ኦሮሚያ በሚባለዉ ክልል በአማራ ህዝብ እና ኦሮሞ ባልሆኑ ነገዶች ላይየዘር ማጥፋት እና ማጽዳት ወንጀል በአስችኳይ ይቁም

ሐምሌ /04 /2012 ዓ.ም

ኦሮሚያ በሚባለዉ ክልል በአማራ ህዝብ እና ኦሮሞ ባልሆኑ ነገዶች ላይ እየደረሰ ያለዉ
ተከታታይ የዘር ማጽዳት በአስቸኳይ እንዲቆም ማስጠንቀቂያ ስለመስጠት
(የጋራ አቋም መግለጫ)


1.የዘር ማጥፋት እና ማጽዳት ወንጀል በአስችኳይ ይቁም
➢ ሰኔ/22/2012 ዓ/ም አርቲስት አጫሉ ሁንዴሳ በሰው እጅ መገደሉን ተከትሎ በተለያዩ ሚዲያዎች በተለይም OMN በተሰኘው ሚዲያ አማካኝነት “ነፍጠኛን ግደል” በሚል በተሰራጨው ቅስቀሳ መሰረት “ኦሮሚያ ክልል” እየተባለ በሚጠራው የሀገራችን ክፍል አማራ ላይ ያተኮረ የዘር ማጽዳት እና ማጥፋት ወንጀል እራሱን ቄሮ እያለ በሚጠራዉ የጥፋት ሀይል ተፈጽሟል::እንዲሁም በጉራጌ ማህበረሰብ : በወላይታ ማህበረሰብ እና ሌሎች ኦሮሞ ባልሆኑ ነገዶችም ላይ ተመሳሳይ የዘር ማጽዳት እና ማጥፋት እርምጃ ተወስዷል::

➢ መረጃዎች እጅግ የሚረብሹ ናቸዉ:: የኦሮሞ ክልል አጣራሁት ባለዉ መረጃ መሰረት የዘር ማጥፋት እርምጃ
የተወሰደባቸዉን ዜጎች እስከ ሁለት መቶ አምሳ ይደርሳል የሚል መረጃ አቅርቧል:: በሌላ መልክ የሚወጡ መረጃዎች
ደግሞ በጅምላ የተጨፈጨፉት ኦሮሞ ያልሆኑ ዜጎች እስከ አንድ ሽህ እንደሚደርሱ እየዘገቡ ይገኛሉ::
➢ እነዚህ በጅምላ የተጨፈጨፉ ዜጎች አገዳደል ደግሞ እጅግ ሰቅጣጭ ነዉ:: እሬሳን በድንጋይ እና በዱላ ተሰብስቦ
መደብደብ፣ እሬሳ ማቃጠል፣ እሬሳ መጎተት፣ ሰዉን ከእነ ነፍሱ በእሳት ማቃጠል : ሰዉን ዘቅዝቆ መስቀል:የሰዉ አይን ማዉጣት: ሰዉን በቤተሰቡ ፊት ለፊት በማጅሩ ማረድ ሁሉ የዘር ማጥፋቱ አካል ነዉ::

➢ በበርካታ ከተሞች በሻሸመኔ፣ በዝዋይ፣ በአርሲ፣ በሀረር፣ እና በልዩ ልዩ ስፍራዎች ህዝብን በጅምላ መግደል ብቻ ሳይሆን ቤት ማቃጠል፣ ንብረታቸዉን ማጥፋት፣ንብረታቸዉን መዝረፍ፣የቢዝነስ ተቋሞቻቸዉን ማቃጠል እና ልዩ ልዩ ወንጀሎች ተከናዉነዋል:: ከተሞች በጅምላ እንዲጠፉ ተደርጓል::

➢ ይሄም አልበቃ ብሎ ታሪካዊ ቅርሶችን ማዉደም እና ሀዉልቶችን ማፈራረስም የዚሁ የዘር ፍጅቱ አካል ነዉ:: የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ሀዉልት በለንዶን እንዲፈርስ ተደርጓል:: የራስ መኮንን ሀዉልት በሀረር እንዲፈርስ ተደርጓል::

