ወያኔ መኢአድን በአቶ አበባዉ መሃሪ በኩል ለመንጠቅ ያደረገቸዉ ሙከራ ከሸፈባት‏

ወያኔ መኢአድን በአቶ አበባዉ መሃሪ በኩል ለመንጠቅ ያደረገቸዉ ሙከራ ከሸፈባት በዶር በዛብህ በኩል ለመንጠቅ ሌላ ሙከራ እያደረገች ነዉ:: የዲያስፖራዉን ፖለቲካ በማምታታት የሚታወቀዉ እና በዉጭ ሀገር የሚኖረዉ ግርማ ካሳ የተባለዉ ሰዉ የስትራቴጂዉ መሪ ነዉ::
-ወያኔ ጠንካራ ሰብዕና ያለዉ እና የመርህ ታጋይ ያስበረግጋታል:: ጠመንጃ ጨበጥኩ ብሎ ከሚፎክርባት ሰዉ ይልቅ ወያኔ የምትፈራዉ እዉነተኛዉና

የመርህ ታጋዮችን ነዉ:: በርግጥም ወያኔ የምትደነቅበት አንድ ባህሪ አላት::ይሄዉም እዉነተኛ ታጋዮችን ታዉቃለች::

-ጥቅምት 2007 ዓ.ም የመኢአድ ጠቅላላ ጉባኤ ከ483 አባላት ተሳታፊ ዉስጥ በ477 አባላት ሙሉ ድጋፍ አቶ ማሙሸት አማረን ፕሬዝዳንት አድርጎ መርጧል:: ወያኔም አቶ ማሙሸት አማረ እዉነተኛ ታጋይ እና የጸና ሰብዕና እንዳለዉ ስታዉቅ ጭንቅ ያዛት:: መኢአድ ዉስጥ ቁጭ ብለዉ ስለላ ለሚያደርጉ አንዳንድ የወያኔ ሰላዮች (አንዱ ዶ/ር በዛብህ ነዉ) ከበረከት ስምዖን ቢሮ በተደጋጋሚ ይተላለፍ የነበረዉ መመሪያ እነ እከሌ የሚባሉ ነፍጠኞች የመኢአድ አመራርን እንዳይዙ የሚል ነበር::

-በዋናነት አመራር እንዳይዙ ሲባሉ የነበሩት አቶ ማሙሸት አማረ : አቶ አብርሃም : ዶር ታዲዮስ እና ሌሎችም ነበሩ:: ወያኔ የነዚህን ሰዎች ዘር: ሀይማኖት: ትዉልድ ቦታ ሁሉ አጥንታ በሰነዶች እንዲህ ብላ አስፍራዉ ነበር:: አቶ ማሙሸት አማረ (የሰሜን ሸዋ ነፍጠኛ ስለሆነ): አቶ አብርሃም ጌጡ (የጎንደር ነፍጠኛ ስለሆነ) : ዶር ታዲዮስ (አማራ እና ኦሮሞ ስለሆነ እና ሁለቱን ህዝቦች ሊያስተባብርብን ይችላል በሚል) ስለሆነም እነዚህና ሌሎችም ለኢህአዴግ ህልዉና የማይመቹ ተቃዋሚዎች የመኢአድ አመራር እንዳይሆኑ::ለዚህም ዶ/ር በዛብህ: አቶ አበባዉ እና ሌሎችም የስለላ እና የማደናቀፍ ሀላፊነቱን ወስዳችሁ ስራችሁን በአግባቡ ስሩ ስትል መመሪያ ሰጥታ ነበር::

-የሆነ ሆኖ የነበረከት ስጋት እዉን ሆኖ ጥቅምት 2007 ዓም ወያኔ የምትፈራቸዉ አመራሮች መኢአድን እንዲመሩ ጠቅላላ ጉባኤዉ መረጣቸዉ:: ከዚያ ብኋላ ወያኔ አበደ:: በሺዎች የሚቆጠሩ የመኢአድ አባላትን: በመቶዎች የሚቆጠሩ አመራሮችን እስር ቤት መወርወር: መግደል እና መደብደብ ጀመረ::

