ወያኔ አቶ ማሙሸት ዓማረንና አቶ ለገሰ ወልደሃናን በማሰቃየት ላይ መሆኑ ተሰማ

 

ወያኔ አቶ ማሙሸት ዓማረንና አቶ ለገሰ ወልደሃናን በማሰቃየት ላይ መሆኑ ተሰማ
ማሙሸት አማረ ህጋዊዉ የመኢአድ መሪ

ወያኔ አቶ ማሙሸት ዓማረንና አቶ ለገሰ ወልደሃናን በማሰቃየት ላይ መሆኑ ተሰማ ::በእስር ላይ በሚገኙት በመላዉ ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) አመራሮች ላይ የሚደረገዉ ኢሰበአዊ አያያዝ ቀጥሏል:: በተለይም በአቶ ማሙሸት አማረ (የመኢአድ ፕሬዝዳንት) እና በአቶ ለገሰ ወልደሃና (የመኢአድ የህዝብ ግንኙነት ም/ሃላፊ) ላይ የከፋ ኢሰበአዊ አያያዝ እየተፈጸመባቸዉ ሲሆን በየቀኑ በሚደርስባቸዉ ድብደባና ስቃይ የተነሳ ህይወታቸው አደጋል ይገኛል::

አቶ ለገሰ በደረሰበት ድብደባ አይኑ እጁ እግሩ ጆሮዉና መላ ሰዉነቱ አሳዛኝ የሆነ ጉዳት ደርሶባቸዋል:: ወያኔ የመኢአድ አመራሮችንና አባላትን አሁን ድረስ ከመላ ሀገሪቱ እየለቀመ ወደ እስር ቤት እያስገባ ከፍተኛ ስቃይ በማድረስ ላይ መሆኑ ተረጋግጦአል::

የወያኔ መንግስት በፖለቲካ ተቃዋሚነትም ሆነ በጋዜጠኝነት ያያዛቸዉን እስረኞች ሁሉ በጭቃኔ እንደሚያሰቃያቸዉ እና በመጨረሻም ብዙዎቹ ለጤና መታወክ ብሎም ለሞት እንደሚዳረጉ ይታወቃል:: የመላዉ አማራ ህዝብ ድርጅት (መአህድ) መስራችን ፕሮፌሰር አስራትን እንደ አብነት መጥቀስ ይቻላል::

በቅርቡም አቶ ሀብታሙ የሰጠዉን ምስክርንት ማስታወስ በቂ ነዉ:: በተለይም የአማራ ዘር ያላቸዉን እስረኞች በተለዬ እና በረቀቀ የማሰቃያ ስልት እያሰቃየ ህይወታቸው እንዲያልፍ ያደርጋል:: አቶ ለገሰ እና አቶ ማሙሸትም የዚሁ የወያኔ የጭካኔ ሰለባ ሆነዋል::

በመላዉ አለም የምትገኙ የመኢአድ ደጋፊዎች እንዲሁም ኢትዮጵያዉያን የዲሞክራሲ እና የሰበአዊ መብት ተቆርቋሪ ሀይሎች በአቶ ለገሰ እና በአቶ ማሙሸት አማረ ላይ የሚደርሰዉን እጅግ ዘግናኝ ኢሰበአዊ አያያዝ እንድታወግዙ እንጠይቃለን:: እንዲሁም ይሄንኑ ሁኔታ ለልዩ ልዩ አለም አቀፍ ተቋማት እንድታሳዉቁ እናሳስባለን::

ሸንኩጥ ዓየለ