➢ ከሁሉም በላይ የሚያሳዝነዉ ደግሞ እራሳቸዉን ለመከላከል የሞከሩ ዜጎችን የመንግስት ፖሊሶች
ማሳደዳቸዉ:ማጥቃታቸዉ፣ ማሰራቸዉ፣ መወንጀላቸዉ፣ እራሳቸዉን ሊከላከሉ ባሉት ላይ ጥይት መተኮሳቸዉ እና
የአስለቃሽ ጭስ መልቀቃቸዉ ነዉ::

➢ ቤተክርስቲያናትን ለማቃጠል በአዲስ አበባ ልዩ ልዩ ስፍራዎች የተሰበሰበዉ የቄሮ የዘር አጥፊ ሀይል ቤተክርስቲያንን ሊያቃጥል ሲሞክር ምዕመናን እና ካህናት ደወል ደዉለዉ ህዝብን ሰብስበዉ ቤተክርስቲያናትን ለመከላከል ያደረጉት ሙከራ በአብይ መንግስትና በታከለ ኡማ አመራር እንደ ወንጀል ተቆጥሮባቸዉ ክርስቲያኖች ተወንጅለዉ ወደ እስር ቤት እንዲገቡ ተደርጓል::

➢ እንዲሁም ቄሮ በሚባለዉ መንጋ ቤቱ በድንጋይ በጅምላ እየተደበደበ እና የቢዝነስ ተቋሙ እየጠፋ ቢቸገር በልዩ ልዩ ስፍራዎች ወጣቶች እና የአዲስ አበባ ነዋሪዎች እራሳቸዉን ለመከላከል በጋራ ቢወጡ የመንግስት ፖሊሶች እየተጠቃ ያለዉን ህዝብ ከወንጀለኛዉ ቄሮ ጋር ተባብረዉ አስለቃሽ ጭስ በመተኮስ እና በማስፈራራት ጸረ ፍትህ እና ጸረ ሰላም መሆናቸዉን አስመስክረዋል::

➢ በልዩ ልዩ ስፍራዎች እራሳቸዉን ሊከላከሉ የሞከሩ ዜጎችን ጠመንጃ በመንጠቅ እና አንቆ ለፖለስ በመስጠት በወንጀለኛዉ ቄሮ ገዳይ ኃይል ተገለዉ እሬሳቸዉ መንገድ ለመንገድ ሲጎተት ፖሊስ በተባባሪነት ተሰልፎ ተገኝቷል::

2. በኦርቶዶክስ ተዋህዶ ላይ የታወጀዉን የጥፋት ተልዕኮ በጥብቅ እናወግዛለን
➢ ወያኔ በማኒፌስቶዉ የኢትዮጵያ አንድነትን አፈርሳለሁ: የአማራን ነገድ አጠፋለሁ: የኦርቶዶክ ተዋህዶ ክርስትናን
አኮሰምናለሁ ብሎ በማወጅ ለሃያ ሰባት አመታት ብዙ ጥፋት ማድረሱ ይታወቃል::በተለዬ ሁኔታ ግን የአቢይ
መንግስት ወደ ስልጣን ከመጣበት ጊዜ ጀምሮ በአለፉት ሁለት አመታት ዉስጥ በተዋህዶ ቤተክርስቲያን ላይ እና
በምዕመኑ ላይ ከፍተኛ መከራ ወርዶበታል::

➢ ኦሮሚያ ተብሎ በሚጠራዉ ክልል ዉስጥ በርካታ ቤተክርስቲያኖች ተቃጥለዋል: በብዙ ሽህ የሚቆጠሩ ክርስቲያኖች ታርደዉ ተጥለዋል እንዲሁም የተዋህዶ እሴት የሆኑ ንብረቶች በብዛት አለ አግባብ ከቤተክርስቲያኒቱ
ተነጥቀዋል:: በሰሞኑ የአል-ቄሮ የዘር ማጽዳት እና ማጥፋት እንቅስቃሴም የተዋህዶ እምነት ተከታዮች:
ቤተክርስቲያናት እና የሀይማኖት አባቶች ብዙ ጥቃት ደርሶባቸዋል::በመሆኑም በኦርቶዶክስ ተዋህዶ ላይ የታወጀዉን
የጥፋት ተልዕኮ በጥብቅ እናወግዛለን::እንዲሁም የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን: እና ልዩ ልዩ የሀገሪቱ
ሀይማኖቶች በጋራ ቆመዉ በዚህች እምነት ላይ የተቃጣዉን አደጋ እንዲያወግዙ ጥሪ እናቀርባል::

