ማሙሸትን ማስፈራሪያ አይበግረውም!

 

ማሙሸትን ማስፈራሪያ አይበግረውም!
ማሙሸት

ማሙሸትን ማስፈራሪያ አይበግረውም! ‹‹ታስረህ የማይገባህ ስለሆንክ አንተን ከዚህ በኋላ አናስርም፤ በሰላም የምትማር ይመስልሃል! ከዚህ በኋላ አልቆልሃል ለምንም ጊዜ የለህም››

ይህ ከላይ የተጠቀሰው መልእክት ለአቶ ማሙሸት አማረ በ0967333321 ከተላኩለት መልእክቶች መካከል አንዱ ነው፡፡ ማሙሸት አማረ አገር በሕወሓት ከተነጠቅን በኋላ ግማሽ የሚሆነውን እድሜውን በእስር አሳልፏል፡፡ ከዐሥር ጊዜ በላይ ታሥሮ 12 ወርቃማ ዓመታት የወጣትነት እድሜውን ወይን (ሕወሓት) ቅርጥፍ አድርጎ በልቶበታል፡፡ ማሙሸትን ሲፈልጉ በሽብረተኛነት ሲሻቸው በአመጽ አሊያም በፈለጉት የፈጠራ ክስ አንገላተውታል፡፡

ሰውየው ግን በአቋሙ ለዘመናት በጽናት ይጓዛል፡፡ እስራትም ሆነ እንግልት ማሙሸትን የሚፈቱት አይደለም፡፡ በፕሮፌሰር አስራት ከተሞረዱት ሰዎች ማሙሸትን የሚያክለው የለም ብል ያጋነንኩ አይመስለኝም፡፡

እና ምን ለማለት ነው፤ ማሙሸትን ሰሞኑን ስልክ በመደወልና መልክት በመላክ ለማስረፈራራት የሚደረገው ነገር ሁሉ የማሙሸትን ባሕሪ ሕወሓት እስካሁን እንዴት እንዳላወቀው አይገባኝም፡፡ ማሙሸት እኮ ታስሮም ግርማ ሞገስ አለው፡፡

ለማንኛውም በማሙሸት ላይ ማስረፈራሪያና መልክት ከሚልኩት ስልኮች መካከል 0912 051486 እና 0967333321 ዋናዎቹ ናቸው፡፡

(በማሙሸት አማረ፣ አብርሐም ጌጡ፣ ዘመነ ምሕረትና ሌሎችም ላይ የደረሱ ግፎችን ግለሰቦቹን አስፈቅጄ ወደፊት በዝርዝር አስነብባለሁ፡፡)

Muluken Tesfaw