ሊያጠፋህ አቅዶ የተነሣ፣ አዳኝህ ሊሆን አይችልም!

ሊያጠፋህ አቅዶ የተነሣ ፣አዳኝህ ሊሆን አይችልም!

ከታላቁ የዐድዋ ጦርነት ድል ማግሥት ጀምሮ ዐማራው እንዲጠፋ ተፈርዶበት ፣ የተለያዩ የማጥፊያ ዘዴዎች ተጠንተው በሥራ ላይ መዋል ከጀመሩ 122 ዓመታት ተቆጥረዋል። በነዚህ ዓመታት ቀስ-በቀስና ደረጃ በደረጃ በአገር በቀል ዐማራና ኢትዮጵያ ጠል በሆኑ ቡድኖችና ግለሰቦች ትብብር፣ ዐማራውን ብቻውን አቁሞ ለማጥፋት የሚያስችሉ ሥራዎች በታቀደ መልኩ ሢሠሩ ኖረዋል።

ዐማራው በሌሎች ነገዶች ብቻ ሳይሆን፣ በራሱ ልጆች ጭምር እንዲገደፍና እንዲጠቃም የረቀቀ ሤራ ተሠርቷል። ከሤራዎቹ ዋናው ትውልዱን ዐማራው በአመራር ሰጭነት የሌለበት፣ የዐማራው ጠላቶች የሆኑ የባንዳ ልጆች የሚመሯቸው የግራ ዘመም ርዕዮት ዓለም አራማጅ የሆኑ ድርጅቶች በማደራጀት፣ ኅብረተሰቡን በጨቋኝና ተጨቋኝ መደቦች፣ ጨቋኝና ተጨቋኝ ብሔረሰቦች ብሎ በመከፋፈል፣ በሁለቱም ክፍፍሎሽ ተጠቂው ዐማራ የሆነበት አካሄድ መከተል ዋናው የዐማራ ማጥቂያ ሥልት ሆኖ በሥፋት ተሠራበት …

ከሞረሽ ወገኔ ዓማራ የተሰጠዉን ሙሉ መግለጫ ለማንበብ ይህንን መስመር ይጠቁሙ