ስለ ኢትዮጵያ አንድነት ስንናገር ጠላት የምናባብል ለሚመስላችሁ

ስለ ኢትዮጵያ አንድነት ስንናገር ጠላት የምናባብል ለሚመስላችሁ

ሸንቁጥ አየለ

    ኢትዮጵያን ከጸረ አማራ እና ከጸረ ኢትዮጵያን አላቀን እጃችን እናስገባታለን:: እኛ ማንንም አናባብልም::አባብለንም አናቅም::

የአባቶቻችን ልጆች እንጅ ጠላት በመጣ ቁጥር አገር አፍርሰን: ድንበር ደርምሰን ኢትዮጵያን አቃጥለን እንጥፋ የምንል አይደለንም::

ኢትዮጵያ የአባቶቻችን ሀገር ነች:: ለማንም ምናምንቴ አሳልፈን አንሰጣትም:: ኢትዮጵያን ከጠላት አላቆ የህዝባችን ማድረግ እና ኢትዮጵያን ጥሎ መፈርጠጥ የተለያዩ ናቸዉ:: ጠላት ጉልበቱ በበረታ ቁጥር አባቶቻችን ኢትዮጵያን ጥለዋት አልፈረጠጡም:: ከጠላት መንጋጋ ተዋግተዉ እና ተጋድለዉ ነጻ እያደረጉ ጠበቋት እንጅ:: የኢትዮጵያን ህዝብ እያስተባበሩ: ጠላትን ስሩን እየነቀሉ እና ሰላምን እያሰፈኑ ኖሩ እንጅ ጠላት መጣ ብለዉ ድንበሬ ከዚህ መልስ ብቻ ነዉ ወደ እሚል ሽሽት ዉስጥ አልገቡም:: እኛም የአባቶቻችን ልጆች እንጅ የባእድ ልጆች አይደለንም እና ኢትዮጵያን ዛሬም አንተዋትም::

ጠላት አጥፍተን: አገር አቅንተን እና ህዝባችንን በፍቅር አንድ አድርገን ለመኖር ግን ቁርጠኞች ነን:: ይሄ ደግሞ ጠላት ማባበል አይባልም:: ጠላትማ ይነቀላል:: ጠላት ሳይነቀል አገርም አይቀና: ህዝብም አንድ አይሆን እናም መርገጫ መሰረትም የለም:: ኢትዮጵያን ከጠላት አላቆ የህዝባችን ማድረግ እና ኢትዮጵያን ጥሎ መፈርጠጥ የተለያዩ መሆናቸዉን ግን በደንብ አስምራችሁ ያዙልኝ::