ኢትዮጵያ የማነች? ማነው የሚያዝባት?

ኢትዮጵያ የማነች? ማነው የሚያዝባት? አንድ በወያኔ የሰለጠነ ጎሳ ወይም ዘር ነኝ ባይ አዲስ ኣበባ የኔ ነው::  ሸዋ የኔ ነው:: ወይም ባሌ የኔ ነው:: ማለት ይችላልን? ለመሆኑ ይሄ ክፍለ ሀገር ወይም በሱ ኣባባል ክልል የኔ ነው ለማለት ምን ህጋዊ መረጃ ወይም ታሪካዊ መነሻ አለው?

በዛሬይቱ እትዮጵያ ላይ ከአዳምና ከሄዋን ጀምሮ ማን ሰፍሮ ይኖር እንደነበረ እናዉቃለን? ለመሆኑ ከዛሬ 5000 ዓመት በፊት ጀምሮ ኢትዮጵያ የአማሮች አባት የዮቶር አገር መሆኑዋን እናዉቃለን?  ከአክሱምና ከዚያ ወዲህ እላዋላይ ከመፈጠራቸዉም በላይ እነማን መንግስት መስርተው ጠብቀው እንደአቆዩአት እናዉቃለን? ካላወቅን አርፈን መቀመጡ ጨዋ ከማድረጉም በላይ ሰላምን ይሰጥናል።

አባቶቻችንም መሬቱዋን በደማቸው ጠብቀው ያቆዩት ለሁሉም እትዮጵያዊ ነው። ማንም ለኦሮሞም ሆነ ለሌላው ጎሳ ይሄ ነው ያንተ ሃገር ብሎ ቆርሶ ሊሰጥ ወይም ሊነሳ የሚችል ምድራዊ ሃይል የለም። እረ እየተስተዋለ!! ህዝባችንን ከአንድነት ከሰላም ጎዳናና ከእድገት መስመር አታሶጡብን። ኢትዮጵያ እንኩዋን ለኛ ለልጆቹዋ ለሌላም ትተርፋለች። እባካችሁ ተዉን። ይህንን ለማድረግ የምትሞክሩ የወያኔ ሎሌወች ወደ ታሪክ ከዞራችሁና ዛሬ ኢትዮጵያ የምትባለው ሃገራችን የማን ዓጽመ-እርስት እንደሆነች ባለመቀበል በሃይል ፍላጎታችሁን ለማሳካት ከተንቀሳቀሳችሁ ባዶአችሁን ነው የምትቀሩት::

ክብርና አንድነት ለሰላም ወዳዱ ሰፊው የኢትዮጵያ ህዝብ!!