የጠቅላይ ሚንስቴር አብይ አህመድን የጅሩ (መሃል ሸዋ) ጉብኝትን በሚመለከት

የጠቅላይ ሚንስቴር አብይ አህመድን የጅሩ (መሃል ሸዋ) ጉብኝትን በሚመለከት

 

የጠቅላይ ሚንስቴር አብይ አህመድን የጅሩ (መሃል ሸዋ) ጉብኝትን በሚመለከት
የሰብአዊ መብት ረገጣ

ጠቅላይ ሚንስቴር አቢይ አህመድ ወደ ጅሩ (መሃል ሸዋ) እንድሚሄዱ ተስተጋብቶአል:: የስራ ጉብኝት ከሆነ ህዝቡ በስርአት ተገኝቶ ቢቀበላቸው መልካም ነው። ዋናው ነገር ይህ የሃገር ዋልታ ህዝብ እስካሁን ድረስ ተዘንግቶ ሳይሆን ሆን ተብሎ የመብራት የውሃ የጤና የመንገድና የትምህርት አገልግሎት ከሌሎች ወንድሞቹ ወደ ወደሁዋላ እንዲቀር በተለየ ሁኔታ ተነጥሎ መኖሩን ማስረዳት ብቻ ሳይሆን አፋፍ ድረስ በመዉሰድ እስካሁን ድረስ እንዴት አብዛኛው አምራች የሚገኝበት ቆላማው አካባቢ ከሁሉም አገልግሎቶች ተገሎ እንደኖረ በአይናቸው ይዩት።

እዉቀት ባላቸዉና በአንደበት ርቱእ የአካባቢው ተወላጆች አጭር ገለጻ ቢደረግላቸው መልካም ነው። በተለይ ዶክተር አብይን ወደ ላምዋሻ አፋፍና ወደ ሞረት መሄጃ (ሰገነት) በመዉሰድ በርቀት የሚገኙት ቦታዎች ከመንገድ ጀምሮ ከማንኛዉም ዘመናዊ አገልግሎት ዉጭ መሆናቸዉን በአይናቸው እንዲያዩት ማድረግ አለባችሁ።

በአይን እንዲያዩ ማድረጉ እሳቸዉንና አብረዋቸው ያሉትን ሰዎች ግንዛቤ ሊያስጨብጣቸው ይችላል። በተለይ ጂሩ አፋፍ ላይ ሆነው ከዠማ ባሻገር መርሃቤቴን (ማዶዉን) በማሳየት ከእነዋሪ መርሃቤቴ ከ50 ኪሎሜትር ባይበልጥም እስካሁን ድረስ ከጅሩ ቀጥታ ወደ መርሃቤቴም ሆነ ወደ መንዝ የሚያገናኝ መንገድ እንደሌለና ሰዎች ወደ ሁዋላ ወደ አዲስ አበባ ሄደው በጎጃም መንገድ በኩል እንደሚሄዱ የሚያሳዝነዉን ታሪክ

የጠቅላይ ሚንስቴር አብይ አህመድን የጅሩ (መሃል ሸዋ) ጉብኝትን በሚመለከት
በጣሊያን ጊዜ የተሰራ የተሽከርካሪ መንገድ

ብትነግሩአቸው ጥሩ ነው። ለዚያ ግብር ከፋይ ሃገር ጠባቂና ህዝብን መጋቢ ባለዉለታ ህዝብ ይሄ አይገባዉምነበር!!! በጠቅላይ ሚንስቴር አቢይ የሚመራው መንግስት ትኩረት ሰጥቶ ለቆላማዉም ሆነ ለደጋማው አካባቢ (ላምዋሻ አመድዋሻ ሽማና ሞረት) በአስቸኩዋይ የሚሰራቸው ስራዎች እንደአንገብጋቢነታቸው በቅደም ተከተል የሚከተሉት ናቸው።

፩) ፍትህ፥ ጸረ ሰሜን ሸዋ የወያኔ ቅጥረኞች ባስቸኩዋይ እንዲነሱና ሰሜን ሸዋ ዉስጥ ላለፉት 27 አመታት ላፈሰሱት 15000 የወግኖቻችን ደም ለፍርድ እንዲቀርቡ። አስተዳደሩም ሆነ የቀበሌዎች አመራር በተማሩና ስለ ሃገራቸው እዉቀት ባላቸው የአካባቢው ልጆች እንዲያዝ።

 

 

 

፪) መንገዶች

፫) መብራት

፬) ትምህርት ቤቶች

፭) ውሃ

፮) የህክምና ናቸው

 

የጠቅላይ ሚንስቴር አብይ አህመድን የጅሩ (መሃል ሸዋ) ጉብኝትን በሚመለከት
የእግር መንገድ

እርሻን በሚመለከት ያለዉን ሃገር በቀል እዉቀት ማሳደግና ገበሬዉን በመስኖ በመንገድ በመብራት በዉሃና በትምህርት ተጠቃሚ ማድርግና ምርቱን በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲሸጥ ወይም የጤፍ የስንዴና የሌሎች እህሎች የዱቄትና የምግብ ኢንዱስትሪዎች በአካባቢው ተከፍተው ገበሬው ነጋዴዉና ወጣቱ ተጠቃሚ እንዲሆን ማድረግ ነው። ጅሩ እንደሌሎች የአማራ አካባቢዎች ህዝቡ ብዙ ስለሆነ ሁሉም በየግል ይዞታው ደክሞ እያመረተ የተረፈዉን ሁልጊዜ ለአዲስ አበባና ለሌሎች ከተሞች ሲያቀርብ ቆይቶአል። አሁንም ለገበሬዉ ከላይ የተጠቀሱትን የልማት አገልግሎቶች በመስጠት ምርቱን ከፍ እንዲያደርግና ኑሮዉን እንዲያሻሽል መርዳት ነው።

ከዚያ ዉጭ አሁን ባለው ይዞታ የህዝቡ አሰፋፈርና ስራ አጥነት መካናይዜሽን የሚያስፈልግ አይመስለኝ። በግል ወይም በጋራ ትራክተር ገዝተው ማረስ የሚፈልጉ ገበሬዎች ካሉ ይችላሉ ግን በትራክተር የሚታረስ ብዙ ሰፋፊ ባዶ መሬት ሲኖር ስለሆነ ያልሆነ ጥያቄ መነሳት የለበትም። ቁልፍ ጥያቄዎች:-  መንገድ መብራት ትምህርት ቤት ዉሃና የጤና አገልግሎት ናቸው። መልካም እድል ለደጉ ወገኔ የጅሩ ህዝብና ለጠቅላይ ሚንስትር አብይ ጉብኝት።

 

የጠቅላይ ሚንስቴር አብይ አህመድን የጅሩ (መሃል ሸዋ) ጉብኝትን በሚመለከት
የጅሩ ድልብ የስጋ በሬ
የጠቅላይ ሚንስቴር አብይ አህመድን የጅሩ (መሃል ሸዋ) ጉብኝትን በሚመለከት
የጤፍ ሰብል