በማዕከላዊ ታስሮ የሚሰቃየው የወጣት አወቀ አባተ የእጅ ጣቶች ተሰባብረዋል

   በማዕከላዊ ታስሮ የሚሰቃየው የወጣት አወቀ አባተ የእጅ ጣቶች ተሰባብረዋልበማዕከላዊ ታስሮ የሚሰቃየው የወጣት አወቀ አባተ የእጅ ጣቶች ተሰባብረዋል :: የለውጥ ሐዋሪያ በሆኑት በዐማራ ወጣቶች ላይ የሚደርሰው ቶርቸር እጅግ ጭቃኔ የበዛበትና ለሚሰማውም አስደንጋጭ ነው::  በአቶ ማሙሸት አማረ በሚመራው መኢአድ የአዲስ አበባ ቀጠና የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊና በአገር አቀፍ የላዕላይ ምክር ቤት አባል በሆነው በወጣት አወቀ አባተ ላይ ከጳጉሜ 5 ቀን ጀምሮ በማዕከላዊ በደረሰበት ድብደባ የአካል ጉዳተኛ መሆኑን አብረውት ታስረው በነበሩ ሰዎች በኩል የወጣው መረጃ ያመለክታል፡፡

ወጣት አወቀ አባተ በወይዘሪት ንግሥት ይርጋ የሽብርተኝነት የክስ መዝገብ ሥር ከተከሰሱት ወጣቶች መካከል አንዱ ሲሆን የተመሠረተበትን የፈጠራ ክስ ጣቶቹ በመሰበራቸው ምክንያት መርማሪዎቹ የተሰበሩ ጣቶቹን ይዘው እንደፈረሙለት ተሰምቶአል፡፡ ወጣት አወቀ አባተ እስካሁን ድረስ የትግሬዎች የቶርቸር ሰለባሲሆን ከመስከረም 3-18 ቀን 2009 ዓ.ም. በየቀኑ በሚፈጸምበት ስቃይ ለአካል ጉዳቱ ምክንያት ነው ተብሏል፡፡

ወጣት አወቀ በአሁኑ ሰዐት የሁለቱም እጆቹ ጣቶች ከመሰባበራቸዉ በተጨማሪ  የጀርባው ሰርሰር (ስፓይናል ኮርድ) በብረት በመደብደቡ ምክንያት በትክክል መራመድ እንደማይችል ታዉቆአል:: የግራ ጆሮውም መስማት ተስኖታል፡፡ ወጣት አወቀ ሽንት በሚሸናበት እና በሚጸዳዳበት ጊዜም ከፍተኛ መጠን ያለው ደም እንደሚፈሰውና በአፋጣኝ ሕክምና ካላገኘ በሕይወት የመቆየት እድሉ የመነመነ እንደሆነ ምንጮቹ ገልጸዋል፡:

ወጣት አወቀ  በአዲስ አበባ አየር ጤና አካባቢ የራሱ ጣውላ ቤት የነበረው ቢሆንም እሱ በመታሰሩ ቤተሰቦቹም እንዳያስቀጥሉት ጫና በመኖሩ ምክንያት ድርጅቱ ተዘግቷል፡፡ ወጣት አወቀ ቀደም ባሉት ዘመናት ከሁሉም የዐማራ አካባቢዎች በተለይ ደግሞ የመኢአድ አባላት ከሁሉም አካባቢ በቃሊቲ፣ ሸዋ ሮቢትና ዝዋይ ሲታሰሩ ቤተሰቦቻቸውንና እስረኞችን በገንዘብና በቁሳቁስ በግንባር ቀደም ሲረዱ ከነበሩት መካከል አንዱ ነው፡፡ ሆኖም አሁን ላይ የወጣት አወቀ ቤተሰቦች በአሁኑ ሰዐት ችግር ላይ መሆናቸውን ጭምር ነው የትግል ጓዶቹ የነገሩን፡፡

ወጣት አወቀ አባተ አሁንም በዐማራነቱ የደረሰበት ስነ ልቦናዊ ጉዳት በአካል ከደረሰበትጉዳት ሁሉ የሚልቅ ነው ብለውናል፡፡ መረጃውን የሰጡን ሰዎች በወጣት አወቀ ላይ የደረሰው ግፍ በጽሑፍ የማይገለጽ ብዙ ጉዳይ እንዳለውና የዓለም አቀፉ ማኀበረሰብ ሕይወቱን ለማትረፍ ጥሪ እንዲቀረብ ሁሉ ተአሳስበዋል፡:

Source :

https://www.brannamedia.com/amharic/awoke-abate/amp/