3. ለዘር ጭፍጨፋ ዋና መነሻ የሆነዉ የወያኔ ህገመንግስት እንዲቀዬር:የጎሳ ፖለቲካ በህግ እዲታገድ እና
የጎሳ ክልሎች እንዲፈርሱ ስለ ማሳሰብ:-
➢ ከወያኔ/ኢህአዴግ ቀጥታ ሀገር አፍራሽ ሕገ መንግሥት በመዉረስ: የጎሳ ክልል አስተዳደር ስርዓት እንዲሁም የጎሳ ፖለቲካ እየተተገበረ ያለዉ በአቢይ መንግስት ነዉ:: አሁን ያለዉ ስርዓት ከዚህ የዘረኝነት አካሂያዱ መጀመሪያ እራሱን ማላቀቅ ካልቻለ በርካታ የዘር ማጥፋት እንቅስቃሴዎች ወደፊትም እንደሚኖሩ ግልጽ ነዉ::

በአማራ ህዝብ እና ኦሮሞ ባልሆኑ ነገዶች ላይየዘር ማጥፋት እና ማጽዳት ወንጀል በአስችኳይ ይቁም

➢ በዚህ ስርዓት የተነሳ ብሄርንና ኃይማኖትን እየለዩ፤ በተለይ የአማራን ማህበረሰብ እንዲሁም ሌሎች ኦሮሞ ያልሆኑ እና በኢትዮጵያዊነታቸዉ የሚያምኑ ልዩ ልዩ ነገዶችን መጨፍጨፍ የሚቆም አይሆንም። ለአለፉት ሰላሳ አመታት የዘር ማጽዳት ስራዉ ያተኮረዉ በአማራ ማህበረሰብ ላይ ቢሆንም አሁን በተከሰተዉ የዘር ማስዳት ወንጀል ግን ጉራጌወች :ወልይታዎች: እና ሌሎች ነገዶችም የጥቃት ሰለባ ተደርገዋል::ሌላዉ ቀርቶ የኦርቶዶክስ ክርስትና እምነት አባል ኦሮሞዎችም ሳይቀር የአማራ እምነት ተከታይ ናችሁ ተብለዉ የዚሁ የአክራሪ ኦነግ ሸኔዎች እንቅስቃሴ የጥቃት ሰለባ እየተደረጉ እንዳለ ማስረጃዎች አሉ::

➢ እዉነተኛ ተቃዋሚዎች እና አብዛኛዉ የኢትዮጵያ ህዝብ የወያኔ ህገመንግስት እንዲለወጥ ለጠ/ሚ አቢይ አህመድ ጥያቄ በአቀረበበት ወቅት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የህዝብ ጥያቄ ጨፍልቆ ለማለፍ “ለአንድ ብሄር ስንል ህገመንግስቱን አንለዉጥም” የሚል የእብሪት መልስ በመስጠት የዘረኝነት ምንጭ የሆነዉ ህገመንግስት ጠበቃ በመሆን እራሱን አጋልጧል::

➢ ዛሬ አንዳንዶች እንደሚሉት የአቢይ መንግስት ኢትዮጵያ እንድትድን የሚፈልግ ቢሆን ኖሮ የዘረኝነት ምንጭ የሆነዉን ህገመንግስት እንዲሻሻል ባደረገዉ ነበር:: እንዲሁም የዘር ማጽዳት እና ፍጅት መንስኤ የሆነዉን የጎሳ አከላለል ማፍረስ ብሎም የጎሳ ፖለቲካን በህግ ማገድ ተቀዳሚ ተግባሩ ይሆን ነበር:: ዛሬ ኦነግ:ሽኔ : ህዉሃት እንዲሁም ኦህዴድ/ኦዴፓ/ ዉስጥ የመሸጉ የብልጽግና ባለስልጣናት ነገድን ከነገድ ለማፋጀት ለም መሬት ያገኙት ጠቅላይ ሚኒስቲሩ እንደ አይኑ ብሌን በሚንከባከበዉ የወያኔ ህገመንግስት: የጎሳ አከላለል ብሎም የጎሳ ፖለቲካ ነዉ::

