ድርጊቶችን ባግባቡ መግለጽ

ድርጊቶችን ባግባቡ መግለጽ

ጠላ ይጠመቃል ገንፎ ይገነፋል
ጠጅ ይጣላል አረም ይታረማል
አረቄ ይወጣል ቅቤ ይነጠራል
እሸት ይጠረጠራል ንፍሮ ይቀቀላል
ፈረስ ይጋልባል ቆሎ ይቆላል
በቅሎ ይሰግራል እንጀራ ይጋገራል
ስጋ ይቆረጣል ይዘለዘላል ሎሚ ይመጠጣል
ዉሃ ይቀዳል እንጨት ይፈለጣል ወይም ይሰበራል
አጥር ይታጠራል በቆሎ ይጠበሳል ውይም ይቀቀላል
ድንጋይ ይካባል ማሺላ ይቆረጣል
አብሲት ይጣላል ጤፍ ይታጨዳል
ወጥ ይፈላል ሸንኮራ አገዳ ወይም ጥንቅሽ ይመጠጣል
ሙቅ ይሞቃል አልጋ ይነጠፋል
ነጋሪት ይጎሰማል በገና ይደረደራል
ከበሮ ይመታል ዳቦ ይደፋል