ወያኔ ዛሬም በአማራው ወገኔ ላይ የጥፋት እጁን አልሰበስብም ብሎአል!!

 

ወያኔ ዛሬም በአማራው ወገኔ ላይ የጥፋት እጁን አልሰበስብም ብሉዋል !!

ወያኔ ዛሬም በአማራው ወገኔ ላይ የጥፋት እጁን አልሰበስብም ብሎአል!! ቀኑ 15/08/2008 ዓ፡ም እለተ ቅዳሜ የወሳዓና እለት ነው፡፡ ወያኔ በተቀነባበረ ሴራ በንፁሃን የሞረትና ጅሩ አርሶ አደሮች ላይ ቦንብ እንዲወረወር በማድረግ የሁለት ንፁሃን አርሶ አደሮችን ነፍስ ሲያጠፋ ለገበያ በመጡ አርሶ አድሮች ሸማቾችና እንሰሳት ላይ ጉዳት ያደረሰ መሆኑ ታውቁዋል፡፡

በሆነው ሁሉ እጅግ ያዘንን ሲሆን ይሄንን እኩይ ሴራ የፈጠሩ ግለሰቦች በአስቸኳይ ለፍርድ እንዲቀርቡ እንጠይቃለን፡፡

ወያኔ ከህዝብ የተነሳበትን ጫና ለመቀልበስ የተለያዬ የተቀነባበረ ሴራ በመስራት ህዝብ እየጨረሰ ነውና ከወዲሁ ሃይ ሊባል ይገባል፡፡ህዝብም ከመቼውም የበለጠ እራሱን በንቃት ሊጠብቅ ይገባል፡፡

ለሞቱት ወንድሞቻችንን ፈጣሪ ነፍሳቸውን በአፀደ ገነት እንዲያኖርልን እየተመኘን ለሟች ቤተሰቦችም መፅናናትን እንመኛለን፡፡


ዝርዝሩን ዙም ኢትዮጵያ እንድሚከተለው አቅርቦታል ያንብቡት

ከወሳዕናው የገበያ ላይ የቦብ ፍንዳታ በስተጀርባ !!
✍…………. …………………… …………. …………

☞ሁሉም ሰው ልብ ሊለው የሚገባ ወሳኝ ዜና፡፡
(የወያኔ አዲስ የዘር ማጥፋት ዘዴ)

ጉዳዩ በሞረትና ጅሩ ወረዳ ላይ በእነዋሪ ከተማ በ15/08/2008 እለተ ቅዳሜ የወሳዕና ገበያ ቀን በተለምዶ ከብት ተራ ተብሎ በሚጠራው የገበያ ቦታ ላይ ቦብ ፈንድቶ የሁለት ሰዎች መሞትና የሌሎች ብዙ ሰዎች መቁሰልን አስመልክቶ በአደጋው የተጎዱ እንሰሳቶችም እንደነበሩ ዘግይቶ በደረሰኝ ዜና ሰሞኑን ለንባብ ያበቃሁላችሁ እንደሆነ ይታወቃል፡፡

Enewari location map
The Location of Enewari in Ethiopia

ነገሩ እንዲህ ነው አንድ ነፍስ ላላወቀ ህፃን ቦንቡን የወያኔ ተላላኪዎች እንደመጫወቻ ሰጥተውት ገበያ አስገብተው የለቀቁት ሲሆን ልጁም በመነካካት ላይ እንዳለ የፈነዳበት ስለመሆኑ መረጃ ደርሶኛል፡፡ ወያኔ ይሄንን ሁሉ እኩይ ሴራ ሊፈፅም የቻለው ምንግዜም ቢሆን እንደፈለግሁት ላሽከረክረው ያልቻልኩት የአማራ ወረዳ አንዱ ነው በማለትና ከፍተኛ ስጋት ላይ በመግባቱ ምክንያት ሲሆን አሁን በየቦታው በህዝብ እንቤተኝነት ተወጥሮ ያለው ወያኔ ከዚህ ወረዳ የበቀሉ ቁርጠኛ የህዝብ ልጆችን ስም ለማጠልሸትና አሸባሪዎች ናቸው ብሎ የተለመደውን ድራማውን ለመስራት ፈልጎ እንደሆነ ታማኝ ምንጮቻችን አክለው ገልፀውልናል፡፡