➢ ይሄዉ መርገምት የሆነ ህገመንግስት እስካልተለወጠ ድረስ ኦነግ: ሸኔ እና ህዉሃት የዘር ፍጅት መፈጸማቸዉን
አያቆሙም::እንዲሁም ጸረ ኢትዮጵያዊ የዉጭ መንግስታት በሀገሪቱ ጉዳይ ጣልቃ በመግባት ኦነግ: ሸኔ እና ህዉሃትን ለመጠቀም የተመቼ ለም መሬት ፈጥሮላቸዋል::

➢ በመሆኑም በአስቸኳይ ይህ ህገ መንግሥት ተቀይሮ የእያንዳንዱን ኢትዮጵያዊ መብት በሚያስከብር ህገ መንሥት
እንዲለወጥ ጥሪ እናደርጋለን። እንዲሁም አሁን ያለዉ ጎሳን መሰረት ያደረገ የክልል አከላለል እንዲሰረዝ ብሎም የጎሳ
ፖለቲካ በህግ እንዲታገድ ጥሪያችንን እናቀርባለን::

➢ ይሄንኑ ሀገር አፍራሽ የሆነ የጎሳ ፖለቲካ ለም መሬት በመጠቀም ወያኔ: ሸኔ : ኦነግ እና አል-ቄሮ ህብረት ፈጥረዉ ኢትዮጵያን የማፍረስ ዘመቻቸዉን ማፋጠን የቻሉት በውጭ ኃይሎች በተለይ በግብፅ መንግሥት ድጋፍ ጭምር ስለሆነ የግብፅ መንግሥት እጁን ከኢትይጵያ ላይ እንዲያነሳ እንጠይቃለን::

4. ሰላማዊ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎችን አጋጣሚን ተጠቅሞ የማጥቃት እና የማሰር ወንጀለኛ
እርምጃን እንቃወማለን:-

➢ በህዝባችን ላይ የተደረገዉ የጅምላ የዘር ማጥፋት ወንጀል ሳይበቃ ይሄንኑ አጋጣሚ በመጠቀም የአብይ
መንግስት በሰላማዊ የተቃዋሚ መሪዎች ላይ የወሰደዉን የመደብደብ እና የማሰር እርምጃ አጥብቀን
እንቃወማለን:: የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ መሪ እስክንድር ነጋ ላይ የተወሰደዉ የድብደባ እና
እንዲሁም በሌሎች የባልደራስ አመራሮች ላይ እና በኢ/ር ይልቃል ላይ የተወሰደዉን የእስር እርምጃ በአስቸኳይ እንዲስተካከል እንጠይቃለን::

5. የህዝብ ድምጽ ሚዲያዎችን የማፈን አምባ ገነናዊ እርምጃን በጥብቅ እናወግዛለን
➢ የአስራት ሚዲያ ከተመሰረትበት ጊዜ ጀምሮ የመላዉ ኢትዮጵያ ህዝብ ድምጽ በመሆን በተለይም ለአማራ
ህዝብ ድምጽ በመሆን የአቅሙን ለመስራት የሞከረ ሚዲያ ነዉ:: አስራት በእንቅስቃሴዉ ሁሉ የኢትዮጵያ
ህዝብ እርስ በርሱ እንዲፋቀር እና መስተጋብር እንዲኖረዉ እንዲሁም የሚሰሩ ኢፍትሃዊ ስራዎችን ለማጋለጥ
ከመስራት የዘለለ ወንጀል ያልሰራ ሚዲያ ነዉ:: አስራት የዘር ቅስቀሳ አላደረገም ወይም ነገዶች እንዲጋጩ
አልሰራም።ሆኖም የአብይ አንባገነን መንግስት አጋጣሚዉን ተጠቅሞ አስራትን የመበርበርና የመዝጋት
እርምጃ ወስዶበታል። ይህም እርምጃ በአስቸኳይ እንዲስተካከል እንጠይቃለን::
6. የፌደራል መንግስት ዜጎችን የመጠበቅ እና የህግ የበላይነት ማስከበር ግዴታዎቹን በተገቢዉ መልክ እንዲወጣ
በጥብቅ ስለማሳሰብ:-

