ሚዲያ የዲሞክራሲ ሀይላት ቁልፍ መሳሪያ: ሊደገፍ የሚገባዉን የሞረሽ ሚዲያ ምስረታ እንደማሳያ

ሸንቁጥ አየለ

ኢሳት ሲቋቋም ወያኔ ክ􏰀 ጭነት እንደተጫነበት እና ወገቡ እንደተገጠበ አህያ በጣም መቅበጥበጥ ብቻ ሳይሆን ኢሳት የሚባል ሚዲያ እንዳይ􏰁ጠር ማንኛዉንም መ􏰁ጨርጨርና ጫና አድርጓል::ኦሮሞ ሚዲያ ኔትዎርክ (OMN) ሲመሰረት የወያኔ ደም ብዛት ከፍ ያለዉ ያለ ምክንያት አይደለም::

አንድ የተቃዋሚ ሚዲያ : ወይም አንድ ነጻ ሚዲያ : ወይም አንድ የሲቪል ማህበራት ሚዲያ ሲቋቋም የወያኔ የመጀመሪያ ጥያቄ ይሄን ሚዲያ እንዴት አድርጌ ላጥ􏰂ዉ የሚል ነዉ::እንደሚታወቀዉ በርካታ ዌብ ሳይቶችን በማ􏰁ን ህዝብ መርጃ ያልደረሰዉ :ያልነቃ እና የደነቆረ አካል ሆኖ እንዲቀጥል አሁንም ወያኔ የተለያዩ ክ􏰀 ስልቶቹን ቀጥሏል::

አንድ ደ􏰂ር ነጻ ጋዜጠኛ: ወይም አንድ ጸሃ􏰃 ከህዝቡ መሃከል ብቅ ሲል የወያኔዎች ቀንድ ይቆማል:: ልባቸዉ ይመታል:: ምቀኝነት ያንቀጠቅጣቸዋል:: የቅናት ዛራቸዉ ይነሳል::እንዴት አድርገዉ እንደሚያጠ􏰀ትም ሳያሰልሱ ያስባሉ:: ያቅዳሉ:: አቅደዉም አይተዉም:: ስንቱን ጀግና ደ􏰂ር ጋዜጠኛ እና ጸሃ􏰃 እስር ቤት ወርዉረው ለጊዜዉ ግፍ እየ􏰁ጸሙ እፎይ ይላሉ::

ወያኔ ብቻ ሳይሆን ማንኛዉም አምባገነን ሀይል ከሽህ ሰራዊት በላይ አንድ ደካማ ሚዲያ ይ􏰁ራል:: ግን ለምን? የዲሞክራሲ ግንባታ ሂደትን ጠንቅቀዉ የተመራመሩ: ዲሞክራሲ በአንዲት አገር ዉስጥ ጎልብቶ እንዲቀጥል የዲሞክራሲ ትጥቅና ስንቅ ሚዲያ መሆኑን የሚያበስሩ ምሁራን አለ ሚዲያ ዲሞክራሲ ግንባታን ማሰብ ቀልድ ነዉ ይላሉ::እነዚሁ ምሁራን እንደሚሉት የአምባገነንነት ጸር ጠመንጃ ሳይሆን ሚዲያ ነዉ ይላሉ::

የዲሞክራሲና አስተዳደር ማዕከል (CENTER FOR DEMOCRACY AND GOVERNANCE) የሚባለዉ ተቋም የሚዲያ ሚና በዲሞክራሲ ግንባታ ሂደት ( “…promoting the transition to and consolidation of democratic regimes throughout the world.” THE ROLE OF MEDIA IN DEMOCRACY:A STRATEGIC APPROACH ) በሚለዉ የስትራቴጅ ጽሁ􏰀 እንደሚያብራራው ስለ ዲሞክራሲ ግንባታ የሚያስብ ማህበረሰብ/አካል/ቡድን የመጀመሪያ ስራዉ ሚዲያ ግንባታ ላይ ትኩረት ሰጥቶ መረባረብ : ሚዲያንም በርትቶ መገንባት መሆኑን አብራርቶ ያቀርባል:: ከዚህ በተጨማሪም ከላይ ከተጠቀሰዉ ሰነድ ጋር ተያያዥነት ያላቸዉ በርካታ የጥናት ጽሁፎች የሚስማሙበት አንድ ጭብጥ ቢኖር ሚዲያ የዲሞክራሲ ሀይላት ቁልፍ መሳሪያ ነዉ::