እነዋሪ ከተማ ከአዲስ አበባ 194 ኪሎ ሜትር እርዝመት ላይ ስትገኝ እንሳሮና ዋዩ ወረዳ እና መርሃቤቴ የአማራ ወረዳዎች የሚያዋስኑዋት ሲሆን ከማንኛውም የኢኮኖሚ ጥገኝነት ነፃ የሆነች ወረዳ ከመሆኑዋም በላይ ህዝቧ ለወያኔ እጅ ያልሰጠ ባንዳነትን የሚፀየፍ ኩሩ ኢትዮጵያዊ ነው፡፡

☞መራኛና ጅሩ ሁለት የወንድ አገር
እነሱም አይመጡ እኛም አንሻገር::✔

ብሎ አገሬው ስለጀግንነቱ ቢያቀነቅንም ይሄንን ሁለት ወንድማማች ህዝብ የሚያገናኝ አገናኝ መንገድ እስከዚች ስዓት ድረስ ያልተሰራለት እና ምንም አይነት መሰረተ ልማት በአካባቢው ላለመስራት ወያኔ ምሎ የተገዘተ ከመሆኑም በላይ በዚሁ የወሳዕና ገበያ እለት የደለቡ ከብቶች የሚሸጡበት ታሪካዊ የገበያ ቀን ሲሆን ከከብቶቹ ሽያጭና ከእህል ሽያጭ በሚገኘው ገቢም አርሶ አደሮቹ የመሬት ማዳበሪያ የሚገዙበት የገንዘብ ማግኛቸው ምንጭ ሲሆን የገቢያቸውን አብዛኛውን ገንዘብ የሚያውሉትም ለመሬት ማዳበሪያ ግዥ ሲሆን ገቢውም በወያኔው ታላቁ ድርጅት በኢፈርት ባለቤቶችና ጉና የሚባል ድርጅት ውስጥ ገቢ እንደሚሆን ይታወቃል፡፡በመሆኑም ወያኔ በእጅ አዙር የዚህን ህዝብ አንጡራ ሃብት በተዘዋዋሪ በእጁ ያስገባና በቅኝ ግዛት ውስጥ ስላስገባው የዚህን ወረዳና የሌሎች መሰል የአማራ ወረዳዎችን የማዳበሪያ አቅርቦት ሙሉ በሙሉ እሱ ስለተቆጣጠረው በሰበብ አስባቡ ህብረተሰቡን አረግጦ እንዲገዛው የሚያችለውን ዘዴ ሁሉ ይጠቀማል፡፡

ይህ ሁሉ የአካባቢው አንጡራ ሃብት እየተዘረፈ እንኳን በሃይለ ስላሴ ዘመነ መንግስት ተሰርቶ የነበረው የጠጠር መንገድ አስፖልት የሚሰራለት ጠፍቶ ዛሬም አገሬው በትራንስፖርትና በመንገድ ችግር እየተሰቃዬ ይገኛል፡፡ ይህ በ194 ኪ/ሜ ከአዲስ አበባ እርቀት ላይ የሚገኝ መንገድ በፌደራሉ የመንገድ ጥገናና ግንባታ እቅድ ውስጥ የተጠቃለለ እንደሆነ ቢታወቅም ሆን ተብሎ ይሄንን ወረዳ ለማሰቃየት ወያኔ የበቀል ዱላውን ዛሬም ድረስ ሳያቆም በሰበብ አስባቡ እየደበደበው ይገኛል፡፡ የሚገርመው ይህ ሁሉ ግፍና እንግልቱ ለህዝቡ አልበቃ ብሎ ዛሬም በተቀነባበረ መልኩ ህዝብን እየጨረሰ በህዝብ ላይ ድራማውን ያለከልካይ እየሰራ ይገኛል፡፡ በዚሁ ወረዳ ውስጥና አጎራባች ወረዳዎች ውስጥ አሉ የሚባሉ ብርቅዬ የህዝብ ልጆች ሽፍታ በሚል ስበብ የጨረሰ ሲሆን ይሄው ዛሬ ያለከልካይ ይሄንን ምስኪን ህዝብ የደም እንባ እያስለቀሰው ይገኛል፡፡