➢ መንግስት የህግ የበላይነትን ማስከበር: የህዝቡን በሰላም ወጥቶ መግባት እና ደህንነቱን ማረጋገጥ አለበት:: የመንግስት ግዴታም ይሄዉ ነዉ:: አሁን ያለዉ የፌደራል መንግስት ግን ይሄን ግዴታዉን እየተወጣ አይደለም:: ይልቁንም የህዝቡን ሰላማዊ እንቅስቃሴ ለማስጠበቅ የተዋቀረው የመንግስ አስተዳደር መዋቅር በዚህ የዘር ማጥፋት ሂደት ዉስጥ ተሳታፊ ሆኖ ህዝባችን ሲጨፈጨፍ ቆሞ ተመልካች እንደነበረ የሚወጡ መረጃዎች ያመለክታሉ:: ይህ ማለት መንግስት እራሱ ያደራጀው መዋቅር ለህዝባችንም ሆነ ለሀገር ህልውና ስጋት መሆኑን ያመልክታል። ይህን የስጋት ምንጭ የሆነ የመንግስት መዋቅር ባስቸካይ እንዲያስተካክል።

➢ መንግስት ከዚህ ቀደም 86 ዜጎች በጎሳ ማንነታቸዉ እና በሀይማኖት ማንነታቸዉ በጀዋር:ኦነግ ሸኔ ትዛዝ ሲጨፈጨፉ ገዳዮችን በማንቆለጳጰስ: እንዲሁም “ኦሮሞ ኦሮሞን እንዳይገለዉ ብለን ወንጀል ሲሰራ በትግስት አለፍነዉ” በሚለዉ ወንጀለኛ መርህ ላይ በመቆም ለተጨፈጨፉ ወገኖች ፍትህ ሳይሰራ በአላዬሁም እንዳለፈዉ ይታወሳል::የኦሮሞ ክልል ባለስልጣናት አጣራንዉ ብለዉ ያቀረቡለትን መረጃም ለራሱ እንዲያመቸዉ የሞቱ ዜጎችን ጎሳ በመቁጠር : ሁኔታዎች ከፌደራል መንግስቱ በሄዱ በገለልተኛ አካላት ሳይጣሩ ነገሮችን አድበስብሶ አልፎት እንደነበረ ይታወሳል::አሁንም በተመሳሳይ ይሄንኑ ሁኔታ ደግሞታል::አሁን የተከናወነዉን የዘር ማጽዳት ወንጀል የኦሮሞ ክልላዊ መንግስት አጣራሁት ብሎ የለቀቀዉን ተአማኒነት የሌለዉ መረጃ እንደ እዉነት በመቀበል ለህዝብ እያሰራጨ ነዉ::

➢ ይሄዉ የኦሮሞ ክልላዊ መንግስት አጣራሁት ብሎ የለቀቀዉ መረጃም ሆን ብሎ እዉነተኛዉን የዘር ጭፍጨፋ እና የዘር ማጽዳት ለመደበቅ የታለመ ሆኖ አግኝተንዋል:: ስለሆነ በአስችኳይ ከፌደራል መንግስቱ ገለልተኛ ሀይል ተቋቁሞ በኦሮሞ ክልል የተከናወነዉን የዘር የማጽዳት ወንጀል እንዲያጣራ ጥሪ እናደርጋለን::ወደፊትም ይሄዉ ድርጊት እንዳይደገምም የአቢይ መንግስት ግልጽ የሆነ ሀገራዊ ስትራቴጂ ነድፎ በአስቸኳይ ለኢትዮጵያ ህዝብ ይፋ እንዲያደረግ ስንል ጥሪ እናቀርባለን::