-ጠቅላላ ጉባኤዉ የመረጣቸዉን አመራር አስወግዶ መኢአድን አንቆ ለአበባዉ ሰጠዉ::ያን ጊዜ የወያኔ ደጋፊዎች በተለይም ግርማ ካሳ የሚባለዉ ሰዉዬ መኢአድን አበባዉ እንዲመራዉ የተሰጠዉ ዉሳኔ ልክ ነዉ ሲል አብሮ ጨፈረ::

-በሚያሳፍር ሁኔታ አሁን ደግሞ ግርማ ካሳ የሚባለዉ የወያኔ ቀኝ እጅ በወያኔ ስትራቴጅ እየተመራ መኢአድን ለአቶ አበባዉ የተሰጠዉ ከህግ ዉጭ ነዉ እያለ ነዉ:: ይሄን ካለ ብኋላ መኢአድን መመራት ያለበት ዶ/ር በዛህብ ነዉ እያለ ነዉ:: ዋና ግቡ ግን በአበባዉ በኩል ሲከሽፍባቸዉ መኢአድን በዶ/ር በዛብህ በኩል ሊጠልፉ ማቀዳቸዉ ነዉ:: ግርማ ካሳ አቶ አበባዉን እፊት ሲደግፈዉ እንዳልነበረ አሁን ላይ ግን አቶ አበባዉ ጭራሽም አመራር ሊሆን አይገባዉም ነበር እያለ አቶ አበባዉን ይወቅሳል:: ግርማ ካሳ ትናንትና ስለተናገረዉ ነገር ግድ የለዉም:: የወያኔን መርህና ግብ ያስፈጽምልኛል ያለዉን ሁሉ እየተነሳ ይዘባርቃል::

-ግርማ ካሳ የዲያስፖራዉ የመኢአድን ክንፍ ለመንጥቅ የተሻለዉ እስትራቴጅ አበባዉን በበዛብህ መተካት ነዉ ብሎ አስቦ አዲስ ስትራቴጅ ለወያኔ አቀረበላት:: እሷም ተፈጻሚ አደረገችለት::

-ግርማ ካሳም ሆኑ ወያኔ ያልገባቸው ግን የመኢአድ ህልዉና በመኢአድ ደጋፊዎች: በመኢአድ አባላት እና የኢትዮጵያን ዲሞክራሲ እና ህልዉና በሚፈልጉ ሚሊዮን ኢትዮጵያዉያን መንፈስ ዉስጥ ያለ ጭብጥ መሆኑን ነዉ:: አጭበርባሪዎችን እና መሃል ሰፋሪዎችን የኢትዮጵያ ህዝብ በደንብ ከለያቸዉ ሰነበተ::

-አሁንም ህጋዊዉ የመኢአድ መሪ አቶ ማሙሸት አማረ ብቻ ነዉ:: ታዋቂዉ ጋዜጠኛ ሙሉቀን ተስፋዉ በተከታታይ እንደዘገበዉ ወያኔ ሰሞኑን በአቶ ማሙሸት አማረ: በአቶ አብርሃም ጌጡ እና በሌሎችም ህጋዊ የመኢአድ አመራሮች ላይ የስድብ : የማስፈራራት እና የወከባ ዘመቻ ከፍታለች:: የወያኔ ጭንቀት ያገረሸባት መኢአድን በዶ/ር በዛብህ በኩል ለመቆጣጠር አሁንም እንቅፋት የሚሆንብኝ የአቶ ማሙሸት አመራር ነዉ ብላ ነዉ:: ሽህ ጊዜ ይጭነቃችሁ እንጅ እዉነቱ አንድ ብቻ ነዉ:: ያም ህጋዊዉ አመራር አቶ ማሙሸት ብቻ ነዉ::

ሸንቁጥ አየለ