አምባ ገነኖች ከማህበረሰቡ የሚደብቁት ግፍ: ዝር􏰃ያ: ሸፍጥ: ዘረኝነት: ተንኮል: ግዲያ: ዜጎችን ማ􏰁ናቀል: መግ􏰂ት እና ህገወጥ አገዛዞች ወደ ህዝብ ጆሮ ከደረሱ እንደሚያከትምላቸዉ ያዉቃሉ:: የነቃ: በመረጃ የታጠቀ: ስለ መብቱ ያወቀ ማህበረሰብ የአምባ ገነኖች የጉሮሮ አጥንት ብቻ ሳይሆን መቃብራቸዉን በፍጥነት ቆፍሮ መቀመቅ የሚከታቸዉ ጉልበትንም ታጥቆ የተቀመጠ እምቅ ሀይል መሆኑን ያውቁታል::

ስለዚህ የአምባ ገነኖች የመጀመሪያ ስራ ህዝብን ማደንቆር ነዉ:: ህዝብን ለማደንቆር ዋናዉ መንገድ ደግሞ ሚዲያዎች እንዳይኖሩ ማድረግ ነዉ:: የደነቆረ ህዝብ ልክ እንደ ከብት በተ􏰁ለገዉ አቅጣጫ ይነዳል እና አምባ ገነኖች የህዝብ ንቃተ ህሊና እንዳያድግ ማንኛዉንም መስዋዕትነት ያደርጋሉ::ፕሮፖጋንዳቸዉም የነሱን ግፍ የሚያጋልጥ ጸረ አምባ ገነንነት ሚዲያ እንዳይኖር ለማድረግ ነዉ::

ስለዚህ ህዝቤን እወዳለሁ: አገሬን እወዳለሁ: የነገዉ ኢትዮጵያዊ ትዉልዴ የዲሞክራሲ አየር የሚተነፍስ እንዲሆን እ􏰁ልጋለሁ የሚል ማንኛዉም ዜጋ ሚዲያዎችን አበክሮ መርዳት አለበት:: አንዳንድ ሰዉ አንድ ሚዲያ ወይም ሁለት ሚዲያ የሚበቃ ይመስለዋል:: የዲሞክራሲ ትግሉ ዉስብስብነት በደንብ ያልገባዉ ሰዉ ምናልባት በጥቂት ሚዲያዎች እረክቶ በጀርባዉ ለጥ የማለት ዝንባሌ ይታይበት ይሆናል::የዲሞክራሲ ትግል ግን ዉስብስብ እና ዘር􏰁 ብዙ ነዉ እና በርካታ ሚዲያዎች የግድ ያስ􏰁ልጋሉ::

ስለሆነም ሚዲያ ሲባል አንድ ወይም ሁለት አይደለም:: ብዙ ዌብ ሳይቶች: ብዙ ሬዲዮን ጣቢያዎች: ብዙ ቴሌቪዥን ጣቢያዎች የግድ ያስ􏰁ልጋሉ:: ዲሞክራሲ ግንባታ ሂደቱ: አምባ ገነኖችን የመዋጋት ስልቱ እና ማህበረሰብን የማንቃት ትግሉ እጅግ ዉስብስብ እና አድካሚ ነዉና ዉስብስብ ስትራቴጅና ስልት ያስ􏰁ልጋል:: በብዙ ምክንያት ህዝብ በቀላሉ በአንድና በሁለት ሚዲያ የሚነቃ አይሆንም::

ህዝብ ብዙ የመረጃ እሳት ሊነድበት ይገባል:: በጥቂት ጋዜጠኞች ጥረት ወይም በጥቂት ጸሃ􏰃ያን ጥረት አለዚያም በጥቂት የዲሞክራሲ አቀንቃኝ ሀይላት ህዝብ ለመራራዉ ትግል አይዘጋጅም:: ብዙ ሚዲያዎች: ብዙ ጋዜጠኞች: ብዙ የዲሞክራሲ አቀንቃኞች እና ብዙ የዲሞክራሲ ታጋዮች ያስ􏰁ልጉታል:: ብዙ ተቋማት: እና ብዙ ዉስብስብ ስትራቴጅዎች: ስልቶች: አ􏰁ጻጸሞች እና አካሂያዶች ያስ􏰁ልጋሉ::