➢ በጎሳ ፖለቲካ የሚመራዉ መንግስት ከዘረኛ መንግስታዊ መርሆዎች በመላቀቅ በህዝባችን ላይ እየተከናወነ ያለዉን የዘር ማጥፋት፣ የንብረት ማዉደም እና ህዝቡ እራሱን ሊከላከል ሲነሳ ህዝብን የማጥቃት ዘረኛ እርምጃዉን እንዲያስተካክል አጥብቀን እናሳስባለን:: የዚህ መግለጫ ዋና አላማዉም ኦሮሞ ባልሆነ ነገዶች ላይ በተለይም በአማራ ማህበረሰብ ላይ እየተከናወነ ያለዉ የዘር ማጥፋት በአስቸኳይ እንዲቆም ማስጠንቀቅ ነዉ:: ይሄ መግለጫ ማስጠንቀቂያ የሆነበት ዋና ምክንያትም አሁን እየተከናወነ ያለዉ የዘር ማጥፋት ወንጀል መዘዙ ተመዞ የማያልቅ እዳ መሆኑን በግራም በቀኝም የቆመ እንዲያዉቀዉ በጥብቅ የሚያሳስብ ብቻ ሳይሆን ተያያዥ እዳም እንዳለ  ለማሳወቅጭምር በመሆኑነዉ::

7. የአማራ ክልላዊ መንግስት በአማራ ህዝብ ስም ስልጣን ላይ ተጎልቶ የአማራ ህዝብ ሲፈጅ ቆሞ
መመልከቱን እንዲያቆም ስለማስጠንቀቅ
➢ የአማራ ክልላዊ መንግስት የስሙ ስያሜ እንደሚያመለክተው የአማራ ህዝብ ወክሎ በአማራ ህዝብ ስልጣን ላይ
የተቀመጣ መንግስት ነው:: በእርግጥ ይህ “መንግስት” ታሪኩ የተበላሸ እና እንኳን “ከክልሉ ውጪ” ላለው አማራ ይቅርና እዚያው “በክልሉ ውስጥ” ላለው የአማራ ህዝብ የማይሆን መሆኑ እናውቃለን:: ነገር ግን እንዲህ አይነቱ አይን ያወጣ የዘር ፍጅት ሲፈፀም ቢያንስ በኦሮሞ ክልል ህግና ስርዓት እንዲከበር ጥሪ ማድረግ ሞራላዊ ግዴታው መሆኑን ማስታወስ እንወዳለን። ስለሆነም የአማራ ክልል መንግስት በአማራ ህዝብ ስልጣን ላይ ተጎልቶ የአማራን ህዝብ በዘር ማንነቱ ሲፈጅ ቆሞ መመልከቱን እንዲያቆም በጥብቅ እናስጠነቅቃለን::

በአማራ ህዝብ እና ኦሮሞ ባልሆኑ ነገዶች ላይየዘር ማጥፋት እና ማጽዳት ወንጀል በአስችኳይ ይቁም

8. የኦሮሞ ክልላዊ መንግስት ኦሮሞ ባልሆኑ ነገዶች ላይ የሚያደርሰዉን የአፓርታይድ የዘር ማግለል እና
ለይቶ በማንነት ማጥቃት እርምጃዉን በአስቸኳይ እንዲያቆም ስለ ማስጠንቀቅ
➢ ኦሮሚያ ተብሎ በተሰዬመዉ ክልል ዉስጥ ከ20 ሚሊዮን በላይ አማሮች እንደሚኖሩ ይታወቃል:: ከአማራ ህዝብ በተጨማሪም በርካታ ሚሊዮን ጉራጌዎች: እና ልዩ ልዩ ነገዶች እንደሚኖሩ ይታወቃል:: በክልሉ የሚኖረዉ የሌላ ነገድ ተወላጅ ሁሉ ግብር ከፍሎ እና ህግ አክብሮ የሚኖር ህዝብ ነው። ይሁንና ለአለፉት ሰላሳ አመታት ኦሮሚያ የተባለዉ ክልል የአፓርታይድ ስርዓት የሚያራምድ ክልል ሆኖ ቀጥሏል:: በተለይም በአለፉት ሁለት አመታት ዉስጥ ኦህዴድ/ኦዴፓ ማዕከላዊ መንግስቱን: መከላከያዉ: ደህንነቱን እና የፖሊስ ሀይሉን በጁ በማስገባት ኦሮሞ ያልሆኑ ነገዶች ላይ የሚከናወነዉን ወንጀል ከማስቆም ይልቅ ቆሞ ተመልካች እና ተባባሪ ሆኖ ተገኝቷል::

