እዉቀት በጋምቤላ ንጹሃን ወገኖቻችን ላይ የተፈጸመውን ጭፍጨፋ አጥብቃ አወገዘች

 

እዉቀት በጋምቤላ ንጹሃን ወገኖቻችን ላይ የተፈጸመውን ጭፍጨፋ አጥብቃ አወገዘች
እዉቀት በንጹሃን ወገኖቻችን ላይ የተፈጸመውን ጭፍጨፋ አጥብቃ አወገዘች

እዉቀት በጋምቤላ ንጹሃን ወገኖቻችን ላይ የተፈጸመውን ጭፍጨፋ አጥብቃ አወገዘች ። ይህንን ሁዋላቀር የሆነ ኢሰብአዊ ወንጀል የፈጸሙ ያስፈጸሙና እንዲፈጸም ምክን ያት የሆኑ ግለሰቦችም ሆነ ድርጅቶችን የኢትዮጵያ ህዝብ ለፍርድ ለማቅረብ ጠንክሮ እንዲሰራ እዉቀት ጥሪዋን አስተላልፋለች።

ባለፉት ሃያ አምስት አመታት ወያኔ የኢትዮጵያን ማእከላዊ መንግስት በማፈራረስ ሀገራችን በወሮበሎች የምትመራ ባለቤት አልባ ሆና አባቶታችን ከሃያላን ወረራና ባርነት ጭምር አስከብረዉና ተከላክለው ያቆዩት ነጻ ህዝብ ዛሬ ተዋርዶ በሃገር ዉስ ጥ በመንግስ ነኝ ባዩ ወያኔና በዉጭ ጸረ ኢትዮጵያ የነሱ ስዉር ተባባሪዎች በመጨፍጨፍ ላይ ይገኛል።

ከዚህ በፊት ታፍራና ተከብራ የነበረችዉ ሃገር ዛሬ የማንም መጫወቻ ሆናለች። በአንድ በኩል ራሱ ወንጀለኛው ወያኔ በብሄር ብሄርሰብ ካባ ተሸፍኖ ለዲሞክራሲና ለእኩልነት ነው የመጣሁት እያለ በዓአማራ በኦሮሞ በአፋር በጋምቤላ በደቡብ ህዝብ በሱማሌ በሲዳማና በሌሎች እጅግ አናሳ በሆኑ ንጹህ ብሄረሰቦችን ላይ ሳይቀር ሁዋላቀርና ታሪክ ይቅር የማይለው የግፍ ጭፍጨፋ አካሂዶአል ። ከዚህ ብሄራዊ ዉርደትና ፍርሃት ነጻ ሆኖ በሰላም ለመኖር የኢትዮጵያ ህዝብ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ጸረ ወያኔ ግምባር መፍጠርና በያለበት ትግሉን አፋፍሞ የወያኔን ስር ከኢትዮጵያ ዉስጥ ነቅሎ መጣል አለበት። ወያኔ እስካለ ድረስ የኢትዮጵያ ህዝብ ወደ ሰላም ዲሞራሲና እድገት በምንም አይነት ሊያመራ እንደማይችል ባለፉት ፪፭ የሰቆቃ አመታት አይተናል።

ድል ለነጻነትና ለሰላም ወዳዱ የኢትዮጵያ ህዝብ!!