ ሳይሆን ኢትዮጵያ ናት ብለው በራሱ በአማራው ኢትዮጵያን ለመምታት ነው። ይህ በፖለቲካ አካሄድ አቅጣጫ ማሳሳት (Misleading) ይባላል።

ወያኔ ሻቢያና ኦነግ ስንት አመት ለፍተው ማፍረስ ያቃታጨዉን የአማራውን የታሪክ ማህደር (ኢትዮጵያን) ለማጥፋት ከሌሎች ባእዳን ቅጥረኞች ጋር ሆነው መርዛቸዉን በመርጨት ላይ ናቸው። አማራዉ ወደፊት ብሩህ ጊዜ ላይ ደርሶ ጥቅሙና ደህንነቱን እንዲጠበቅ አላፊነት የሚሰማቸውና እዉቀት ያላቸው ዓማሮች ብቻ አቅጣጫ ሊሰጡት ይገባል።

የአማራው ጠላቶች ወያኔና የነሱን የዘር ፖለቲካ የሚያራምዱትን የዉሸት ፕሮፓጋንዳ በሁሉም አቅጣጫ ባዶ ማድረግ ይገባል። ይህም ማለት አማራው በአማራነቱ መደራጀትና ከዚህ በፊት አባቶቹ እንዳደረጉት ዓማራዉንና ሌሎች ከሱ ጋር የተሳሰሩ ብዙ ሚሊዮን ወገኖቹን መከላከልና መምራት መቻል አለበት። ኢትዮጵያዊነቱን ሳይገፍ ነገር ግን በአማራነቱ እንደ አንድ ነገድ መደራጀትና አቅሙን ማጎልበት የግድ ነው።

ይህም ማለት ከእንግዲህ የብዙሃኑን የአማራ ህዝብ ያላሳተፈ ህገወጥ መንግስት ኢትዮጵያ ዉስጥ እንዳይመሰረት መከላከል ነው። አማራነት እንደ ነገድና ኢትዮጵያዊነት እንደሃገር ከአባቶቻችን የተሰጠን እንጂ ከባርነት አገዛዝ ያገኘነው አይደለም። ገፍቶ እንኩዋን ቢመጣና አንዳንድ ነገዶች ለመገንጠል ቢፈልጉ አማራው ሃገሩን ኢትዮጵያን ለቆ የትም አይሄድም። የሚፈልጉ ይሂዱ እንጂ አማራ ከአባቱ ኢትዮጵ መሬት ንቅንቅ አይልም። ክብሩን ማንነቱንና ታሪኩን ያዘለችዉን ሃገር ለማንም ጥሎ እንደማይሄድና የነሱ መቀለጃ እንደማይሆን ኣንዳንድ ባንዳ ቤተ አማራ ነን ባይ ባእድ ነገዶች ቢያዉቁትና ባይደክሙ ጥሩ ነው።