ፕሮፌሰር አስራትና አቶ ዐማረ (የማሙሸት አባት)

ፕሮፌሰር አስራትና አቶ ዐማረ (የማሙሸት አባት)

ሸንቁጥ አየለ

ፕሮፈሰር አስራትና አቶ ዐማረ (የማሙሸት አባት)
ፕሮፈሰር አስራት ወልደየስ

ማሙሸት አማረ ኢትዮጵያን ለማዳን ወደ ትግል የገባዉ ወያኔ በአማራ ህዝብ ላይ በ1983 የጅምላ ፍጅትባወጀበት እና በሚያከናዉንበት ወቅት ነበር:: በወቅቱ ክቡር ፕሮፌሰር አስራት መአህድን መስርተዉ በመላ ሀገሪቱ በመንቀሳቀስ ህዝቡን ሲያስተባብሩ የማሙሸትን አባት አቶ አማረን ያስገረማቸዉ ነገር ነበር:: አቶ አማረ አንድ ጥያቄ ፕሮፌሰር አስራትን ጠጋ ብለዉ ጠየቁ:: “ለመሆኑ በዚህ እድሜዎት ወደ ትግል ለምን ገቡ?” ሲሉ ፕሮፌሰር አስራትም በትህትና መለሱ:: “ህዝቡን በዘሩ ምክንያት ወያኔዎች እያስፈጅት እና እየፈጁት ነዉ:: የአማራን ህዝብ ከእልቂት ለመከላከል ብዬ ነዉ በዚህ እድሜዬ የምደክመዉ::”

አቶ አማረ ወደ እነ ማሙሸት ዞር ብለዉ ተመለከቱ:: አላመነቱም::” እኚህ ሽማግሌ በዚህ እድሜአቸዉ ስለ ህዝባቸዉ እየደከሙ እናንተ ምን ትሰራላችሁ? በሉ ፕሮፌሰር አስራትን ተከተሏቸዉ !” ማሙሸት አማረ በዚያን ወቅት በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የኢኮኖሚክስ ተማሪ ነበር::እናም የአባቱን ትዕዛዝ አክብሮ ወደ ትግሉ ዘዉ ብሎ ገባ:: ወደ ትግሉ በጥልቀት ሲገባ ከፕሮፌሰር አስራት ጋር ወደ ጥልቁ የትግል አለም ተያይዘዉ ገቡ:: ማሙሸት አማረ መላዉ ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) ከተመሰረት ብኋላም በልዩ ልዩ እርከኖች በማገልገል እስከ ድርጅቱ ፕሬዝዳንት እነት አገልግሏል:: አሁንም የመኢአድ ህጋዊ ፕሬዝዳንት ማሙሸት አማረ ነዉ::

ማሙሸት አማረ ከሊቁ ክቡር ፕሮፌሰር አስራት ጋር 8 አመታት ታስሯል:: በወቅቱ የኢትዮጵያ አርበኞች ግንባር የሚባል ታጣቂ ሀይልን በሰሜን ሸዋ እና በምስራቅ ጎጃም አንቀሳቅሳችኋል እስረኞችን በደብረብርሃን እና በልዩ ልዩ ቦታዎች ወህኒ ቤት እየተሰበረ እንዲያመልጡ አድርጋችኋል እንዲሁም በአዲስ አበባ ቤተ መንግስቱ እንዲቆፈር እና በመንግስት ባለስልጣኖች ላይ ጥቃት የማድረስ ሙከራ አድርጋችኋል ተብለዉ ስምንት አመታት ሙሉ በወህኒ ማቀዋል:: ከቅንጅት አመራሮች ጋር ማሙሸት አማረ ሁለት አመታትን ታስሮ ተፈቷል:: ቅንጅት ሲመሰረት የመላዉ ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት ፓርቲን በመወከል ከቅንጅት አመራሮች ጋር ቁልፍ ሚና ተጫዉቷል:: በመከራ ዉስጥ እያለፈ ለኢትዮጵያ ትግል እና ተጋድሎ አንድም ቀን ግንባሩን ሲያጥፍ አልተስተዋለም::