➢ በክልሉ የሚኖሩ ልዩ ልዩ ነገዶችን ማለትም አማራዉን: ጉራጌዉን: ጋሞዉን: ጌዲዮዉን: ወላይታዉን እና ሌሎችንም ነገዶች ማፈናቀል: መግደል: ገሎ ማቃጠል: ገድሎ መስቀል: ንብረታቸዉን ማዉደም እና ንብረታቸዉን መዉረስ በኦነግ ሸኔ ቄሮ ትብብር ሲፈጽም ተባባሪ በመሆን እጁን አጣጥፎ ቆሞ ይመለከታል::ይሄ አይነቱ የኦሮሞ ክልል ወንጀለኛ አካሂያድ ወደፊት ለህዝቦች አብሮ መኖርም ሆነ ለጋራ ደህንነታቸዉ እጅግ አደገኛ ጋሬጣ መሆኑን ማሳሰብ እንወዳለን::የክልሉ ፖሊስ ሀይል እና የፌደራል መንግስቱ ፖሊስ ሀይል ተናበዉ በመቆም በአማራ ማህበረሰብ ላይ እና በልዩ ልዩ ኦሮሞ ባልሆኑ ነገዶች ላይ የሚደርሰዉን ወንጀል ቆመዉ የሚመለከቱ እስከ መቼ ነዉ? ይሄን ወንጀለኛ አካሂያዳችሁን እንድታስተካክሉ እና በክልሉ ዉስጥ ለሚኖሩ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ነገዶች ሁሉ የህግ ከለላ እና ጥበቃ እንድትሰጡ ስንል በጥብቅ እናሳስባለን::

9.የተባበሩት መንሥታት የሰብአዊ መብት ተቋም የዘር ጭፍጨፋዉን በገለልተኝነት እንዲያጣራ ስለ መጠዬቅ
➢ ብሄርና ኃይማኖት ለይቶ የሚደረገው የዘር ማጥፋት እና ማጽዳት ወንጀል ባሰቸኳይ እንዲቆም ጥሪ እያደረግን፤
የተባበሩት መንሥታት የሰብአዊ መብት ተቋም ልዩ ልኡካን በአስቸኳይ ወደ ኢትዮጵያ እንዲልክና ሁኔታውን እንዲያጣራ ጥሪ እናቀርባለን።

10. የጥቃት ኢላማ ለተደረጉ ወገኖቻችን ካሳ እንዲሰጣቸዉ እና እርዳታ በአስቸኳይ እንዲቀርብላቸዉ መጠዬቅ
➢ በዘር ጭፍጨፋዉ የጥቃት ኢላማ ተደርገዉ ለሞቱ : የአካል ጉዳት ለደረሰባቸዉ እና ለተፈናቀሉ ወገኖቻችን ሁሉ ካሳና እንዲሰጣቸዉ ብሎም አስቸኳይ እርዳታ እንዲደረግላቸ በጥብቅ እናሳስባለን።  

ሐምሌ 04/2012 ዓም በመላዉ ዓለም የሚገኙ የልዩ ልዩ የፖለቲካ ድርጅቶች የድጋፍ ማህበራት:ልዩ ልዩ ህዝባዊ ማህበራት: ሚዲያዎች:አክቲቪስቶች እና ጋዜጠኞች በኢትዮጵያ በተደጋጋሚ እየተከሰተ ያለዉን የዘር ማጥፋት እና ማጽዳት በማዉገዝ እና በአስቸኳይ መፍትሄ እንዲበጅለት ለማሳሰብ ስብሰባ በማድረግ ይሄን የጋራ አቋም መግለጫ አዉጥተዋል::