ሚዲያ የዲሞክራሲ ሀይላት ቁልፍ መሳሪያ ነዉ:: አሁን ባሉት ኢሳት: ኦሮሞ ሚዲያ ኔትዎርክ (OMN): የተወሰኑ ዌብ ሳይቶች እንዲሁም አንድ እና ሁለት ጋዜጦች ላይ የሞረሽ ሬዲዮ መታከል ለዲሞክራሲያን ሀይላት ትልቅ ጉልበትን ይጨምራል:: የማህበረሰብ እና ተቋማት ጥናት ተመራማሪዎች አበክረዉ እንደሚመክሩት ማንኛዉንም አይነት መሰረታዊ የህብረተሰብ ለዉጥ ለማምጣት ካስ􏰁ልገ እያንዳንዱን እማህበረሰቡ እጅ ላይ ያሉ ተቋማትን በማስተባበር : በእጃቸዉ ላይ ያለዉን እዉቀት ብሎም ሀብት በማቀናጀት ብሎም ለአንድ ግብ እንዲሰሩ ማድረግ የሚቻለዉ የመጀመሪያ ደረጃ አዎንታዊ የተግባቦት እና የትብብር መን􏰁ስ ሲገነቡ ነዉ::

በመሆኑም ማንኛዉ በዲሞክራሲ ትግል ላይ ያለ ኢትዮጵያዊ ግለሰብ: ተቋም እና ሀይል የሞረሽን ሚዲያ ምስረታ ጥረት በመደገፍ ነገ ለሰ􏰂 ትብብር ቅድመ መሰረት መጣል ይጠበቅበታል:: የትግሉ ሂደት ግብ አንድ ነዉ:: ለሁሉም ዜጎቿ የተመቸች ዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን መፍጠር::ማንም ወገን በዘሩ: በሀይማኖቱ: በፖለቲካ አመለካከቱ እና በግለሰብ ፍልስፍናዉ የማይገለልባት ሀገር መገንባት ነዉ::

ይሄ ሂደት ግን እንዲህ ወረቀት ላይ እንደመጻፍ ወይም ተሰብስቦ እንዲሚወራዉ ቀላል ጉዳይ አይደለም:: ነገሩን ከባድ ከሚያደርጉት ሁኔታዎች ዉስጥ ዋናዉና አንዱም የነቃ ማህበረሰብን እና በመረጃ የታጠቀ ህዝብን የመፍጠር ሂደቱ ብዙ ሀብት: እዉቀት እና ጉልበት የሚ􏰁ልግ መሆኑ ነዉ::

እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ዜጋ ወይም የዲሞክራሲ ሀይል አንድ ወይም ሁለት ሚዲያዎችን ብቻ ሳይሆን መርዳት ያለበት አቅሙ በቻለዉ መጠን በርካታ ሚዲያዎችን መርዳት ይጠበቅበታል:: ስለ ሆነም አሁን በመቋቋም ሂደት ላይ ያለዉን የሞረሽ ሬዲዮ ጣቢያ ለመርዳት ሁሉም ወገን ቁርጠኛ ተነሳሽነት በማድረግ የዲሞክራሲያን ክንድ እንዲ􏰁ረጥም ማገዝ ይጠበቅበታል::

አንዱ ሲደክም አንዱ እዳር ቆሞ አይሆንም:: አንዱ ሲደክም ሌሎቻችን አይዞህ በርታ ከማለት በተጨማሪም በተጨባጭ የቻልነዉን እርዳታ በማድረግ ነገን ደግሞ ለሰ􏰂 ትብብር እና የኢትዮጵያን ህዝብ የዲሞክርሲ ጥም ለመቁረጥ የሚያስችል መሰረት መጣል ወሳኝ ነዉ::

ተነሱ : አታመንቱ የሞረሽ ሚዲያ ምስረታ እዉን ይሆን ዘንድ እንርዳ! ሚዲያ የዲሞክራሲ ሀይላት ቁልፍ መሳሪያ ነዉ !

https://www.facebook.com/S.Ayele.Eth/posts/1024078357641216