ጥልቅ

ጥልቅ

ጥልቅ
ጥልቀት
መጥለቅ
ጠለቀ
ጠላቂ
ማጥለቅ

አጥላቂ
አጠላላቂ
አጠላለቅ

ጥልቅ፥ መግባት ከእይታ መሰውር መስጠም ማለት ነው። አጠቃቀሙ ፩) የዉሃን የባህርን ወይም የዉቅያኖስን ጥልቀት (ከላይ ከዉሃው አናት እስከ ታች መሬት ድረስ ያለውን እርቀትየሚያመለክት ነው)። ምሳሌ፤ ፓስፊክ ዉቅያኖስ ከአለም ካሉ ዉቅያኖሶችም ሆነ ባህሮች በጥልቀቱ አንደኛ ነው።

፪) የአንድን ሰው አስተሳሰብ ብስለት የእዉቀት ደረጃ ወይም እረቂቅነት ለመግለጽ እንጠቀምበታለን። ምሳሌ፤ መጽሃፍ ቅዱስ ዉስጥ ያሉ ቃሎች ጥልቅ ናቸው ማለት በቀላሉ ልንረዳቸው አንችልም።

፫) መጥለቅ በዉሃ ዉስጥ፥ በዉሃ ዋና ወደ ዉስጥ መግባትና ከእይታ መጥፋት ማለት ነው (በእንግሊዝኛ ዳይቭ ማለት ነው።

፬) መጥለቅ ለፀሃይ፥ ማታ ፀሃይ በስተምስራቅ ስትገባ በዓማርኛ ፀሃይ ጠለቀች ነው የሚባለው። ይህም የሚያመልክተው ፀሃይ ትጠልቃለች ወይም በሌላ በኩል ትወጣለች እንጂ እንደማጥጠፋ የእግዚአብሄርን ረቂቅ ስራ የሚያመለክት ነው።

፭) ጥልቅ፥ ተጠብቆ ሲነበብ ዘሎ እሰው ነገ ዉስጥ ያለአግባም በግባትን የሚያመለክት ሲሆን። “ምን ጥልቅ አረገህ” ማለት ምን አገባህ? ነገሩ አንተን አይመለከትም ማለት ነው። ስለዚህ ጥልቅ ህብረቃል ይሆናል ማለት ነው። ይህም ማለት ሰምና ወርቅን ሊፈጥር የሚችል ቃል ነው። አማርኛ በጣም ረቂቅ ወይም ጥልቅ ትርጉሞችን የያዘ ቁዋንቁዋ ነው። ብዙ ማለት ይቻላል ።

፭) ማጥለቅ: – ልብስ ጫማና ካልሲ ማጥለቅ ወይም መልበስ::

ጽድቅና ኩነኔ

ጽድቅና ኩነኔ ቢኖርም ባይኖርም
ከክፋት ደግነት ሳይሻል አይቀርም