ፕሮፈሰር አስራትና አቶ ዐማረ (የማሙሸት አባት)
ማሙሸት ዓማረ ለመኢአድ አባላት ንግግር ሲያደርግ

በሊቢያ ኢትዮጵያዉያን ወጣቶች በአክራሪዎች የተገደሉ ወቅት ደግሞ የኢትዮጵያን ህዝብ ቀስቅሰሃል በአዲስ አበባ የተደረገዉን ሰልፍ በድብቅ መርተሃል እንዲሁም ለተገደሉት ወጣቶች ተጠያቂዉ መንግስት ነዉ ብለሃል ወጣቱ በድህነት እንዲሰደድ በበረሃ እንዲያልቅ የሚያደርገዉ መንግስት ነዉ ብለሃል ተብሎ ከአንድ አመት በላይ ታስሯል:: ማሙሸት አማረን አያይዘዉም የከሰሱት ክስ መንግስት እንዳይረጋጋ መንግስትን እረስፍት ነስተሃል በማለት ጭምር ነዉ:: በተያያዥ ክሶችም እንዲሁ ከአንድ አመት በላይ እስር ቤት ማሳለፉይልታወቃል:: በአሁኑ ወቅት በአማራ ክልል እና በኦሮሚያ የተቀሰቀሰዉን አመጽ መርተሃል አስተባብረሃል ሰራዊት በድብቅ አቋቁመሃል በሰሜን ሸዋ ወታደራዊ ማሰልጠኛ አዘጋጅተሃል ተብሎ በእስር ላይ ይገኛል::

ይሄም ሁሉ ሆኖ ይሄ ጀግና አላፈገፈገም: አልደከመዉም: አልሰለቸዉም: ወያኔን የሚያክል አማራን ጠላቴ ነዉ ያለ ሀይል: ኢትዮጵያን ካላፈረስኩ ጤና የለኝም ብሎ የሚያስብ ሀይል: ኢትዮጵያን ለማጥፋትም አማራ የሚባለዉን ዘር መደምሰስ አለብኝ ብሎ የሚል ሀይልን ማሙሸት አማረ ፊት ለፊ ግንባሩን ሳያጥፍ 26 አመታት ሙሉ እየታገለ አለ:: ወያኔዎች ማሙሸት አማረን በብዙ ነገሮች ይጠሉታል::በዘሩ: በሀይማኖቱ: በፖለቲካ አመለካከቱ: ኢትዮጵያን በመዉደዱ: በማንነት ኩራቱ: በልበ ሙሉነቱ ብሎም ጽኑ በሆነዉ የዲሞክራሲ እና የህዝቦች ብልጽግና አቋሙ:: ወያኔዎች የቱንም ያህል ቢጠሉት እና ቢያሰቃዩትም እንደ ማሙሸት አማረ አይነቶችን ጀግኖችን ግን ምንም ነገር አልበገራቸዉም:: ማሙሸት አማረ በአጠቃላይ ከ13 አመታት በላይ በወያኔ እስር ቤት የህይወት ዘመኑን እንዲገፋ ያስገደደዉ የወገኖቹ ፍቅር ነዉ::

ሆኖም አንድም ቀን ሲማረር ተሰምቶ አያዉቅም:: ሰዎች ወያኔን ሲራገሙ እና ሲወቅሱ ማሙሸት አማረ የሆነ የግርምት ፈገግታ አለዉ :: ፈገግ ይላል ! የራሱ የሆነ ፈግታ ብቻ ! ከዚያም ” ወያኔዎች ስራቸዉን እየሰሩ ነዉ:: እኛ እንደራጅ:: እንታገል::እንሰባሰብ:: ለዉጥ የሚመጣዉ በትግል ብቻ ነዉ” ሲል ያስረዳል:: ማደራጀት ጸጋዉ ነዉ:: ስለ መደራጀት ተናግሮ አይታክተዉም::

ማሙሸት ዓማረ ለመኢአድ አባላት ንግ ግር ሲያደርግ