ቅኑና ሃገር ወዳዱ አሰፋ ጫቦ አረፉ

ቅኑና ሃገር ወዳዱ አሰፋ ጫቦ አረፉ

ቅኑ አሰፋ ጫቦኢትዮጵያ ታላቅ ልጅዋን አጣች። ከእንግዲህ ማን እዉነቱን ተናግሮ ምስክር ይሆናታል? ሞት ለሁሉም አይቀርም ግን በትውልድ ታምኖ ተከብሮና ተወዶ ወደ ማይቀረው ዓለም ማለፍ ለእንደነ አሰፋ ጫቦ አይነት የተሰጠ ልዩ ጸጋ ነው።

ኢትዮጵያ አደጋ ላይ በወደቀችበትና ወያኔ ጀሌዎቹን ሰብስቦ የደባ ህገ መንግስቱን ሲያጸድቅ

“አለባብሰው ቢያርሱ

ባረም ይመለሱ”

በማለት ያልሆነ ስራ መሰራቱንና ህዝቡም ያልተሳተፈበትና እዉቅና ያልሰጠው መሆኑን በመግለጽ ፊት ለፊት እዉነቱን አፍረጥርጠው የተናገሩ አድርባይነትና ፍርሃት ያልሸበባቸው ቆራጥ ኢትዮጵያዊ ነበሩ። ወይኔዎች ልብ ኖሮአቸው ይህንን የአቶ አሰፋን አባባል ከግምት ዉስጥ ቢያስገቡ ኖሮ ዛሬ የሚገኙበት ማጥ ዉስጥ ገብተው ተቀርቅረው አይቀሩም ነበር። በዚያን ጸረ ኢትዮጵያዉያን ተጠራርተው ባዘጋጁት ስብሰባ ላይ ፕሮፈሰር አስራትና አቶ አሰፋ ጫቦ ከሌሎች ጥቂት የቁርጥ ቀን ልጆች ጋር ሆነው ከታሪክ ተጠያቂነት ድነዋል:: የሃገራቸዉን ክብር በመጠበቅ ገና ከመጀመሪያው በወያኔና በተከታዮቹ ላይ ስጋት ከመፍጠርም አልፈው ጸረ ወያኔው ትግል እዚህ ደረጃ ላይ እንዲደርስ ከፍተኛ የስነልቦና የቅስቀሳ ስራ ሰርተዋል።

ህዝባችንም ለበታኝ ጸረ ኢትዮጵያዉያን እንዳይንበረከክ በመጻፍና በመናገር አስተምረዋል።

ቅኑና ሃገር ወዳዱ አሰፋ ጫቦ አረፉ
ከ600 ዓመት በላይ እድሜ ያላትና አቶ አሰፋ ጫቦ ተውልዶ ባደገበት አካባቢ የምትገኘው የጋሞ ብርብር ማሪያም የኢትዮጵያ ታሪክ ቁዋሚ ምስክር

ሞት አይቀርም

ስም አይቀበርም”

ዕውቀት ለመላው ቤተሰባቸው ለቤተ ዘመድና ለሰፊው ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ሁሉ መጽናናትን ይስጥልን ብላ መልእክቱዋን የምታስተላልፈው በከፍተኛ ሃዘን ነው። የወንድማችንን አቶ አሰፋ ጫቦን ነብስ በገነት ያኑርልን። ዐሜን!!