ከዚህ ወረዳ ብቻ እስካሁን የበቀሉ ጠንካራና ብርቱ የፖለቲካ ብቃት ያላቸው ታዋቂ ፖለቲከኞች ውስጥ እነ አቶ ማሙሸት አማረ፣ኢ/ር ግዛቸው ሽፈራው፣አቶ ሸንቁጥ አየለን እናም በርካታ ወጣት ፖለቲከኞችን ያፈራች ወረዳ መሆኑዋን ተከትሎ እስከዛሬም በአማራው ላይ ወያኔ ሲፈፅም የነበረውን ግፍና በደል በቅርበት ሲከታተሉ የነበሩት እነዚሁ ብርቅዬ የኢትዮጵያ ልጆች አሁንም ለወያኔ ያልተኙ ብርቱ የህዝብ ልጆች ከመሆናቸውም አልፈው በሰላማዊ ትግል ብቻ ወያኔን ያንቀጠቀጡ የሰላም አንባሳደሮች ከመሆናቸውም በላይ የህዝባቸው ሰቆቃና ህመም የሚሰማቸው በህዝቡ የሚወደዱና የነገ የኢትዮጵያ የአደራ ልጆች ናቸው፡፡

ታዲያ ወያኔ የሰላማዊ እንቅስቃሲያቸው ከመቼውም በላይ የራስ ምታት ስለሆነበት ምንም በማያውቁ ህፃናት አማካኝነት ህዝብን ለማሸበርና የህፃናቱን እድሜ ለመቅጨት አዲስ የዘር ማጥፋት እስትራቴጅ የነደፈ መሆኑን ደርሰንበታል፡፡

ወያኔ በዚህ ታላቅ የወሳዕና የከብት ገበያ ላይ ለምን ቦብ ማፈንዳት አስፈለገው ብለን ስናስብ ሁሉም የሞረትና ጅሩ ኗሪዎች ከተለያዬ የአገሪቷ ክፍል ለብአሉ የሚሰባሰቡበት ቀን ስለሆነና የደለቡ ከብቶች ሽያጭ በከፍተኛ ሁኔታ የሚከናወንበት ወቅት ስለሆነ ሆን ተብሎ ህዝብን ለመጨረስ የተቀነባበረ የውንብድናና የባንዳነት ተልዕኮ ነው፡፡

ማሳሰቢያ
———

ሁሉም ኢትዮጵያዊ ህፃን ልጆቹን የሚያውቁት ሰውም ይሁን የማያውቁት ሰው መጫወቻ ብሎ ምንም አይነት እቃ ቢሰጣቸው እንዳይቀበሉ ከፍተኛ የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራ መስራት እንዳለበት ለመምከር እየወደድሁ የወያኔን አዲሱንና እኩይ የጥፋት አጀንዳውን ከወዲሁ በተባበረ ክንድ ማክሸፍ እንዳለብን በታላቅ አክብሮት ለማሳሰብ እወዳለሁ፡፡

በአደጋው ለሞቱባቸው ቤተሰቦች ታላቅ መፅናናትን እየተመኘሁ ሟቾቹም በአፀደ ገነትእግዚያብሄር እንዲያሳርፋቸው እመኛለሁ፡፡

ድል ለሰፊው የኢትዮጵያ ህዝብ

ሞት ለወያኔ፡፡

ምንጭ:- Zoom Ethiopia

18 hrs ·